2012-11-23 17:01:34

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምርህተ ክርስቶስ (21.11.2012)


ውድ ውንድሞችና እኅቶች፧ በዚሁ የእምነት ዓመት በእምነት ምን ያህል ደስታ እንዳለ ለመረዳት እና የእምነት እውነትን ለሁሉ ለማዳረስ አዲስ ኃይል በማፈላለግ እንገስግስ፣ እነኚህ የእምነት እውነቶች እግዚአብሔር ስለ ገዛ ራሱ የሚሰጠን መረጃዎች የያዘ ቀለል ያለ የእግዚአብሔር መልእክት አይደሉም፣ አዳኙና ነጻ አውጪ የሆነ የእግዚአብሔርና የሰው ልጆች ግኑኝት ይገልጣሉ፣ ይህ ግኑኝነት የሰው ልጅ ጥልቅ ፍላጎት የሆኑ የሰላም የወንድማማችነትና የፍቅር ፍላጎቶች እውን ያደርጋል፣ እምነት ከእግዚአብሔር ግኑኝነት የሚያስገኝልን ዕሴትን ዋጋ ለመስጠት እና በሰው ልጅ ባህርይ ያለውን እውነት ርኅራኄና መልካም ነገርን ከፍ እንዴት ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ያብራራል፣ በእንዲህ ያለ ጉዞ እግዚአብሔር ራሱን በመግለጥ የሰው ልጆች እንዲያውቁት ሲያደርግ የሰው ልጅም እግዚአብሔርን በማቀቅ ገዛ ራሱን በይበልጥ በማወቅ መነሻውና መድረሻውን ይገለጥለታል እንዲሁም የሰው ልጅ ሕይወት ምንኛ ታላቅና ክቡር መሆኑን ይገነዘባል፣
እምነት ለሰው ልጅ ሓቀኛ የእግዚአብሔር እውቀትን ይሰጠዋል፣ ይህ እውቀት ጠቅላላ የሰው ልጅን ያካትታል፣ ለሕይወት ትርጉም የሚሰጥ ለኑሮም አዲስ ጣዕም የሚሰጥ እና በዓለም መኖርም እንዴት ደስ የሚል መሆኑንም የሚያረዳ እውቀት ይሰጣል፣ እምነት ገዛ ራስን ለሎች መስዋዕት በማድረግ ይገለጣል፣ ይህም የሚያሳዝን ብቸኝነትን በማሸነፍ ለማፍቀር የሚያስችል የመተባበር መንፈስ በማስረጽ ወንድማማችነት ይፈጥራል፣ ይህ በእምነት የምናገኘው በኧእምሮ ብቻ የምናሰላስለው የአመክንዮ እውቀት ብቻ አይደለም የሕይወት ጉዳይም ነው፣ ለፍቅሩ ምስጋና ይግባውና ይህ እውቀት ፍቅር የሆነው እግዚአብሔርን የምናውቅበት ነው፣ ፍቅር ዓይኖቻችንን በመክፈት እንድናይ ያደርጋል፣ እውቀታችንን ከሚጠመዝዙ ግላዊ አስተያየትና እኔነት ባሻገር በዓለም ያሉ ነገሮችን ሁሉ እንድናውቅ አእምሮአችንን ይከፍትልናል፣ እንዲህ ስንል ግን የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ትይዩ በሆነ መንገድ የሰው ልጅ የአመክንዮ (አእምሮ) እና የኅልና ጉዞም ነው፣ የሰው ልጆች ልብ ጥልቅ በሆነ መንገድ የኢየሱስ መንፈስ በነካው ግዜ ሁላቸውን የእኔነት አስተያዮቶች በማሸነፍ የሕይወት እውነተኛ ዕሴቶች ለሆኑ ነገሮች ክፍት ይሆናል፣
ዛሬ በዚሁ ትምህርተ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ማመን እንዴት በሰው ልጅ አእምሮ ሊሰላሰል እንደሚቻል እንመለክታለን፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ልማድ በመጀመርያ ዘመናት ፊደዪዝም ወይም ዕውር እምነት የሚል አስተሳሰብን ያወግዝ ነበር፣ ይህም ማለት የማይረዳ ስለሆነ አምናለሁ የሚል ነበር፣ እግዚአብሔር ምሥጢር ይሁን እንጂ፣ የማይረዱት መሥረተ ቢስ ነገር ወይንም አብሰርድ አይደልም፣ ምሥጢር ሲባል ምክንያተ አልቦ ወይንም ኢራሽራል ማለት አይደለም ነገር ግን እጅግ ከፍ ያለ ስሜት ትርጉም እና እውነት ያለው ነው፣ ምሥጢርን የተመለከትን እንደሆነ አ እምሮ አችን ጨለማን ያያል ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ በምሥጢር ብርሃን ስለሌለ ሳይሆን እጅግ ብዙ ብርሃን ስላለ ነው፣ ለምሳሌ የሰው ልጅ ዓይኖት በቀጥታ ጸሐይን የተመለከቱ እንደሆነ ምንም ማየት ስለማይችሉ እንዲያው ጸሐይ የብርሃን ምንጭ ሳለች፣ ጸሐይ ብርሃን አይደለችም ለማለት የሚችል ማነው፧ እምነትም ጸሐይ የሆነውን እግዚአብሔር ለማየት ያስችለናል፣ ምክንያቱም በታሪክ ለተገለጠውን እግዚአብሔር በመቀበል ጠቅላላውን የእግዚአብሔር ምሥጢር ብርሃን ይቀበላል፣ በዚህም እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጅ የቀረበበትንና በተፈጥሮው አእምሮ ዕውቀት ደረጃ በመስተካከል እንዲያቀው በመፍቀዱ የመፍቀዱ ታላቅ ተአምርን ያመሰግናል (ብርሃነ አሕዛብ 13)፣ እንዲሁም በዚሁ ግዜ እግዚአብሔር አእምሮውን ያበራለታል ወደር ወሰን የሌላቸው አዳዲስ መአዝኖችም ይከፍትለታል፣ በዚህም እምነት ሁል ግዜ የማይጨረሸውን የእውነትና የነገሮች ሁኔታን ለማካበት አለማቋረጥ የእውቀት አሰሳ ያካሄዳል፣ ስለአንቀጸ እምነት አንዳንድ ዘመናውያን ሊቃውንት “አንቀጸ እምነቶች አእምሮአችንን ይጋርዳሉ” ብለው የሚያስተምሩት ትምህርት ሐሰት ነው፣ ታላላቅ የካቶሊካዊ ልማድ አስተማሪዎች እንደገለጹት አንቀጸ እምነቶች በአንጻሩ አእምሮአችን ይከስታታሉ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ ወደ ክርስትና ከመመለሱ በፊት እውነትን ያኔ በነበሩ የተለያዩ የፍልስፍና መንገዶች አለእረፍት ይፈልጋታል ሆኖም ግን አያገኛትም፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ አድካሚ የአእምሮ የእውነት ፍለጋ ከክርስቶስ እውነት ጋር ለመገናኘት የሚደረገው ፍለጋን ያመለክታል፣ በመጨረሻም “ለማመን ተረዳኡ ለመርዳትም አመንሁ” ያለው የመላው ሕይወቱ የትምህርት ጉዞን እንደማመልከት ነው፣ አእምሮና እምነት ተገልጾን በሚመለከት ለእያንዳንዳቸው ባዳ ወይንም ተቃራኒ አይደሉም ሆኖም ግን ሁለቱም ትርጉምን ለመረዳት የሚረዱ ናቸው በዚህም እውነተኛውን መል እክት ለመረዳትና በምስጢሩ ደጅ ለመድረስ ይችላሉ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ ከሌሎች የክርስትያን ጸሐፊዎች ጋር በመሆን ከአመክንዮ ጋር የሚስማማ እምነት እንዳለ ይመስክራሉ፣ ይህም አመክንዮ የሚያስብና ለማሰብ የሚጠራ ነው፣ ይህንን በተመለከተ ቅዱስ አንሰልሞ ፕሮስሎⷞን በሚለው ድርሰቱ ካቶሊካዊ እምነት የአመክንዮ አሰሳ እምነት ነው ይላል፣ በዚህም የአ እምሮ አችን አሰሳ የእምነት ውስጣዊ ሥራ ይሆናል፣ ከሁላቸው በላይ ግን ቅዱስ ቶማስ ዘአኵኖ ይህንን ልማድ ከዘመኑ ፍላስፋዎች የአ እምሮ አሰሳ ጋር በማያያዝ የአመክንዮ ዋና አሰሳ በሰው ልጆች አ እምሮ ውስጥ ከክርስትና እምነት እውነትና ከሰው ልጅ አእምሮ ጋር ከተያያዘው ዋና የማሰብ ስጦታ እንደሚመንጭ ያመለክታል፣ የካቶሊካውያን እምነት ሰለዚህ ሁሉንም የአሰሳ ፍላጎቶች ያሟላ ስለሆነ ለሰው ልጅ አእምሮም መተማመንን ያፈልቃል፣ ለዚህም ነው አንደኛው የቫቲካ ጉባኤ ደይ ፊልዩስ በሚለው አንቀጸ እምነታዊ ሰነድ “የሰው ልጅ አእምሮ በእርግጥነት የእግዚአብሔርን መኖር ከፍጥረት ሊረዳ ይችላል ሆኖም ግን ያለመሳሳት በትትክለኛነት ቀላል በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ማወቅ የእምነት ተግባር ነው ይላል፣ ይህ እውቀት እግዚአብሔርን የሚመለከቱ እውነቶች በብርሃነ ጸጋው እንደሚሰጠን ያመለክታል፣ በሌላ አነጋገር የእምነት እውቀት የአ እምሮ እውቀትን አይቃረንም ለማለት ነው፣ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፊደስ ኤት ራጽዮ እምነትና አመክንዮ በሚለው ሐዋርያዊ መል እክታቸው “የሰው ልጅ አ እምሮ የእምነት እውነቶችን በመቀበል አይደመሰሰም ወይንም ዝቅ አይልም ምክንያቱም የእምነት እውነቶች አውቆና ነጻ በሆነ ፍላጎት የምንቀበላቸው እውነቶች ስለሆኑ” ይላሉ፣ በአእምሮአችን ውስጥ ያለው የማይረካ ታላቅ የእውነት ፍላጎት ሊረካ የሚችለው እምነትና አመክንዮ የተዋሃሃደ ግኑኝነት ሲኖራቸው ብቻ ነው፣ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰውና የገዛ ራሳችን ሁኔታ በሙላት የሚከስትልን ይህ መንገድ ብቻ ነው፣
ይህ ዓንቀጸ እምነት በመላው የአዲስ ኪዳን ጽሑፎች ጎልቶ ይታያል፣ ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ ለነበሩ ክርስትያኖች ሲጽፍ “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥”(1ኛ ቆሮ 1፤22-23) ይላል፣ እንደ እውነቱም ከሆነ እግዚአብሔር ዓለምን በታላቅ የእብሪት ችሎታ ሳይሆን በአንድያ ልጁ ትሕትና አማካኝነት ነው ያዳነው፣ እንደ ሰው ልጆች አስተሳሰብ ይህ ጌታ የፈጸመው የድኅነት ተግባር የግሪካውያን ጥበብን የሚቋወም ሆኖ እናገኘዋለን፣ ሆኖም ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው የክርስቶስ መስቀል አንድ አመክንዮ አለው ይህም “ቃለ መስቀል” ነው፣ ይህ ቃል የሚለው በግሪክ ሎጎስ የሚሉት ሆኖ አእምሮን አመክንዮን በማመለከት አእምሮአችን ያሰላሰልውን በአፍ የሚገልጥ ቃል በመሆኑ ከማንኛው ቃል በላይ ነው፣ የአመክንዮ ውጤት ለማለት ያህል፣ ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ በመስቀል ሞኝነት ወይንም ኢምክንያታዊነት ሳይሆን ምክንያታዊ የሆነና በእምነት ብርሃን አ እምሮ አችን ሊረዳው የሚችል የድኅነት ተግባር ያያል፣ በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ በሰው ልጅ አእምሮ ያለውን እምነት ያሳያል፣ እግዚአብሔር የሠራውን ሁሉ እያዩ የእርሱን ህልውና ለመረዳትና በእርሱ ለማመን በማይችሉ ብዙ ሰዎች ደግሞ ይደነቃል፣ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱም “የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።”(ሮሜ 1፤20) ይላል፣ እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ በስደት ለሚገኙት የዘመኑ ክርስትያኖች “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።”(1ጴጥ 3፤15) ሲል ስደት በሞላበትና እምነታቸውን የመመስከር ግዴታ በነበረባቸው ጊዜ አማኞቹ በቃለ ወንጌል ማመናቸውንና በዚህም ለተስፋችን የሚያብራሩና የሚያስረዱ ተጨባጭ መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠይቃቸዋል፣ በዚሁ በማመንና መረዳት መካከል ያለው መተሳሰር የሳይንስና የእምነት ግኑኝነት ይመሰረታል፣ የሳይንስ አሰሳ ሁሌ በሰው ልጅና በምንኖርበት ዓለም የሚገኙ አዳዳሲስ እውነቶችን ለማወቅ ያስችለናል፣ ይህንን ሁሌ እንመለከታወለን፣ በእምነት መድረስ የሚቻለው እውነተኛው የሰው ልጅ በጎ ነገር የሰው ልጅ ለመመራመር በሚያካሄደው ጉዞ ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲከተል ይከስትለታል፣ ለምሳሌ ያህል ሕመሞችን በማሸነፍ የሰው ልጅ ሕይወትን ለማገልገ ጥናቶችና አሰሳዎች ይደገፋሉ፣ የምንኖርበት ዓለምና ኅዋ ውስጥ ያሉትን ምሥጢራ ለማወቅ የሚደረጉ ጥናቶችና አሰሳዎችም አስፈላጊዎች ናቸው፣ ሆኖም ግን የሰው ልጅ የፍጥረት ሁሉ የበላይ መሆኑን ተረድቶ እነኚህን ፍጥረታት እንዲጠብቃቸውና ለመኖር የሚያመቹ እንዲያደርጋቸው እንጂ አለአግባብ እንዲመዝምዛቸው እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፣ በእውነቱ የተመለከትን እንደሆነ እምነት ከሳይንስ ጋር አይጋጭም እንዲያው ዋነኛ ከሆነው የእግዚአብሔር ዕቅድ የሚቃረኑ ነገሮችን ትቶ ለሁሉም የሚሆን በጎ ነገርን ለማዳበር መሠረታው መምዘኛ በመቀበል ለሰው ልጅ ጉጂ የሆኑ ነገሮች ከማፍራት እንዲቆጠብ በመጠየቅ ይተባበረዋል፣ ለዚህም ማመን ምክንያታዊ ነው፣ ሳይንስ እግዚአብሔር ለዓለማችን ካለው ዕቅድ ጋር የሚስማማ እንደሆነ እምነትም ለዚሁ ዕቅድ ታማኝ በመሆን ሳይንስ ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ነገርና ለእውነት አሰሳ እንዲያካሄድ ትፈቅደዋለች፣
የሰው ልጅ ለእምነት ክፍት በመሆን እግዚአብሔርን እንዲያውቅና በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሰጠው ድኅነት እንዲቀበል ይጠብቃል፣ በወንጌል የተመለከትን እንደሆነ አዲስ ሰብ አውነትና የሰው ልጅና የሁሉም ፍጡር አዲስ ሰዋስው እናያለን፣ ለዚህም አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ሃይማኖት “የእግዚአብሔር እውነት የተፈጥሮ ሥር ዓትን የሚያዘውና ዓለምን የሚገዛ ጥበቡ ነው፣ እያንዳንዱ የፈጠረው ነገር ከእርሱ ጋር ስላለው ግኑንነት እውነተኛ እውቀት የሚሰጠው ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ብቻ ነው”(ቍ 216) ይላል፣
ስለዚህ ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል መነሳታችን በዘመናችን ላሉ ሴትና ወንድ ልጆች ሕይወት ውስጥ በመግባት አዲስ የወንጌል ማእከልነት ለመስጠት ይርዳን፣ የኑሮ ትርጉምና የእውነተኛ ነጻነት መሠረት በሆነው ክርስቶስ እንድንገናኝ እንጸልይ፣ አለ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ገዛ ራሱን ያጠፋል፣ ቀድመው ያለፉንና ሕይወታቸውን ወንጌል ለመስበክ የሰጡ ይህንን ያረጋግጡናል፣ እምነት የሚረዳ ነው፣ ሕይወታችን ይመሰክረዋል፣ በሰው ልጅ ነፍስ የተመሠረተውን በጎ ነገር እና ለእውነት ያለውን ፍላጎት ሊያረካ የሚችል ጊዜው የማያልፍ ዕለቱ የማያልቅ የዘለዓለም ብፅዕና በሆነው በክርስቶስ መተማመንና ሕይወትን ለእርሱ መስጠት ዋጋ አለው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.