2012-11-26 14:25:57

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “የኢየሱስ የህጻንነት ጊዜ”


RealAudioMP3 ሁሌ መሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በቅርቡ ለንባብ የበቃው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 “የኢየሱስ የህጻንነት ጊዜ” በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው መጽሐፍ ይኸው በ9 ቋንቋዎች ተተርጉሞ በ 50 አገሮች መሰራጨቱንም አስታውሰው፣ ይኽ ቅዱስ መጽሐፍ ባህል በቲዮሎጊያና በሥነ መንፈሳዊነት እጅግ ሃብታም የሆነው የቅዱስነታቸው መጽሐፍ በዚህ ለበዓለ ልደት በምንዘጋጅበት የምጽአት ወቅት ለንባብ የበቃ በመሆኑ በርግጥ አቢይ ጸጋ ነው። በዚህ የምጽአት ዘመን የሚሸኘን ጥልቅ መጽሐፍ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅበራዊ ሕይወት፣ ስቃይና ትንሣኤ ላይ በማተኮር ከደረስዋቸው መጻሕፍት በመቀጠል ይኸንን የናዝሬቱ ኢየሱስ ርእስ ሥር የጀመሩት ድርሰት በዚህ የኢየሱስ የሕጻንነት ጊዜ በሚል ርእስ ሥር በደረሱት መጽሐፍ ሥር በማሟላት ቀድመው እንዳሉትም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ቃሉና ተግባሩን በጥልቅ ለማብራራት የነበራቸው ፍላጎት እግብር ላይ በማዋል፣ ይኽ መጽሐፍ ከሚያቅፈው የገጽ ብዛት አንጻር ሲታይ ትንሽ ቢመስልም ቅሉ መልእክቱ ሰፊና ጥልቅ ነው። ወደ ኢየሱስ የሚመራ ከኢየሱስ ጋር እንድንጓዝ የእርሱ ወዳጆች ለመሆን የሚደግፈን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ጥልቅ አስተንትኖና መንፈሳዊነት የሚያገልጽ መጽሐፍ ነው።
የታሪክን የእምነትን ኢየሱስ የሚያጠቃልል፣ ከእውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንድንገናኝ የሚደገፍ መጽሐፍ ነው። እንዲህ መሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ኃላፊነት ያረጋግጥልናል። ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስታይን እምነትና ተግባር ሐዋርያዊ ኃላፊ ናቸው። ስለዚህ የእያንዳንዳችን እምነት ለማጽናት የደረሱት መጽሐፍ ነው። የናዝሬቱ ኢየሱስ አደኛው መጽሐፍ ለንባብ ለማብቃት ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ የተሳተፉት በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ብፁዕ ካርዲናል ማርቲኒ “የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሐፍ የእግዚአብሔር ልጅ በበለጠ እንድናውቀውና እንድንገነዘበው የሚያበቃ የደራሲው አቢይ እምነት የሚመሰክር ነው” እንዳሉ አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ ይኽ አዲስ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሐፍ ይኸንን የነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ማርቲኒ አባባል የሚያረጋግጥ ነው በማለት ያቀረቡትን የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.