2012-11-12 14:31:26

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ መንፈሳዊ መዝሙር (ዜማ) እምነትን ኅያው የሚያደርግ የእግዚአብሔር ፍጹም ውበት መግለጫ ነው።


እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ስድስት ሺ የሚገመቱት የቅድስት ቸቺሊያ የቅዱስ ማኅሌት መዘምራንና ሙዚቀኞች ማኅበር አባላትን በአገረ ቫቲካን ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው፦ “በሊጡርጊያ የሚቀርበው መንፈሳዊ መዝሙር ወይንም ዝማሬ RealAudioMP3 የሥነ ወበት ማሰረጃ ሳይሆን የእምነት መግለጫ ነው፣ ከዚህ አኳያ ሲታይ በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ያለው አስተዋጽዖ ለመገመቱ አያዳግትም” በሚል ቅዉም ሃሳብ የሚጠቃለል ሥልጣናዊ አስተምህሮ መለገሳቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ በመግለጥ፣ ይህ የቅድስት ቸቺሊያ የመንፈሳዊ መዝሙር ማኅበር ምሥረታ አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን፣ ዝማሬ (ቅዱስ ማኅሌት) በእያንዳንዱ በሚሰቃየው ነፍስ የሚገባ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ዝማሬ የሚለው ቃል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአራተኛውና በአምስተኛው ክፍለ ዘመን መካከል የኖረው አቢይ የቤተ ክርስትያን አባት ቅዱስ አጎስጢኖስ ዘሂፖ መዝሙረ ዳዊት ሲያዜም ምንኛ ልቡ ተማርኮ ዓይኖቹ በእንባ መሞላቱ የገለጠው መንፈሳዊ መዝሙር ያለው ጥልቅ ማራኪነት የሚያጎላ ነው። እ.ኤ.አ በ1900 ዓመታት አጋማሽ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ፈረንሳዊው የሥነ ሙዚቃና የሥነ ትያትር ሊቅ የሙዚቃ ደራሲና ገጣሚ ፓውሎ ክላውደል በፈረንሳይ የኖትረ ዳም ካቴድራል ውስጥ ለበዓለ ልደት ቀዳሜ ጸሎት ሠርክ በመከታተል በግረጎሪያን የሚዚቃ ቅኝት ተሸኝቶ የቀረበው የማርያም የምስጋና ጸሎት በማዳመጥ ካለ ምንም ማመንታት ወዲያውኑ የክርስትያን እምነት ተቀብለው መለወጣቸው ቅዱስ አባታችን በማስታወስ መንፈሳዊ መዝሙር ቅዱስ መንፈሳዊ ኃይል ሲያርባሩ፥ “እምነት የእግዚአብሔር ቃል ከማዳመጥ የሚወለድ ነው፣ ሆኖም ግን ይኽ ማዳመጥ በየስሜት ኅዋሳት እማካኝነት ብቻ ሳይሆን ቀልባዊና ልባዊ ማዳመጥ የሚያጠቃልል ነው። ከዚህ አኳያ ሲታይ መዝሙረ ዳዊትና የቅዱስ መጽሓፍ መዝሙሮች ያለው ተገናኝና አገናኝ ባህርይ ጥልቅ ነው” ብለዋል።
የቅዱስ አጎስጢኖስ ጥንታዊው አገላለጥ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሥርዓተ አምልኮ እርሱም በሊጡርጊያ በቃለ ውኅደት የሚቀርበው ዝማሬ (ዜማ) በተመለከተ የሰጠው ውሳኔ ቀድሞ የሚያጎላ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲገልጡ፦ የቅዳሴ ዜማ ወይንም ዝማሬ ለሥነ ውበት መግለጫ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ላለን እምነት የሚያበረታና የሚገልጥ ለእግዚአብሔር ክብርና ለምእመናን ቅድስና የሚቀርብ ጸሎት ነው። የመንፈሳዊ መዝሙር ዓላማም ይኽ ነው። ስለዚህ መንፍሳዊ መዝሙር (ዝማሬ) በሊጡርጊያ የሚታከል ሳይሆን ለገዛእ ራሱ ሊጡርጊያ ነው ቀጥለውም ክላውደልን በማስታወስ፦ የማርያም የምስጋና ጸሎት ምንኛ ጥልቅና ማራኪ ብቻ ሳይሆን በእውነቱ ወደ እምነት የሚመራ ልብንና መንፈስን በጥልቀት የሚነካ ነው። እንደ ካላውደል ተማርከው ስንቶቹ በመንፈሳዊ ዜማ የመለወጥ ጸጋ ለመታደል በቅተዋል፣ እናንተ የመንፍሳዊ መዝሙር ዘማርያንና ሙዚቀኞች ያለባችው ኃላፊነት አቢይ ነው።” ካሉ በኋላ ለሁሉም የቅድስት ቸቺሊያ የሙዚቀኞችና የመዘምራን ማኅበር አባላት በቅድስት ቤተ ክርስትያን የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ምንኛ አቢይ መሆኑ ጠቅሰው ሁሉንም በአገልግሎታቸው እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ተማጥነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.