2012-11-26 14:23:29

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲስ ካርዲናላት ሰየሙ
በአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አምናለሁኝ


RealAudioMP3 “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላ የሰውን ዘር የሚያቅፍ በመሆኑ ቤተ ክርስትያን ካቶሊክ ነች”
ባለፈው ቅዳሴ በላቲን ሥርዓት ዓመታዊ የክርስቶስ ንጉሥ በዓል ዋዜማ ቅዱስ አባታችን በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ስድስት ከተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳትን የካርዲናልነት ማእርግ እንደሰጡ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ የካርዲናልነት ማእርግ የተቀበሉት የጳጳሳዊ ቤት ኅየንተ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት የጳጳሳዊ የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ፎሮ ለ ሙራ ሊቀ ካህናት እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን የተሸሙት ብፁዕ አቡነ ጀምስ ሚካየል ሃርቨይ፣ በሊባኖስ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስታይን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ በቻራ ቡትሮስ ራይ፣ በህንድ የሶሪያ ማላንካረሰ ሥርዓት ለምትከተለው ቤተ ክርስትያን አቢይ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ባሰሊይስ ክሊሚስ ቶቱንካል፣ በናይጀሪያ የአቡጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆን ኦሎሩንፈሚ ኦናየካን፣ በኮሎምቢያ የበጎታ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሩበን ሳላዛር ጎመዝና በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ መሆናቸውም አስታውቀዋል።
እንዲህ ባለ መልኩም በጠቅላላ የኵላዊት ቤተ ርክስትያን የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት 211 ሲሆኑ፣ 120 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመምረጥ መብት ያላቸውና ዘጠና አንዱም የካርዲናላት ጉባኤ አባላት ቢሆኑም በእድሜ መግፋት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምርጫ የማይሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለነዚህ ስድስት ብፁዓን ጳጳሳት የካርዲናልነት ማእርግ ሰጥተው ባሰሙት ስብከት፦ “የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ እንደሚያመለክተውም፦ ‘ቤተ ክርስትያን አንዲት ካቶሊካዊት ሐዋርያዊት ነች” ለዚህ መሆን የሚያበቃት ያ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ይኸንን ዓይነት ምልክት በተግባር እንድትኖር የጠራት ክርስቶስ ነው (ቍ. 811)። ቤተ ክርስትያን ካቶሊካዊት ነች፣ ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ በማደን ተልእኮው መላው የሰውን ዘር ስለ ሚያጠቃልል ነው። ይኽም በወንጌል ማቴ. ምዕ. 15 ቍ. 24 ‘እኔ የተላክሁት ከእስራኤል ቤት እንደ በጎች ለጠፉት ነው’ አክሎም በምዕራፍ 8 ቍ. 11 ‘…ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፣ ከአብራሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ ጋር በመንግሥተ ሰማይ ይቀመጣሉ’ በሚለው ቃሉ የማዳን እቅድ ኩላዊ ባኅርዩን አረጋግጦልናል፣ የዕለቱ ምንባበ ወንጌል ማር. ምዕ. 10 ቁ. 33 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገዛ እራሱ ‘የሰው ልጅ’ ሲል ይገልጣል፣ ይኸንን በነቢይ ዳንኤል ምዕ. 7፣ ከ 13-14 ‘የሰው ልጅ የሚመስል…ከስማይ ደመናት ጋር መጣ’…’ ከሚለው ሃሳብ ጋር በማጣመር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሐዊ ተልእኮው መላውን የሰውን ዘር የሚያቅፍ መሆኑ ያረጋግጥልናል። ቤተ ክርስትያን በዚህ ተልእኮ መሠረትም መከፋፈል መለያየት በክርስቶስ መሸነፉ በመመስከር፣ በእርሱ ሰብአዊነት እንድንማረክም በእርሱ አማካኝነት በእግዚአብሔር ሱታፌ እንዲኖረን እርሱ ያወጀውን የእግዚአብሔር መንግሥት ታውጃለች። ጥሪዋም ይኽ ነው” ብለዋል።
“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያኑ ወደ አንድ የኅብረተሰብ ክፍል ሳይሆን ወደ መላው ሰው ዘር በመላክ፣ አህዛብ አንድ ህዝብ ለመሆን በእርሱዋ ዙሪያ በመሰባሰብ ከእርስዋ ጋር እንዲያብሩ መጠራታቸው ያረጋግጥልናል። ይኸንን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በ ‘Lumen gentium-ብርሃነ አሕዛብ’ በተሰየመው ዶግማዊ ውሳኔው አማካይነትም፣ የቤተ ክርስትያን ኩላዊነት ባህርይ የሚያረጋግጥ ሥልጣን ሲሆን፣ ከጥንት ጀምራ Kat’holon-ሁሉንም የምታቀፍ ‘አድማስ’ ነች (ግብረ ሐዋ. 2, 7-8፣ 1,8 ተመልክተ) የቤተ ክርስትያንት ተልእኮ ሁሉንም የሚያቅፍ ከታች ሳይሆን ከላይ ከመንፈስ ቅዱስ የወረደ ሥጦታ ነው። የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ኵላዊነት ያለው ይኸንን በክርስቶስ የተኖረ ክርስቶስ በገዛ እራሱ ለደቀ መዛሙርት በሰጠው ትእዛዝ ያረጋግጠዋል (ማር. 16,15 ማቴ. 28,19)። ግብረ ሐዋርያት እንደሚያመለክተውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ደቀ መዛሙርቱ ራእያቸው በዳዊትነት መንግሥት ላይ አኑረው በገዛ እራሳቸው ላይ ተዘግተው እያሉ፣ መንፍስ ቅዱስ በላያቸው ላይ በማውረድ የመዳን እቅድ ኩላዊ መሆኑ ታምነው ለዚህ ተልእኮ እንዲጠመዱ ብርታቱን ሰጥቷቸዋል።
ቤተ ክርስትያን በእየሩሳሌም በአንጽዮኪያ በሮማ …እና በሌሎች ሥፍራም የምትመሠረተው ቤተ ክርስትያን “አንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ነች፣ ሐዋርያዊትም ነች፣ ይኽ ትእምርተ አንድነትና ሲታፌ በቅድስት ሥላሴ አምሳያ የሚመሰል ሲሆን፣ ይኽ አንድነት የቤተ ክርስትያን ኩላዊነት ባህርይ የሚኖር ሆኖ በብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ የሚገለጥ ባህርይ ጭምር ነው ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ጴንጠቆስጣዊ ነች” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እያንዳንዱ ብፁዕ ካርዲናል የሚፈጽመው ቃለ ማሕላ “መላ የሕይወቴ ዘመን ክርስቶስን ወንጌሉን ቅድስት ሓዋርያዊት ሮማዊት ‘በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሮማ ጳጳስ ሥር የሚኖር’ ቤተ ክርስታያን ካለ ማቋረጥ በቋሚና ቀጣይ ተአዛዞ የሚኖረው ውሳኔ” የሚያመለክት መሆን አብራርተው፣ ‘ቀዩ ቆብ’ ለሰማዕትነት ዝግጁ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ምልክት ነው፣ ቀለበቱም ከቤተ ክርስትያን ጋር የሚያጸኑት የፍቅር ትሥሥር ነው፣ ይኽም ከቅዱስ ጴጥሮስ በካርዲላኖች ጉባኤ ከአበይት የቅድስት መንበር ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲላኖችና ሊቀ ጳጳሳት ጋር እንዲሁም ከሕዝበ እግዚአብሔር ጋር የሚኖሩት ውህደት ነው።” ብለው፣ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር በመተባበር የሕዝበ እግዚአብሔር የዓንቀጸ ሃይማኖትና ሥርዓትና ተአዛዞ አቅቦ መኖሩ፣ በሕይወትና በቃል ምስክር ሆነው፣ በመከታተል የሚያንጹ መሆናቸው ገልጠው፣ ስለ ወዳጁ ገዛ እርሱን የሚሰዋው ፍቅር አብነት ሆነው ለመኖር የተጠሩ መሆናቸውም አስታውሰው፣ ቆራጥ የክርስቶስ ተክታዮች ሆነው እንዲገኙ እግዚአብሔር እንዲያበረታቸው እንጸልይ፣ በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.