2012-11-28 13:33:55

ሪዮ ደ ጃነይሮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን WYD-Rio 2013 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.)
ብፁዕ ካርዲናል ርይልኮ፦ ሪዮ የአሰተናጋጅነት ከተማ ምልክት ነች


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ከተማ እንዲካሄድ ለወሰኑት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማዘጋጃ በተለያየ መልኩ በተለያዩ አገሮች በብሔራዊ አቀፍ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ ሳምንት በሪዮ ደ ጃነይሮ የዓለማውያን ምእመናን ሐዋራያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ የሪዮ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዖራኒ ዡዋው ተምፐስታ የተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ድርገት፣ የወጣት ካቶሊክ ማኅበራት፣ የዓለማውያን ምእመናን ማኅበራት ተጠሪዎች በማሳተፍ እየተካሄደ ባለው የማዘጋጃ ጉባኤ የሪዮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለየት የሚያደርገው በእምነት ዓመት የሚካሄድ መሆኑ መስተጋባቱ ለማወቅ ተችለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ርይልኮ ለስብሰባ ከሚገኙበት ከሪዮ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ከጋዜጠኛ ራፋኤለ በሊንካን ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የሪዮ እ.ኤ.አ. የ 2013 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተዋጣለት እንዲሆን በሪዮ በመካሄድ ላይ ያለው የቅድመ ዝግጅቶች ገምጋሚ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከ 75 የተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ልኡካን ከ 40 በላይ ከሚገመቱት የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ ማኅበራት፣ እንቅስቃሴዎች የተወጣጡ ልኡካን ያሳተፈ ብቻ ሳይሆን በእውነቱ ሪዮ አስተናጋጅነቷ ቀርቦ ያጣጣመ ጉባኤ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለማክበር 238 ቀናት የቀሩት ሲሆን፣ ይህ የብራዚል የኮርኮቫዶ እጆቹን የዘረጋው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትልቁ ሐውልት አርማ ያደረገ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የጌታችን ኢየሱስ ፍቅር ኵላዊነቱን የሚመሰክር ነው። ክርስቶስ የወጣቱ ትውልድ ሕይወት እውነትና መንገድ እንዲሆን ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት የሚመጣ ነው። ስለዚህ ወጣቱ ትውልድ በክርስቶስ የተለወጠ አዲስ-እውነት ሕይወት እንዲኖረው ከክርስቶስ ጋር እንዲገናኝ ቅድስት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ሊከተለው የሚገባው መንገድ የሚገነዘብበት ቀን መሆኑ ጉባኤ በተለያዩ መልኩ እንዳሰመረበት ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.