2012-11-14 14:00:17

እንግልጣር፦ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ


የእንግልጣርና የወይልስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. እስከ ነገ ሓሙስ ህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚዘልቀው የሰው ልጅ ለብዝበዛ ታልሞ ከቦታ ቦታ የማንቀሳቀሱ ክብር ሰራዥ ተግባር ማእከል ያደረገ ከትላትና በስትያ ጉባኤው በሊድስ መጀመሩ RealAudioMP3 ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በዚህ በመካሄድ ላይ ያለው ጉባኤ በሎንደ ከተማ የፖሊስ ጽ/ቤት ሰው ልጅ ለተለያዩ ጸያፍና ክብር ሰራዥ ተግባር የመገልገያ መሣሪያ ለማድረግ ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ወንጀልና ወንጀለኞችን የሚከታተለው ቢሮ ኃላፊ ከቪን ሃይላንድ ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ከዚህ ቀደም በዚህ ጸያፍ ተግባር የተጠቁት ነጻ ለወጡትን ዜጎች የተሟላ ሕንጸት በሚሰጥ የሰው ልጅ ከዚህ ጸያፍ ተግባር ለማላቀቅ የሚታገለው ሶፊ ሃየስ የግብረ ሠናይ ማኅበር ውስጥ በመደገፍ ላይ ከሚገኙት ምስክርነት እንደሚሰጡ ያመለክታል።
ይኽ እጅግ በዓለማችን በመስፋፋት ላይ ያለው ክብር ሰራዥ ጸያፍ ተግባር ጨርሶ ለማጥፋት ሁሉም መንግሥታት ይኸንን ተግባር ለመቆጣጠር የሚያግዝ ለዚህ ጉዳይ በትክክል ያተኮረ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እንዲኖራቸውና በሁሉም መስክ ይኸንን ጸያፍ ተግባር እንዲዋጉ ጥሪ የሚያቀርብ መሆኑና በመጨረሻም ጉባኤ የ2013 ዓ.ም. ዓመታዊ የወጪ እቅድ እንደሚያጸድቅም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.