2012-11-20 09:30:54

ር ሊ ጳ በነዲክት የፈረንሳ ብፁዓን ጳጳሳት አነጋግረዋል ፡


የፈረንሳ ብፁዓን ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ማለት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ መሆናቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
በዚሁ የቫቲካን መግለጫ መሠረት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ከትናትን ወድያ ቅድሜ ዕለት ረፋድ ላይ ብፁዓን ጳጳሳቱን በቫቲካን ክለመንቲና አዳራሽ ተቀብለው አነጋግረዋል።
ወቅቱ ክርስትያኖች ሁሉ ቤተ ሰብ እና ሕይወት የሚታደጉበት ወቅት መሆኑ የተያዝነው ዓመተ እምነት ለአዲሱ ትውልድ የክርስትና እሴቶች የምናስተላልፍበት ግዜ መሆኑ ቅድስነታቸው ለብፁዓን ጳጳሳቱ መግለጣቸው መግለጨው አክሎ አመልክተውዋል።
በነዲክት 16ኛ በማያያዝ ለብፁዓን የፈረንሳ ጳጳሳት እንደገለጡላቸው የቤተ ክርስትያን እና የመንግስት አቋሞች የተጠበቁ ሆነው ሕብረተ ሰቡ በተመለከተ ዓበይት ጉዳዮች ሲከሰቱ ቤተ ክርስትያን ድምጽዋ ማሰማት ይጠበቅባታል ።
የኢየሱስ ክርስቶስ መልእክተ ሰናየ እና ቤተ ክርስትያኑ በሕብረ ተሰብ ለሚከስቱ ጥያቄዎች ተጨባጭ ምላሽ የያዙ መሆናቸውም ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት መቀበል በተቸገረ እና ቤተ ክርስትያንን ወደ ጐን ትቶ የሚራመድ ሕብረተ ሰብ ለቤተ ክርስትያን ፈታኝ መሆኑ ያመለከቱት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ቤተ ክርስትያኒቱ ታማኝ የክርስቶስ ምስክሮች እንደሚያስፈልግዋት ማመልከታቸው ተገልጸዋል።
በአንድ ወንድ እና አንድ ሴት መካከል የሚታሰረው ቃል ኪዳን ለማዳከም የሚወጡ የሕግ እቅዶች ለመግታት ቤተ ክርስትያን ያላትን መብት በመጠቀም መከላከል እንደሚጠበቅባት ቅድስነታቸው ለብፁዓን የፈረንሳ ጳጳሳት መግለጣቸው ታውቆዋል።ምእመናን የሃይማኖት እምነት ሸክም ሳይሆን አርነት ሰጭ መሆኑ እና ይህንኑ ለመገንዘብ ማሕበራዊ ትምህርት ቤተ ክርስትያን በጥልቅ መገንዘብ እንዲሚያሻ ቅድስነታቸው መናገራቸው ተመልክተዋል።
በዓለም ዙርያ የሚገኙ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአምስት ዓመት አንድ ግዜ ቫቲካን እንደሚጐበኙ የሐዋርያት ጰጥሮሰ ጳውሎስ መቃብር እንደሚሳለሙ እንዲሁም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው አብያተ ክርትስያኖቻቸው ነክ ጉዳያች አንስተው ሐሳብ ለሐሳብ እንደሚለዋወጡ የሚታወስ ነው ።








All the contents on this site are copyrighted ©.