2012-11-23 14:16:26

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ከያኒያን የእምነት ውበት መስካሪያን ናቸው


RealAudioMP3 “ውበት የእምነት መስካሪ፣ ከያኒ እንደ ቤተ ክርስትያን የእምነት ውበት መስካሪ” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ስልጣን መሠረት ያወጁት እምነት ዓመት ምክንያት ያስተላለፉት “Porata Fidei-የእምነት በር” የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት በማስደገፍ እንዲሁም የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የባህል ሃብት ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት በጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሥር እንዲጠቃለል ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን አማካኝነት የሰጡት የውሳኔ ሰነድ ጭምር በማስደገፍ፣ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ለጠራው 17ኛው የጳጳሳዊ ተቋሞች ይፋዊ ጉባኤ፣ ቅዱስ አባታችን መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ለዚህ ትላትና በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ፒዮስ አሥረኛ የጉባኤ አዳራሽ ተጋባእያን በባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በኩል ባስተላለፉት መልእክት፦ “የእምነት ውበት ከያኒ በፈጠራ ችሎታውና በስነ ጥበባዊ ብቃቱ ለሚገልጠው ውበት እንቅፋት መሆን አይችልም ምክንያቱም የእምነት ውበት የሕይወት ምንጭና የፍጻሜ ወይንም የሁሉም መድረሻ አድማስ መሠረት ነው” ብለዋል።
“እውነተኛው ከያኒ” ይላሉ ቅዱስ አባታችን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዋቢ በማድረግ፦ “የዓለም ውበት አቃቢና ላለው የስነ ውበት የመገንዘብ ስሜት፣ ፈጣን የማስተዋል ተሰጥኦና ውበት ቀድሞ የማጤንና በተለይ ደግሞ እምነት ያለው ውበት የማስተናገድና ተጨባጭ አድርጎ የማቅረብ ችሎት የተካነ በመሆኑ ከእምነትና ከአምልኮ ከቤተ ክርስትያን ሊጡርጊያ ተግባር ተመክሮ ጋር ጥብቅ ግኑኝነት ያለው ነው” ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት እ.ኤ.አ በ 1931 ዓ.ም. የመጪው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተሾሙት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ገና ካህን ጆቫኒ ባቲስታ ሞንቲኒ “መንፈሳዊ(ቅዱስ) ስዕሎች የዚያ ወደር የሌለው ለመግለጥ የማይቻለውን ውበት መግለጫ ነው” በማለት ቅዱስ ስዕሎች ያላቸውን ክብር ያሰመሩበት ሃሳብና እንዲሁም በዚህ የተገባው የእምነት ዓመት ከያንያን የሰነ ጥበብ ባለ ሙያዎች ምክንያት ለከያኒያን ያስተላለፉት መልክት ጭምር በመጥቀስ፣ “በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመላ ሰብአዊ ታሪክ ቦግ የሚያደርግ የእግዚአብሔር አምሳያ ክብር በሆነው ላይ ላለን አሜን ያለው እጹብ ድንቅ ውበት ፍቱን ምስክርነት በማቅረቡ ረገድ የስነ ጥበብ ሙያ በጠቅላላ ግብረ ከያኒያን ያለው አስተዋጽዖ አቢይ ነው” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬ መለገሳችው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.