2012-11-14 13:55:55

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ


ዝክረ 50ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በአርቆ አሳቢነት ተጠናቅሮ እንዲቀርብ ቀድሞ ያቀረበው ማሳስቢያ ተከትሎ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይፋ ሆኖ ለንበብ የበቃበው ዝክረ 20ኛው ዓመት እየታሰበ ያለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ በማስደገፍ RealAudioMP3 የቫቲካን ረዲዮ ለዝክረ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ጉባኤ ምክንያት በተከታታይ የጉባኤው ሰነዶች ታሪካዊ ቲዮሎጊያዊ አንቀጸ እምነታዊ ባህርዩ ላይ ያተኮረ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ ቤተ ክርስትያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ ተመርቶ እንዳ ቀረበው የስርጭት መርሃ ግብር፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የጀመሩት አስተምህሮ በመቀጠል ትላትና፦ “የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ‘እግዚአብሔርን ማወቅ’፣ የእያንዳንዱ ክርስትያን ሕይወት መሠረታዊ ጥያቄ ማእከል ያደረገ ነው” በሚለው ጥልቅ ሃሳብ ላይ በማተኮር ሁለተኛው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር ያቀረቡ ሲሆን፣ “እግዚአብሔርን በገዛ እራሳችን ብቃትና ሃይል ለይተን ለማወቅ እንችላለን? የዚህ ጥያቄ መልስ አዎ ወይንም አይ የሚል ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም ማወቅ በተባለው ቃል ላይ በለን ግንዛቤ ይወሰናልና” እግዚአብሔር በሰው ልጅ የአስተሳሰብ ሥልት የሚዘጋ ባለ መሆኑ ህልወተ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ተጨባጭ መረጃ የሚወሰን አይደለም። የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 31 ‘እግዚአብሔር የምናውቅባቸው መንገዶች በሚል ንኡስ ርእስ ሥር እንደተመለከተውም የህልወተ እግዚአብሔር ተጨባጭ ማረጋገጫዎች ይኽም በሚጣጣሙና በአሳማኝ ክርክር ላይ ተመስርቶ ስለ እውነታው እርግጠኛ እንዲሆን የሚያስችል በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው እርሱን ለማወቅ ለመውደድ የተጠራ እግዚአብሔር የሚሻ እርሱን የሚያውቅባቸው በተፈጥሮ ሳይንሶች እንደሚታወቀው ዓይነት ሳይሆን እንዳንድ መንገዶችን ያገኛል” በሚል ሃሳብ ያስቀመጠው አገላለጥ ጠቅሰው፣ ስለዚህ ለኅልወተ እግዚአብሔር መግለጫ፣ ተጨባጭ መረጃ ማቅረብ ወይን መሻት ሳይሆን እግዚአብሔርን ማወቅ ነው፣ እንዲህ በመሆኑም የሚያስፈልገው ኅልወተ ማረጋገጥ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። የትምህተ ክርስቶስ መዝገብ መጽሓፈ ጥበብ ዋቢ በማድረግ ምዕ. 13 ከ 1-9 ያለውን ቃለ እግዚአብሔር መሠረት፦ “እግዚአብሔርን የማወቅ ጉድለት በልቡናቸው ያለባቸው ሰዎች ሁሉ በእውነት ከንቱ ናቸው፣ በሚታዩ መልካም ነገሮች ያለውን ያውቁ ዘንድ ተሳናቸ ሥራውንም እያዩ ሠሪውን አላወቁትም…ውበት የፈጠረ እርሱ ይህን ፍጥረት ፈጥሯልና የእነዚህ ጌታ ፈጽሞ እንደሚበልጥ ይወቁ” በማለት ይገልጥልናል። አንደኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ቤተ ክርስትያን እንደምታምነውና እንደምታስተምረውም እግዚአብሔር…ሰብአዊ ፍጡር በብርሃነ አእምሮ ባህርይ አማካኝነት ከፍጥረት ሁሉ በመንደርደር እግዚአብሔርን ለማወቅ ይችላል።” የቅዱስ ኢግንጽዮስ ዘ ለዮላ መንፈሳውያን ሱባኤዎች ቁ. 235 ላይ “ኅልወተ እግዚአብሔር በፍጠረት ሁሉ ምኅዳር ያለው በተለያየ መልኩ እንደሚገለጥ” ያረጋግጥልናል፣ ይኽ ደግሞ መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 18 (19) ቁ. 1 ዘንድ፦ “ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ፣ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራሉ።” የሚለው ቃለ እግዚአብሔር የሚያጎላ መሆኑ በማረጋገጥ የሰጡትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.