2012-11-20 09:49:00

. የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ አስከፊ መሆኑ ተገለጸ ፡



ከአንድ ሳምንት በፊት በእስራኤል መንግስት እና በፍልስጤሙ ሐማስ መካከል የተጀመረው የመጠቃቃት ድርጊት እንዳልተርጋጋ እና ሁኔታው እንደተወጠረ መሆኑ እና ግጭቱ ከተጀመረ ሐምሳ ፍሊስጤማውያን ሕይወታቸው እንዳጡ ተገለለጠ ።
የእስራኤል የአየር ኀይሎች ጋዛ ሰርጥን መደብደብ እንዳላቃረጡ ሐማስም ሮኬቶች ወደ እስራኤል መፈንጨፍ እንደቀጠለበት እና በሐማስ በተወረወሩ ሮኬቶች የቁሰሉ የእስራኤል ዜጎች መኖራቸውም ተዘግበዋል።
የእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በመሩበት ግዜ መንግስታቸው እግረኛ ጦር ለመዝመት እያሰላሰለ መሆኑ ማመልከታቸው ተዘግበዋል ።
የሊባኖስ ሂዝቦላህ ሚሊሽያ መሪ ናስራላህ እስራኤል እግረኛ ጦር በማዝመት ጋዛ ሰርጥን ከወረረች ዓቢይ እና አስከፊ ስህተት ትፈጽማለች ሲሉ መግለጣቸው ከበይሩት የደረሰ ዜና አመልክተዋል።
ዓረብ ሊግ የአረብ ሀገራት ማሕበር የፓለስጢና ራስ ገዝ ፕረሲዳንት አቡ ማዘን በጠየቁት መሠረት ከሁለት ቀናት በኃላ የልዑካን ቡድን ወደ ጋዛ ሰርጥ እንደሚልክ አስታውቀዋል ።
የግብጽ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት መሐመድ ሞርሲ ሐማስ እና እስራኤል ለማስታረቅ የምታካሄደው ጥረት የሚደነቅ እና ምለካም ተግባር መሆኑ የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፕረዝ ጠቁመው እስራኤል ሰላም ትሻለች ሲሉ መግለጣቸው ከኢየሩሳሌም የመጣ ዜና አስታውቀዋል።
በሌላ ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን የእስራኤል እና የፍሊስጤሙ ሐማስ ግጭት ለማርገብ በሚቻልበት ሁኔታ ከክልሉ ሀገራት መንግስታት መሪዎች ለመምከር ዛሬ ካይሮ ግብጽ ገበተዋል።ባን ኪሙን ሁለቱ ወገኖች ኀይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ እና ለሰላማዊ ድርድር እንዲቀርቡ በአጽንኦት ማሳሰባቸው ተዘግበዋል።
እስራኤል ራስዋ የመከላከል መብትዋ የተጠበቀ መሆኑ መግለጫ የሰጡት የዩኤስ አመሪካ መሪ ፕረኢሲዳንት ባራክ ኦባማ እስራኤል እግረኛ ጦር ከማዝመት እንድትቆጠብ መጠየቃቸው ተመልክተዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የጀርመን መንግስት መሪ ቻንስለር ኤንገላ መርክል የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት እንዳሳሰባቸው እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጒዶ ቨስተርወለ ወደ ተልአቪቭ መላካቸው እና ዛሬ ምሽት ከየእስራኤል አቻቸው ከአቪግዶር ሊበርማን ጋር ተገኛኝተው እንደሚወያዩ እና ነገ ከጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔታንያሁ እና ከፍሊስጤም ራስ ገዝ መሪ ከፕረሲዳንት ማህሙድ ዓባስ ጋር እንደሚገናኙ ከበርሊን የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።
የኔቶ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አውራ ጽሐፊ አንደርስ ራስሙሰን እስራኤል ራስዋ የመከላከል መብት የተጠበቀ ሆኖ የማጥቃት ተግባርዋ መጠን የጠበቀ መሆን እና ለስለስ ማለት ይጠበቅባታል ማለታቸው ከብሩሰል የደረሰ ዜና ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.