2012-11-19 14:57:58

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አማንያንና ኢአማንያን ለሕይወት እሴት መረጋገጥ በጋራ


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና ዙሪያ መልሶቻቸውንም ጭምር መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን RealAudioMP3 የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ያነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከህዳር 16 ቀን እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም. በፖርቱጋል በጉይማርስና በብራጋ “የህይወት ክቡር ዋጋ” ርእሰ ዙሪያ ዓውደ ጥናት ማካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፦ “ለህይወት ክብርነት ሁሉም ግንዛቤ ኑሮት፣ እያንዳንዱ በነጻ ለእንዳሻኝ ውሳኔ የሚጠቀምበት ሳይሆን፣ እንዲያቅበው የተሰጠው ጸጋ መሆኑ ታምኖ፣ ለሕይወት ታማኝ በመሆን አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ሁሉም አማኝም ኢአማኝም እንዲንከባከበው” አደራ እንዳሉ አስታውቀዋል።
በዚህ በአሁኑ ወቅት የሞት ባህል በተለያየ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑና እንዲህ ባለ መልኩም በሕይወት ባህል ላይ የሚሰነዘረው አደጋ አስታውሰው፦ “ሕይወት ዘለዓለማዊነት በውስጡ ያቀበ ከእግዚአብሒር ፍጽሙ ፍቅር የታደለ ጸጋ ነው። የዮሐንስ ወንጌል እንደሚያረጋግጥልንም ‘እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደ አንድ ልጁን ሰጠ። ስለዚህ በልጁ የሚያምን ሁሉ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኖረዋል እንጂ አይጠፋም፣ (ዮሐ. 3.16)፣ እግዚአብሔር ሕይወት ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሕይወት እስከ መስጠት አፍቅሮናል ይኽ ፍቅር አንድ ልጁን አሳልፎ በመስጠትም አረጋግጦልና፣ እግዚአብሔር አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እያንዳንዱን ሰው ያፈቅራል፣ ሆኖም ግን ወቅታዊው ሰው በገዛ እራሱ ኃይል በመታመን እይታው ከእግዚአብሔር አርቆ ተዘግቶ ሲኖር ይታያል። ይኽ አይነቱ ባህል ለማንኛውም ሰብአዊ መሠረታዊ ጥያቄ መፍትሔ አላስገኘም፣ ስለዚህ እግዚአብሔርን የኅልውናችን ማእከል ካላደረግን ከገዛ እራሳችን ጭምር ርቀን እንገኛለን፣ ገዛ እራሱን ለእግዚአብሔርና ለወንድሞች ክፍት የሚያደርግ፣ ከዓለምና ከሰዎች ይለያል ማለት ሳይሆን በበለጠ በቅንነትና በፍትህ በእውነትና በፍቅር ለሁሉም ቅርብ ይሆናል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.