2012-11-21 15:08:01

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ አዲሱ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሐፍ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 “የኢየሱስ የህጻንነት ጊዜ” ርእስ ሥር የደረሱት አዲስ መጽሐፍ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በፒዮስ አሥረኛ የጉባኤ አዳራሽ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ጉባኤ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ፣ ብራዚላዊቷ የቲዮሎጊያ ሊቅ ማሪያ ክላራ ቢንግመር የቫቲካን ማተሚያ ቤት ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አባ ጁዜፐ ኮስታ፣ የሪዞሊ ማተሚያ ቤቶች ሊቀ መንበር የሥነ ታሪክ ሊቅ ጋዜጠኛ ፓውሎ ሚየሊ ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ይክ መጽሐፍ በ 9 ቋንቋች ተተርጉሞ በ 50 አገሮች መሰራጨቱንም አባ ሎምባርዲ ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያላቸው ጴጥሮሳዊ ኃላፊነት ሥፋትና አድካሚነት ሁሉም የሚያውቀው ነው፣ ሆኖም እንዲህ ያለ ጥልቅና ሰፊ መጽሐፈ ደርሰው ሲለግሱ የመጀመሪያቸው አይደለም” ሲሉ፣ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ በበኩላቸውም፣ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ የደረሱት መጽሐፍ ባለፈ ታሪክ የሚታጠር ትረካ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ኵላዊ የሰው ልጅ ታሪክ የሚተነትን ያለፈ ያለ የሚኖር የሰው ልጅ ጭኾት ስቃይ መከራ ትርጉምና መልስ የሆነውን የሚያስታውቅ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት ዘመን የነበረው የሰው ልጅ እንባ ዛሬም በዚህ በምንኖርበት ታሪክ የሚታይ እውነት ነው። የጋዛን ሕጻናትን እናስብ” ካሉ በኋላ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕጻንነት ታሪክ የሚያወሳው መጽሐፍ የወንጌል መጽሐፍትን የሚዳስስ ወንጌላዊ ነው። ስለዚህ ሕጻን ሲባለ የደረሰ አማኝ ማለት መሆኑ የሚያረጋግጥና ይኽንን ለማለት የሚያችለው ምክንያት ግልጽ በሆነ አነጋገር የሚያብራራ መጽሐፍ ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
የቲዮሎጊያ ሊቅ ማሪያ ክላራ ቢንገመር በበኵላቸውም፦ “ይኽ መጽሐፍ ጸጋ ነው በማለት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በደረሱት መጽሐፍ አማካኝነት የምናከብረው በዓለ ልደት ዘእግዚእነ ሊሰጠው የሚገባው ትኵረትና አቢይና ጥልቅ ትርጉም በማብራራት፣ ለዚህ ቅዱስ ሕጻን የተገቡ ሥፍራ ሆነን እንድንገኝ ማንነቱን በጥልቀት መገንዘብ ያለው አስፈላጊነት የሚተነትን ያለንበት ዘመን ከምን ጊዜም በበለጠ ወንጌል እጅግ እንደሚያስፈልገው የሚያረጋግጥና የሚመሰክር መጽሐፍ ነው” እንዳሉ ጂሶቱ አስታወቁ።
አባ ኮስታ ይኽ አዲሱ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሐፍ፦ “የዮሴፍ የማርያም እምነት መስካሪ ነው። ስለዚህም የእኛ እምነት የሚመሰክርም ነው” ሲሊ ፓውሎ ሚየሊ በበኩላቸውም፦ በማርያም የእንዳልከው ይሁንልኛ መልስ አማካኝነት መቀበለን ሱታፌን ዋና ተዋናያን መሆን የሚል ሁሉም በእምነት ሊኖረው የሚገባው ባህርይና ጸባይ የሚያስረዳ” መጽሐፍ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችልዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.