2012-11-16 16:27:17

ዓመተ እምነት እና የክርስትያን አንድነት ጉዞ



የክርስትያን አንድነት ጉዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውነተኛ ቀውስ መደቀኑ አይቶ እንዳላየ መሆን አይቻልም እና ክርስትያኖች ሁሉ ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ በጋራ መመስከር መቻል ይጠበቅባቸዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በክርስትያን አንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት አጠቃላይ ጉባኤ ለተሳተፉ ያሰሙት ቃል ነው።
በማያያዝ ባለፈው ወርሀ ጥቅምት ይፋ የሆነውን ዓመተ እምነት ለኤኩመኒዝም ለክርስትያን አንድነት አስተዋጽኦ ያደርግ ዘንዳም ቅድስነታቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ንግግራቸው በማያያዝ ከሁሉም በፊት የቅዱስ ወንጌል ዜና ሰናየ በተቀበሉ እና የክርስትና ሕይወት ለዘመናት አብቦ በነበረበት የዓለማችን ክልል በአሁኑ ወቅት የእምነት ቀውስ እና መንፈሳዊ ድህነት በጉልህ እንደሚታይ አስምረውበታል።
መንፈሳዊ ድህነት ሕይወታቸው ከእግዚአብሔር የሚያርቅ ስለሆነ ይህን ለመጠገን የክርስትያኖች ሁሉ ሐላፍነት እንደሆነም በነዲክት 16ኛ በተጨማሪ አስገንዝበዋል።
በመድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለምናምን ሁሉ የኅያው እግዚአብሔር ህልውና ዳግም መስበክ እና መንገር ይጠበቅብናል ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ።
የክርስትያኖች መለያየት የኢየሱስ ክርስቶስ ፍላጎት የሚጻረር ከመሆኑ ባሻገር ቅሌት እና የሚያሳዝን እንደሆነ አመልክተዋል ።እምነተ እግዚአብሔር ለሁሉም ክርስትያን የሚስተባብር እንደሆነ እና በሚቀጥለው ቅርብ ግዜ እውን ባይሆንም ለአንድነት ክርስትያን የተጀመረው ሂደት ቀጥሎ እልባት እንድያገኝ ተስፋ እንዳላቸው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት አክለው ገልጠዋል።የክርስትያኖች አንድነት ሰብአዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነም ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።
ለክርስትያኖች አንድነት መጸለይ ማስተንተን እንዲሁም መንፈሳውነት እንደሚያስፈልግም በነዲክት 16ኛ አውስተዋል።በተለያዩ አብያተ ክርስትያኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለመቅረፍ በእግዚአብሔር እምነት መጣል እና ትዕግስት እንደሚጠይቁ ቅድስነታቸው ተናግረዋል።
በየኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት የታየው ጠንካራ አንድነት የእግዚአብሔር ምግባር የሚያንጸባርቅ እንደሆነ ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት አስገንዝበዋል።አዲስ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል እና ኤኩመኒዝም ውስጣዊ ለውጥ እና በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ቆርጦ መነሳት እና መጓዝ ይሻሉ ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ና ።









All the contents on this site are copyrighted ©.