2012-11-21 15:04:38

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ “የኢየሱስ የህጻንነት ጊዜ” ርእስ ሥር የደረሱት አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ


RealAudioMP3 ወንጌላውያን ማቴዎስና ሉቃስ ወንጌላዊ መልእክታቸውን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የህጻንነት ጊዜ በመንደርደር ሲያጀምሩ ምን ለማለት ፈልገው ነው? ታሪኩ እውነት ነውን፣ እንዴት ባለ ሁኔታ እኔን ይመለከተኛል? የተሰኙት ሁለት አበይትና አንገብጋቢ ጥያቄዎች መሠረት በማድረግ ቅዱስነታቸው ለእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሁለቱ ወንጌላውያን መልእክት በሥነ ትንተና በስነ መንፈሳዊነትና ቲዮሎጊያ እንዲሁም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርት ሥርና በጴጥሮሳዊ ተከታይነት ሥልጣን በመዳሰስ ሰው ልጅ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያደረገው ጉዞ መሪ ሃሳብ የሚሆነውን ለማስመር አቅደው የደረሱት መጽሓፍ መሆኑ ትላትና በጽሐፉ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ጉባኤ መገለጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የደረሱት መጽሐፍ የታተመበት የኢጣሊያ የሪዞሊና እንዲሁም የቫቲካን ማተሚያ ቤት ሠራተኞችን ትላትና ተቀብለው ማነጋጋረቸው የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አክለው፣ ይህ መጽሐፍ ጲላጦስ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ከየት ነህን” በማለት ከሚያቀርብለት “መሆናዊ ማንነቱና ተልእኮው” ከሚመለከት ጥያቄ በመንደርደር ማቴዎስና ሉቃስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ወይን የዘር ሐረግ አቀራረብ ላይ ያለው ልዩነት “ከእግዚአብሔር ቃል መግባት ታሪክ ጋር የተሳሰር የእርሱ ማንነት አዲስ ጅማሬ ያጠቃለለ የእግዚአብሔር ታሪክ ሠሪነት ቀጣይነቱ የሚያረጋግጥ ቲዮሎግያዊና ትእምርትም ሲሆን ይኽ ደግሞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አናሥር ባህርይ ነው” የሚል ትርጉም ያለው መሆኑ በመተንተን፦ ምንም’ኳ የዘረ ሐረግ ታሪክ አስፈላጊ ቢሆንም ቅሉ ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ፍጥረት ነው” የሚለው ቅውም ሃሳብም በጥልቀት ያስረዳሉ።
“ቅዱስ ዮሴፍ ሕጋዊ የኢየሱስ አባት ነው። በእርሱ አማካኝነት ሕግ እንደሚያዘውም፣ ከዳዊት ዘር ጋር የተሳሰረ ነው። ሆኖም ግን ከላይ ከእግዚአብሔር የመጣም ነው። ኢየሱስ ከይት ነው? የሚለው ጥያቄ ምሥጢር፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድርባዊ አናሥር በተጨባጭ ሁኔታ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዱ ከእግዚአብሔር ከአባቱ የሚልና ሁለተኛው ደግሞ ምንም’ኳ በመጨረሻ ትሁት ናዝራዊቷ ድንግል አማካኝነት አዲሱ ጅማሬ፣ የሰው ልጅ ሰብአዊነት በአዲስ አግባብ ጅማሬውን የሚገለጥ ቢሆንም ቅሉ የዓለም ታሪክ ዘንድ የሚገለጠው የሰው ልጅ የዘር ሐረግ ያለው አስፈላጊነት የሚገለጥ ነው።”
ሁለተኛው ረዥም ገጽ ያለው ርእሰ ጉዳይ እርሱም ለዘካርያስ የተበሰረው የዮሓንስ መጥመቅ መወለድ ቃልና ብሥራተ ገብርኤል ላይ ያተኮረ እነዚህን “ሁለት ብሥራቶች” በማዛመድ ሥልት የተነተኑበት ክፍል ሲሆን። ሁለቱ ብሥራቶች የጥንታውያን ትንቢቶች ፍጻሜ” ናቸው በማለት ብሥራተ ገብርኤል በማርያምና በዮሴፍ ላይ የቀሰቀሰው “አቀባበል-ምላሽ፦ መደናገጥ ትካዜ ጽናት” መሆኑና በተለይ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም፦ እግዚአብሔር ወደ ዓለም ዳግም በአዲስ ለመግባት ፈቃዱ የፈጠራት ‘መግቢያ’ ነች። እግዚአብሔር የማርያም በሮችን ያንኳኳል፣ የሰው ልጅ ነጻነት ያሻል፣ ቅዱስ በርናርዶስ ዘ ኪያራቫለ፦ ‘እግዚአብሔር በነጻነት የፈጠረውን ሰው ከነጻነት ከሚመነጨው ለፈቃዱ የእነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ ከሚለው፣ ካለ ነጻው መልስ ሊያድነው አይፈልግም። በሌላው አነጋገር እግዚአብሔር የሰው ልጅ ጥገኛ ሆነ ለማለት ይቻላል። የእርሱ ከሃሌ ኩሉነት ባንድ ሰው ልጅ ካለ ምንም ጫና ከሚሰውጥ ነጻው እሺ ከሚለው መልስ ጋር የተሳሰረ” መሆኑ በስፋት የማርያም እነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ የሚለው መልስ አማካኝነት እናት ለመሆን መብቃቷ ጋር በማዛመድ የሚያብራራ ነው።
ሦስተኛው ምዕራፍም “በአንድ ትክክለኛ የኵላዊ-ታሪክ ሂደት የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም መወለድ” ላይ በማነጣጠር፣ የንጉሥ አጉስቶ ሮማዊ ግዛት ወቅት የነበረውን ታሪካዊ ገጽታ ጭምር የተብራራበት ክፍል ነው። በዚህ ምዕራፍ ሥር ቅዱስ አባታችን የመዳን ታሪክ ያለው ኵላዊ ገጽታው ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባልታወቀ ጊዜ ባንድ ወቅት የተወለደ የአፈ ታሪክ ገጸ ባህርይ አለ መሆኑ በትክክልና በጥልቀት ሲያስረዱ፦ “እርሱ ካንድ የታሪክ ወቅት ጋር የተሳሰረ፣ ባንድ ወቅትና በአንድ ህብረተሰብ ‘አስተሳሰብና ተግባር’ ባህል ዘንድ የተወለደ መሆኑና ይዞት የመጣው የእግዚአብሔር የማዳን ፈቃድ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ በሙላት ለሰው ልጅ ‘ኵላዊ ገጽታውን’ በተግባር በማቅረብ አረጋግጦታል። በእርሱ ዘንድ ያ የፍጥረት ሁሉ ምክንያት የሆነው ቃል ወደ ዓለም ገባ” ብለዋል።
“የግብጹ ስደት፣ ቃል ወደ ተገባው ምድር መመለስ፣ መቼም ቢሆን ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተሰዶና ርቆ አይኖርም፣ ከአባቱ የሚለይ ሳይሆን ወደ ቤቱ የሚመለስ ወደዚሁ ቤት መመለስ የሚመራ፣ ወደ አብ ተጓዥ ከባይተዋርነት የሚያላቅቅ ወደ አገር የሚመራ” መሆኑ በጥልቀት የተነተኑበት መጽሐፍ መሆኑ ቸራዞ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.