2012-11-16 13:14:55

የመካከለኛው ምሥራቅ ካቶሊክ ወጣቶች ጉባኤ


በመላ መካከለኛው ምሥራቅ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተወጣጡ በጠቅላላ 1500 ወጣቶችን ያሳተፈ የመካከለኛው ምስራቅ ካቶሊክ ወጣቶች የሦስት ቀናት ጉባኤ ትላትና አቡ ዱባይ በሚገኘው በቅዱስ ዮሴፍ ካቴድራል መከፈቱ ሲገለጥ፣ ይኽ በጸሎትና በአስተንትኖ የሚሸኘው የሦስት ቀናት ጉባኤ በማስመልከት የሰሜንና ደቡብ አረቢያ ሐዋርያዊ መሥተዳድር ብፁዕ አቡነ ፓውል ሂንደር ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሉቺያ RealAudioMP3 ፊዮረ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፦ ይህ የመካከለኛው ምሥራቅ የካቶሊክ ወጣቶች ጉባኤ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያወጁትና የተገባው የእምነት ዓመት መሠረት ያደረገ መሆኑ ጠቅሰው፣ አክለውም በሳቸው ሐዋርያዊ መሥተዳድር ሥር የሚገኘው ሰበካ የእምነት ዓመት በሁሉም ቁምስናዎች በይፋ ከተጀመረ ወዲህ እቅዱ ቀጣይነት ባለው መንገድ በተለያዩ መንፍሳዊ ባህላዊ መርሃ ግብሮች አማካኝነት እየተኖረ ነው ብለዋል።
የክልሉ ካቶሊካውያን ምእመናን እምነታቸውን አቅበው ለመኖር እንዲችሉ የሚያከናውኑት ተግባር የሚደነቅ ነው። በመካከለኛው ምሥራቅ ይዘት እምነት መኖር ማለት ክርስትና እምነት መኖር ከበድ የሚል ቢሆንም ቅሉ፣ ምእመናኑ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን መርሃ ግብር በመከተል የአካባቢው ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ግምት የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ ብዙኃኑ ክርስትያን ምእመን የውጭ አገር ዜጋ በመሆኑም ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ናቸው። ሆኖም ይኽ ያለባቸው ልዩነት ለክርስቶስና ለቤተ ክርስትያን ያላቸው ፍቅር አማካኝነት አንድ በመሆን የሚጋረጥባቸው ፈተና ለመቅረፍ በመደጋገፍ ቤተ ክርስትያናዊና ክርስቶሳዊ ፍቅራቸውን በመኖር ሃይማኖታዊ መለያቸው ጎላ በማድረግ እየመሰከሩ ናቸው ብለዋል።
በዚያ ክልል የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን የውጭ አገር ዜጋ ማለትም በኤመሬት አረብ አገሮች የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን ከውጭ አገር የተሰባሰበ ስደተኛ በመሆኑ በዚያ አገር የመቆየትም ሆኖ እዛው የመኖር ውሳኔ ያለው አይደለም፣ በዚህ አገር እየኖረ እየኖርበት ካለው አገር ለቆ የሚወጣበት ቀን ከወዲሁ እያሰላሰለ ነው የሚኖረው። ስለዚህ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ይኸንን ሁሉ ያመዛዘነ አገልግሎት ነው የምታቀርበው። በዚህ ክልል ያለው የእምነት ገጠመኝ በተለይ ደግሞ ከዚህ አኳያ ሲታይ እምነት የነጋድያን አቋም ወይንም የነጋዲነት ተጨባጭ ሁኔታ የሚከተል ነው። በዚያ ክልል በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚያገለግሉት ካህናት በጠቅላላ መንፈሳውያን እረኞች የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን እምነቱን ከዚያ ካለው የተሸጋጋሪነት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አዛምዶ በሙላት ለመኖር እንዲችል በተለያየ ሐዋርይዊ ግብረ ኖልዎ ዘርፍ አማካኝነት ጸንተው እያገለገሉ ናቸው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የአረብ አገሮች ጸደይ ተብሎ የሚንገረለት የአረብ አገሮች ኅዳሴና ለውጥ እያረጋገጠው ያለው የህዝብ ጥያቄና ንቅናቄ ያቀጣጠለው አዲስ ሁነት በተባበሩት ኤመሪት አረብ አገሮች በኦማንም በየመን ጭምር አዲስ ራእይ እያጋባ ነው። ኤመሪት አረብ አገሮች ይኽ በአረብ አገሮች የተከሰተው ጸደይ በታዛቢነት የሚመለከቱት ሁነት ነው። ሰለዚህ ይኽንን ተጨባጭ ሁኔታ በቀጥታ በባለቤትነት ከኖሩት እና በመኖር ከሚገኙት አገሮች የሚሰደዱት እነርሱም ከሶሪያ ከግብጽ ከኢራቅ ከሊባኖስ የሚሰደዱት የአረብ አገሮች ጸደይ የቀሰቀሰው ኅዳሴና ለውጥ የግል ገጠመኝ አድርጎ ነው የሚኖረው። ከፊልፒንስ ከሕንድና ከላቲን አመሪካ አገሮች የሚመጡት ስደተኞች የሚኖሩት ገጠመኝ አይሆንም፣ ሆኖም ግን በአንድ እምነት ጥላ ሥር የሚሰባሰቡ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመን በመሆናቸው ሁሉም ከተለያየ አገር የተወጣጣ ቢሆንም ቅሉ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ምእመን በመሆኑ፣ የእያንዳንዱ ገጠመኝ በጋራ ተካፍሎ የሚኖረው ተጨባጭ ሁኔታ ይሆናል። በክልሉ ለዚህ ክርስትያን ምእመን የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎዎ የእያንዳንዱ ክርስትያን ምእመን ተጨባጭ ሁኔታ አቢይ ግምት የሚሰጥ ነው በማለት የሰጡንት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.