2012-11-19 14:41:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ጤንነት የገቢ ምንጭ ወይንም ለጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ የታቀበ ንብረት አይደለም


እ.ኤ.አ. ከህዳር 15 ቀን እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም. “አቢያተ ህክምና የአስፍሆተ ወንጌል የሰብአዊና የመንፈሳዊ ተልእኮ ሥፍራ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የአቢያተ ህክምናና የህክምና ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የጠራው 27ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአገረ ቫቲካን መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ RealAudioMP3 ይህ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የሥነ ህክምና ባለ ሙያዎችና ሊቃውንት፣ የሥነ ምርምር ሊቃውንት እንዲሁም በአቢያተ ህክምና ቆሞሶችና የቤተ ጸሎት ኃላፊዎች ካህናትና የበጎ ፈቃድ የግብረ ሠናይ ማኅበር አባላት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን አበይት አካላ ጭምር በማሳተፍ የተካሄደው ጉባኤ ስለ አቢያተ ሕክምና ተጨባጭ ሰብአዊ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ሁኔታ በመዳሰስ፣ በአቢያተ ህክምና የመተባበርና የፍቅር ሥራ ለማነቃቃት አልሞ አቢያተ ህክምና ለተልእኮ ወንጌል የተገባ ሥፍራ መሆኑ በተለያየ መልኩ ያበከረ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለተጋባእያኑ በዚህ የእምነት ዓመት የህክምና አገልግሎትና የሥነ ህክምና ባለ ሙያዎች ጸሎትና መንፈሳዊነት ላይ ያተኮረ በለገሱት ሥልጣናዊ አስተምህሮ መጠናቀቁ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውሳታ ስፐራንዛ አክለው፣ ቅዱስነታቸው “ጤንነት የገቢ ምንጭ ወይንም ለጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ የታቀበ ንብረት አይደለም” በሚል ቋሚ ሃሳብ ላይ የጸና ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፦ “በስነ ምርምር ግብረአዊ ሙያ የተጨበጠው እድገት የህመምተኛው አካላዊ ጤንነት ለማረጋገጥና ለጤንነት ዋስትና የመስጠቱ ብቃት ያለው ሆኖ ሲገኝ፣ ነገር ግን የሚሰቃየውን ሰው በሙላትና ልዩ መሆኑ ላይ ጸንቶ ሊሰጥ የሚገባው እንክብካቤ ተዳክሞ ይታያል። በኤኮኖሚ መቃወስ እጅግ በተጠቃው ዓለም በአሁኑ ወቅት ለጤና ጥበቃ የሚፈሰው መዋዕለ ንዋይ እንዲጎድል ተደርጎ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ለአደጋ ተጋልጦ የብዙ ሰው ልጅ የጤና ጥበቃ መብት ተጥሶ ጤና ጥበቃ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር መሆኑ እየተዘነጋ ነው። ጤንነት ኵላዊ ሃብት ነው። ስለዚህ የህክምና መስጫ አቢያተ ህክምናና የጤን አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ጤንነት የንግድ ዓለም ሕግ በመከተለ የገቢ ምንጭ አድርጎ ማቅረቡና ለጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ የታቀበ ጸጋ አድርጎ ከማቅረቡ አሠራር መቆጠብ ይኖርባቸዋል” በማለት፣ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ጨርሶ ለማግለል ወይንም ያለው ሙሉ ጥልቅ ምሥጢረ ትርጉሙ በቃል ብቻ የገለጠ ሳይሆን ስቃይን በገዛ እራሱ በመቀበል የገዛ እራሱ በማድረግ በመኖር እኛን የስቃይ ክርስትያናዊ ጥበብ መሆኑ ሲገልጥ፣ የስቃይ ተካፋይ መሆኑ መተባበር ገዛ እራሱ በሙላት የሚሰጥበት መሆኑ ገልጦልናል። ስለዚህ የህክምና ሙያና አቢያተ ህክምና የሚስጡት የጤና ጥበቃ አገልግሎት ግብረአዊ ሙያ ሳይሆን ተእልኮ ነው። የመልካሙ ሳምራዊው ተልእኮ እርሱም የሚሰዋው የፍቅር ሥራ የሚኖርበት የሚገለጥበት በእያንዳንዱ ታማሚው ገጽ የክርስቶስን ገጽ የሚለይበት የሚስተነተንበት ሥፍራ ነው” እንዳሉ ጋዜጠኛ ስፐራንዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ከምን ግዜም በበለጠ የአሁኑ ወቅት ኅብረተሰብ “ርህሩህ ቸር ልብ ያለው ሁሉን ለመቀበል የተዘረጉ እጆቾ ያሉት መልካም ሳምራዊው እንደሚያሻው የተረጋገጠ ነው። ይኽ ማለት ደግሞ የሰብአዊ ልክነት የሚወሰነው ከስቃይና ከሚሰቃየው ጋር በሚጸናው ግኑኝነት መሆኑ ያረጋግጥልናል” ካሉ በኋላ “የሚሰቃየውና ከሚስቃየው ጎን ያለው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እረሮ እንባ ስቃይ ብናኝ ሆኖ እንደሚቀር የተረጋገጠ ነው” በማለት ያቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ አጠናቀው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.