2012-11-17 08:43:55

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (14.11.2012)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፡
ባለፈው ዕለተ ሮብ የሰው ልጅ በልቡ ሁሌ የእግዚአብሔር ፍላጎት እንዳለው ተመልከተናል፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ ይህንን አሳብ ከእናንተው ጋር አብረን ጠለቅ ባለ መንገድ ለማሰላሰል እወዳልሁ፣ ይህንን የምናደርገው ደግሞ እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚያስችሉን የተለያዩ መንገዶችን በማጥናት ይሆናል፣ ከሁሉ አስቀድሜ ግን እግዚአብሔር በልባችን የሚያኖረው የእርሱ ፍላጎት ጅማሬ ከማንኛውም የሰው ጅማሬ ይቀድማል፣ ወደ እርሱ በምንጓዝበት ጊዜም ይሁን መጀመርያ የሚያበራልን እርሱ ነው፣ ሁሌ ነጻነታችን እየጠበቀ ፊታችን ወደ እርሱ እንድናዞር ያደርገናል ይመራላንም፣ ራሱን እየገለጠልን ይህንን ግልጸት ለመቀበል ደግሞ ጸጋ በመስጠት ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ ተመክሮን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ ሓቅን ባገኘንባት ጊዜ የምንይዛት እኛ ሳይሆን ሓቅ ራስዋ ናት የምትፈልገንና የምትይዘን፣
ይሁንና የሰው ልጅ ልብን ለእግዚአብሔር እውቀት ክፍት የሚያደርጉ የተለያዩ መንገዶች አሉ፣ ወደ እርሱ የሚያደርሱ የተለያዩ ምልክቶች አሉ፣ እርግጥ ነው ብዙ ጊዜ እነኚህን መንገዶች ተከትለን ወይንም ምልክቶቹን አንብበን ለማወቅ እንዳንችል የዓለም አሸብራቂ ነገሮች ነጸብራቅ ሊያታልለን የሚቻልበት አደጋ አለ፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ከፍለጋችን አይቦዝንም ለፈጠረውና ላዳነው የሰው ልጅ ታማኝ ነው፣ ስለሚወደን ደግሞ ሁሌ እጉናችን ነው፣ ምንም እንኳ አንዳንድ አስተሳሰቦች ለቤተ ክርስትያንና ለክርስትያን ለሁሉም ፍጥረት አንድያ የዓለም አዳኝ ከሆነ ከኢየሱስ ጋር እንዲገኛኙ የደስታ ወንጌልን ለማዳረስ ጫና ቢያደርጉም እላይ የጠቀስነው እርግጠኝነት በየዕለቱ ሊሸኘን ያስፈልጋል፣ ከባድ ቢሆንም ተል እኮ አችን ይህ ነው፣ የቤተ ክርስትያን ተል እኮም ይህ ነው፣ እያንዳንዱ አማኝ ይህንን በደስታ እንዲኖረው ያስፈልጋል፣ ተል እኮው የገዛ ራሱ አድርጎ በእምነት እያዳበረው ለእግዚአብሔርና በጓደኛ ፍቅር በጎ አድራጎት እያገለገለ ተስፋን ማንጸባረቅ ይችላል፣ ይህ ተል እኮ ለሁላችን ጥሪ በሆነው በቅድስና ይንጸባረቃል፣
ባለነው ዘመን ሁላችን እንደምናውቀው እምነትን ብዙዎች የማይረዱት የሚቃወሙት እና እምቢ የሚሉት ሲሆን በእምነት ላይ ችግርና ፈተና አይቀሬ ነው፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለክርስትያኖቹ (1ኛ ጴጥ 3፡15) “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ” ይላቸው ነበር፣ ባለፉት ዘመናት እንደ ክርስትያን ማኅበር ሲታይ የነበረው የምዕራቡ ዓለም መቀሳቅሻው እምነት ነበር፣ ከሕዝቡ የላቀው ወገን በእግዚአብሔር መማጠንና ለርሱ መገዛት የዕለት ኑሮአቸው ክፍል ነበር፣ ይህ ኅብረተሰብ በእምነት እንጐድላለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፣ በዛሬው ዓለማችን ግን ሁኔታው ተቀያየረ፣ ሁሌ አማኙ ለማመኑ ምክንያት ለመስጠት የሚችል መሆን አለበት፣ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፊደስ ኤት ራስዮ እምነትና አመክንዮ በሚለው ሐዋርያዊ መልእክታቸው “ባለነው ዘመን እምነት ብዙ ፈተና እያጋጠማት ናት፣ ፈተናዎቹ ረቂቅ የሆኑ የተለያዩ መልኮች አላቸው ከሁሉ በላይ ደግሞ አልቦ እግዚአብሔር የሚል አስተሳሰብ እየገነነ ነው” ብለው ነበር፣ ኢሉሚኒዝም ከሚባለው የፍልስፍና አስተያየት ጀምሮ በሐይማኖቶች ላይ ትችት ሲጠናከር፣ በሰው ልጆች ታሪክም በእግዚብሔር የማያምኑ አረማዊያን እንዳሉ ቢገለፅም አረማዊያን እግዚአብሔር የሰው ልጅ ለነፍሱ የፈጠራ ውጤት ሕብረተሰቡ ያፈራው አጉል እምነት ነው ይላሉ። ባለፈት ክፍለ ዘመናትም የሰው ልጅ በራሱ እውቀት የፈጠራ ችሎታውን ቢያሳድግም ግን “ በእግዚብሔር ምስል መፈጠሩን “ የረሳና ድካሙን እንመለከታለን። አሁን እኛ በምንኖርበት ዘመን ደግሞ ከሁሉም የባሰና እምነታችንን የሚያሰጉ ሁኔታዎች ሲከሰቱ እነሱም በአንድ በኩል በእግዚብሔር ባያምኑም በሕይወታቸውም ባይመሰክሩበትም ሌሎችን የእምነት ተከታዮችንና= የእምነትን እውነት የሃይማኖት ክብረ በዓላትና ስርዓቶችን የማይቃወሙ ሲሆኑ በዕለታዊ ሕይወታችን ዋጋ ቢሶች እንደሆኑ ነው። አብዛኛውን ግዜ ከእግዚብሔር ጋር ያለውን ግንኙነታችንና እምነታችን የላላ ሲሆን የምንኖረው ኑሮም በሕይወታችን እሱ እንደሌለ ነው። በመጨረሻም የዚህ ሕይወት ውጤቱ አደናቅፎ ሲጥለን ምክንያቱም በግዴለሽነት በእምነታችንና ለእግዚብሔር ብለን የኖረው ሕይወት ባለመኖሩ ነው፣

በእውነቱ ከፈጣሪው የራቀ ሰው ዝቅ ሲል ይህም ማንነቱን አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ዝቅጠት እንዳደረሰው ያለፉት ክፍለ ዘመናት ውጤቶች አሁን ስንመለከታቸው ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ትርጉማቸውን ሲያጡ ነው። ይሕም የእግዚአብሔር መከታነት በመርሳት ከግብረገብ በመራቅ ወደ አጉል ነፃነት ስንራመድ ይሕም ሰዎችን ወደ ጣዖት እምነት እንደሚያደርሳቸው ነው፣

ኢየሱስ በበረሃ ውስጥ ያሳለፋቸው ፈተናዎች ከሕዝባዊ ተልዕኮ በፊት ስንመለከት የሰው ልጅ ከእኔነቱ መውጣት ካልቻለ ከጣዖቶቹ ጋር ያለውን ድክመትና እስራት ያሳየናል። በሕይወታችን እግዚአብሔርን ካላስቀደምን ሰው ትክክለኛውን መንገድን እንደማያገኝና ከፈጣሪውና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነትም እንደሚያጣ ነው። የጥንት አዋቂዎች ያሉት የተረት ምሳሌዎች አሁንም ትክክለኛ መሆናቸውን ሲገልፁልን ይሕም ሰው ራሱ የሕይወቱና የሞቱ ጌታ ሆኖ አምላክ የሆነ ይመስለዋል፣
በዚሁ ታናሹ እግዚአብሔር የመሆን ፍላጎት ፊት ቤተ ክርስትያን በክርስቶስ የተሰጣትን ተል እኮ አጥብቃ በመያዝ ስለሰው ልጅና ስለ ፍጻሜው እውነቱን ቍርጥ አድርጋ ከመንገር አታርፍም፣ ሁለተኛው የቫቲካን ፍሥሓና ተስፋ በሚለው ሰነዱ ቍ 19 ላይ “የሰው ልጅ ክቡር የሆነበት ምክንያት ከሁሉም በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ሱታፌ እንዲኖረው ስለተጠራ ነው፣ የሰው ልጅ ከመወለዱ ጀምሮ ወዲያውኑ ከእግዚአብሄር ጋር እንዲወያይ የተጠራ ነው፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ ህልውና የሚያገኘው እግዚአብሔር በፍቅር ስለፈጠረውና በህልውና እንዲቀጥል ስለሚጠብቀው ነው፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ይንን ፍቅር ካላቀውና በፈጣሪው ካላመነ በሙላት በእውነት የተመሠረተ ሕይወት ለመኖር አይችልም” ይላል፣
ታዲያ እምነታችን በእግዚአብሔር ለማያምኑና አረማዊያን የተጠራችበትን ጥሪ እንዴት አድርጋ ነው ማቅረብና መመለስ የምትችለው “በየዋሕነትና ትህትና” ነው። የዘመናችን ሰውም እግዚብሔር መኖሩን ለማረጋገጥና በተደጋጋሚም ዕቆቅልሽ ሆኖበት ለሚጠይቀው ጥያቄ መልሱ አቅጣጫው ወደ ፈጣሪው መንገድ የሚያገናኘው እንዲሆን እመኛለሁ። እዚህ ላይ አንዳንድ መንገዶችን ልገልፅላችሁ ስወድ እነሱም ከእምነት ጥንካሬና እንዲሁም በተፈጥሮ ማሰላሰል የሚገኙ መልሶች በ3 ቃላት አሳጥሬ ልገልፅላችሁ እፈልጋለሁ፣ እነሱም የመጀመሪያው የዓለም ፍጥረት ሁለተኛው የሰው ልጅ ሁሄታ ሶስተኛው እምነት ናቸው፣
የመጀመሪያው የምንኖርበት ዓለም ፍጥረት ነው፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ በሕይወቱ ለረጅም ግዜያት እውነትን ሲፈልግ እውነት እሯሷ እንዳጠመደችው በተወልን የታወቀው መጽሀፍ ጽሑፉ እናገኘዋለን። እንዲህም ይላል” የምድር ተፈጥሮ ውበቱን ፣ ባሕሩን ፣ ነፈሱ በየአቅጣጫው ሳይታይ የሚነፍሰው ፣ የሰማይ ውበቱን ወዘተ….. እነዚህ በተጨባጭ የምናያቸው ማን ፈጠራቸው ብሎ እራሱን ሲጠይቅ ፣ የሚሰጡትም መልስም፣ እንዴት እንደምናምር ተመልከተን ፣ ከማለቱ ባሻገር የተፈጥሮ ውበታቸውና አቀማመጣቸው ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑ ይመስላል። እነዚህ ፍጥረታት ያማሩና ውብም ሆነው ባይናገሩም ግን እነዚህን የፈጠረ ውበቱ እንደነሱ ያማረና የማይናገር ይሆን? (የቅዱስ አጎስጢኖስ ስብከት ቍ 241, 2)፣ ለዘመናችን ሰው የተፈጥሮን ውበትና አቀማመጡን እንደየችሎታው ቢያሰላስል ማሳሰቡ መልካም ነው። የምንኖርበት ዓለም በቅላጭ ድንጋይ እንደሚሉት የተፈጠረች ሳይሆን ግን በማስተዋል የምናይና የምንመለከት ከሆነ ድንቅ የሆኑ እንቅስቃሴዎችንዋን ማየት እንችላለን። ብዙ ስዕሎችዋን ስንመለከት ከበስተጀርባዋ የእውቀት ፈጣሪ እንዳለ እናያለን፣

አልበርት አኒስታይንም፡ የተፈጥሮን ሕጎች ስንመለከት ይላል አሳባችን ሊያስበው ከሚችለው ከእወቀት አድማስ ባሻገር ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሰው ልጅ ቦታ የማይሰጠውን አስተካክሎ የፈጠረ የበላይ ኅይል አለ ይላል፣ (ዓለምን የማይበት ዓይኔ 2005 ሮማ የተጻፈው) ይሕ የመጀመሪያ መንገድ እግዚአብሔር እንዳለ የሚገልፅልንና ተፈጥሮን በዓይናችን ዓይተን የምናሰላስልበት ነው፣
ሁለተኛው መንገድ የሰው ልጅ ፍጥረት፤ ቅዱስ አጎስጢኖስ አሁንም ሰው ከፈጣሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያብራራ እግዚአብሔር ለሰው ያለው ቅርበት ሰው ለራሱ ካለው ቅርበት ይበልጣል ሲል በታወቀው መጽሀፉ ንስሐ በተባለው ይገልጽልናል። እዚህ ላይ ነው ቅ. አጎስጢኖስ እንዲያሳስበን የሚፈልገው “ ከሕሊናህ አትራቅ ወደ ሕሊናህ ተመለስ ፡ በሰው ልጅ ሕሊና ውስጥ እውነት ትኖራለች “ ( ዴ ቬራ ሬሊጆኔ 39, 72 ) ይህ ነጥብ ነው በተለይ አሁን በምንኖርበት ቀውጢ ዓለም ውስጥ መርሳትና መዘንጋት የምንችለው። ማስተዋል ኖሮን አንዴ ቆመን ውስጣችንን ኅሊናችንን ብናዳምጣትና ብንፈልጋት በውስጣችን ያለውን ጥማት ከማርካት ባሻገር ሌላውንም ማርካት ትችላለች። ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስም ሲያስተምረን ሰብዓዊ ፍጡር ለእውነትና ለውበት ካለው ግልጽነት፤ ለበጐ ምግባር ካለው ስሜት፡ ከነጻነቱና ከሕሊናው ድምዕ በሚመነጭ ዘላለማዊነትና ደስታን ለመላበስ ካለው ጉጉት የተነሣ ሰው ራሱን ስለ እግዚአብሔር ህልውና ይጠይቃል፣
ሶስተኛው መንገድ እምነት ሲሆን፣ በተለይም አሁን በምንኖርበት ዓለም ወደ እውቀት በማድረስ እግዚብሔርን እንድናውቅና በእምነት እንድንኖር የሚያደርገን መንገድ ነው። የሚያምን ከእግዚአብሔር ጋር የተጣመረና በጸጋውና በቸርነቱ ይኖራል። ስለዚህ ምስክርነቱ ለሱ ብቻ ሳይሆን ከሙታን ተለይቶ ለተነሳው ክርስቶስ ነው። እምነቱም በሚኖረው እለታዊ ኑሮ መመስከር አያስፈራውም። ከማንኛውም ሰው ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ፈቃደኛ ከመሆኑ ባሻገር ግዋደኝነቱን ለሁሉም ከማበርከት ወደ ኋላ አይልም። ተስፋ ለቆረጡ ሁሉ ተስፋን ይሰጣል።
እምነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘንና በየዕለታዊ ኑራችን ዋጋ ለምንሰጠው ማንኛውንም አይነት እርምጃ ሕይወታችንና አስተሳሰባችንን ይቀይራል። ይሕ ከተጨባጭ ኑሮ የሚያርቅ ሕልም ወይንም የአዕምሮ መደበቂያና ስሜታዊ ሳይሆን እውነተኛና የሁሉንም ሕይወት የሚነካና የሚቀይር የወንጌሉ ብስራት ነው። የሰውን ልጅ ነፃ የሚያወጣ መልካም ዜና ነው፣
አንድ ክርስቲያን እንዲሁም አንድ ማኅበረ ክርስትያን የእግዚብሔርን ኅሳብ በተግባር ላይ ለማዋል የምንሠራ አማኞች መጀመሪያ ያፈቀረንን እግዚአብሔር መንገዱን እየሰሩ ሲሆን ይሕም እሱን ለማያውቁና በጥርጥር ለሚኖሩ ነው። ይሕ ደግሞ እያንዳንዱን አማኝ በሕይወቱ መመስከር እንዳለበት ሲጠይቅ ምስክርነቱም በእለታዊ ኑሮው ክርስቶስን በመምሰል ነው፣
ዛሬ ብዙ ሰዎች ስለክርስትያን እምነት የተወሰነ ግንዛቤ አላቸው፤ ምክንያቱም እንደ ማንኛው የእምነት አንቀጽ አድርገው ይመልከቱትና በታሪክ የተገለጠውን የእግዚአብሔር እውነትን ለማየት አይችሉም፣ ሆኖም ግን ክርስትና እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ጋራ ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለመወያየት በታሪክ ራሱን ገልጦ ከእርሱ ጋር የፍቅር ግኑኝነት እንዲፈጥር አደረገው፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ከማንኛውም አንቀጸ ሃይማኖትና እሴት በላይ የሰው ልጅና እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የሚገናኙበት ፍጻሜ ነው፣ ተየክርስትና እምነት የግብረ ገብነት ወይንም የሞራል መመሪያ ከመሆኑ በፊት የፍቅር ጉዞ ፍጻሜ ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በግል የመቀበል ሁኔታ ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስትያንና የክርስትያን ማኅበር ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰውን እውነተኛ መንገድ የሆነውን ክርስቶስን መመለክትና እሱን ማሳየት አለበባቸው፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.