2012-11-12 14:36:15

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ የአሕዛብ ቅጥር ግቢ ከሉተራን አቢያተ ክርስትያን ጋር ለመወያየት


እ.ኤ.አ. ህዳር 09 ቀን 2012 ዓ.ም. ሮማ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤትና ሮማ የሚገኘው የኖርወይ የባህል ተቋም በመተባበር፦ “የክርስትና እምነት አዋሳኝ፣ በኖርወይና በቅድስት መንበር መካከል የጋራ ቅርስ መሻት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ ሥነ ጥንታዊ ሥነ ንድፍ ሰሜናዊ ሥነ ሙዚቃ ሥነ መንፍሳዊ ንግደት በተሰኙት ዘርፎች አማካኝነት የሁለቱ አገሮች የጋራው እርሱም የሚያገናኛቸው RealAudioMP3 የክርስትናው ታሪካዊ ቅርስ ለመለየት በተካሄደው ዓውደ ጥናት የቫቲካን ግላዊ ዝግ ቤተ መዝግበ ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ፓጋኖ በቅድስት መንበር የኖርወይ ልኡከ መንግሥት ሮልፍ ትሮለ አንደርሰንና የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ አስተምህሮ ማቅረባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ያነቃቃው መርሃ ግብር በተለያዩ አገሮች ማካሄዱ አስታውሰው፣ ቀጣዩ መርሃ ግብር በኦስሎ ለማካሄድ ሃሳብ እንዳለ ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ በኖርወይ ከብዙሃኑ የሉተራን ሃይማኖት ተከታይ ጋር ለመወያየትና እንዲሁም በአገሪቱ በጥልቀት የተስፋፋው ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ሃይማኖት በግል በማለት ማኅበራዊ ግጽታውን የሚክድ ባህል ግምት በመስጠት የቀረበ ሃሳብ መሆኑ አብራርተዋል።
የኖርወይ የሥነ ድርሰት የሥነ ጽሑፍ በጠቅላላ ሥነ ባህል መግለጫ የሆኑት ሃብቶች እምነትን ግድ ማለትና አለማለት የሚንጸባረቅባቸው ከመሆኑም ባሻገር፣ በሰው ልጅ ኅላዌ በኑባሬ ያለው እግዚአብሔርን የመሻቱ ባህርይ ማንም ሊክደው አይችልም፣ ይኽ ደግሞ የኖርወይ ባህል የሚያንጸባርቀው ሃሳብ ነው። በኖርወይ ያሉት አቢያተ ክርስትያን ጭምር ያንን ሰብአዊ ዝምባሌ መስካሪዎች ናቸው ካሉ በኋላ፣ ኖርወይ የኖቤል አገር ነች፣ ይኽ ደግሞ ኩላዊነት ቅርጽ የሚያሰጣት ባህል መሆኑ አብራርተው፣ በኖርወይ ተዘማጅና ሃይማኖትና ግብረ ገብ ግድ የማይል ባህል የተስፋፋ ቢሆንም ቅሉ ያለው ግድ አለማለቱ መንፈሳዊው ዝምባሌ ምስክር ነው። ይኽ ደግሞ የአገሪቱ ጥንታዊው ክርስትያናዊ ባህል የሚያጎላ ሲሆን፣ ይኽንን በጥልቀት ለማስተጋባት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ቀጣዩ “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በኦስሎ ለማካሄድ እቅድ አለው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.