2012-11-20 09:20:39

መልአከእግዚአብሔር ጸሎት ር ሊ ጳጳሳት በነዲክት ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ ትናትና ረፋድ ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።
ቅድስነታቸው ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፋጻሜ በጽፈት ቤታቸው ሰገነት ብቅ በማለት ባሰሙት ንግግር በአሁኑ ግዜ ዓለመችን በጦርነት እና ተፈጥሮአዊ መቅሰፍት ታውካለች ክርስቶስ የማይለወጥ የሰው ማጣቀሻ እና የማይነቃነቅ የሕይወት ምንጭ ነው ብለዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚሁ መረጋጋት የማይታይበት ዓለም አረጋጊ እና ሰላም እና ምሕረት ሰጪ እንደሆነ ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ የዕለቱ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል ምርኩዝ አድርገው ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዳግመኛ ምጽአቱ ለሐዋርያቱ ያደረገውን ንግግር በመጥቀስ ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኃላ ወድያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች ጨረቃም ብርሃንዋን አታሳይም ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ ብለዋል ።
በነዲክት 16ኛ በማያያዝ የአሁን እና መጪውን ግዜ የሚያስተሳስር የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነው ብለዋል ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የወቅቱ እና መጪውን ግዜ ለሐዋርያቱ ሲናገር ለማስፈራራት ሳይሆም የዘለዓለመዊ ሕይወት ትክክለኛውን መንገድ ለማመልከት እንደሆነም ቅድስነታቸው አመልክተዋል።
ሁሉም ነገር ሐላፊ ሲሆን የእግዚአብሔር ቃል ግን ህያው እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት አስገንዝበዋል።
ቅድስነታቸው ስለ የጌታ መምጫ ግዜ ምልክት ወንጌላውያን ማርቆስ እና ሉቃስ ጠቅሰው ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ የበለስ ዛፍ ምስሌ ትምህርት ይሁናችሁ ቅርንጫፎችዋ ሲያቁጠቁጡና ቅጠሎችዋም ሲለመልሙ ያን ግዜ ያን ግዜ ጸደይ መቅረቡን ታውቅላችሁ ብለዋል። በመጨረሻም በቅዱስ በጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር ከመሰናበታቸው በፊት በአርጀንቲና ፐረጋሚኖ ላይ ሥርዓተ ብፅዕና የተፈጸመላቸውን ባለፈ ምእተ ዓመት አጋማሽ የኖሩ መነኲሲት ማሪያ ፐረጽ አስታውሰው ጠንካራ እምነታቸው አሞጉሰው ከምእምነናን ተሰናብተዋል።









All the contents on this site are copyrighted ©.