2012-11-09 15:01:01

የመርከበኞች የባህር ተጓዦችና በባህር በሮችና በባህር ሃብት ለተዳዳሪ ክልሎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንክብካቤ


ትላትና ጧት በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክልፍ ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ከሕዳር 19 ቀን እስከ ሕዳር 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ለመርከበኞች ለባህር ተጓዦች በባህር ሃብት ለተዳዳሪ ክልሎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው እንክብካቤ ላይ ያተክረ “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለባህር ተጓዦች ለመርከበኞች በባህር ሃብት ለተዳዳሪ ዜጎች” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ እንደሚካሄድ የስድተኞችና RealAudioMP3 የተጓዦች (መንገደኞች) ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮና ምክትላቸው ክቡር አባ ጋብሪኤለ ፈርዲናንዶ በንቲቮሊዮ በጋራ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።
በባህር ሃብት ለሚተዳደሩት ለመርከበኞች ለባህር ተጓዦች በቤተ ክርስትያን የገዛ እራሱ የቻለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እ.ኤ.አ. ከ 1800 አጋማሽ ከኤውሮጳ ወደ ሁለቱ አመሪካዎች ይሰደዱ ለነበሩት የኤውሮጳ ዜጎች መንፈሳዊ እንክብካቤ ለመስጠት በሚል እቅድ መሠረት አንድ በማለት በቅድስት ቤተ ክርስትያን የተጀመረ አገልግሎት መሆኑ ሲገለጥ፣ በአሁኑ ወቅት 110 ቅድስተ ማርያም የባህር ኮከብ በሚል መጠሪያ ለነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ያቀና ሐዋርያዊ እንክብካቤ መስጫ ማእከሎች እንዳሉና በዚህ አገልግሎት በብዙ መቶዎች የሚገመቱ ካህናት ገዳማውያን ዲያቆናት እና ዓለማውያን ምእመናን ተሰማርተው እያገለገሉ መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው አያይዘውም፦ “በባህር ሃብት ተዳዳሪው ሕዝብ ብዛት አንድ ሚሊዮንና ሁለት መቶ ሺህ መሆኑና፣ በዓለም የመጓጓዣ አገልግሎት የሚፈጸመው የንግድ ምርት አቅርቦት 90 በመቶ በመርከቦች አማካኝነ የሚከናወን መሆኑና በዓሳ ሃብት ልማት ተዳዳሪው ሕዝብ ብዛት 36 ሚሊዮን ሲሆን፣ የነዚህ በባህር ሃብት ተዳዳሪ ሠረተኞች ቤተሰቦቻቸው ጭምር የሚኖሩት የተነጠለ ሕይወት፣ በባህር ጉዞ የሚፈጀው ረዥም ሳምታት ወሮችም ጭምር የሚፈጅ በመሆኑም ባህረኛው ከሌላው ከየብስ ነዋሪው ሕዝብ ርቆ ለብቻው መኖር በሚያስከትልበት የብቸኝነት መንፈስ ለተለያየ አደጋ ሊጋለጥ የሚችል በመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ይኸንን ሁሉ ግምት በመስጠት ለዚህ የኅብረተሰብ ክፍል የተገባ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት በማቅረብ፣ ይኸንን የምትሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት በቤተ ክርስትን እቅዶች ሥር ወቅታዊ በማድረጉ ረገድ ነቅታም ትገኛለች” እንዳሉ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።
“በባህር ሃብት ተዳዳሪ ሠራተኞች የሚያጋጥማቸው ችግር የባህር ብከላ፣ የሚይፈጽሙት ረዥም የሥራ ሰዓት በዚህ ሙያ መሠማራት ከሚያስከትለው ዘርፈ ብዙ አደጋ ሁሉ ለመከላከል የባህር ሃብት ተዳዳሪ ዜጎች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በሚል ውሳኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ 2007 ዓ.ም. የተደነገገው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ እንዲሆን አገሮች በተናጥል በሕዝብ ተወካዮቻቸው ምክር ቤት በኩል የተቀብለነዋል ውሳኔ ያቀርቡበት ዘንድ እየተጠበቀ ነው። 8 የባህር በር ያላቸው አገሮች ያጠቃለለ በጠቅላላ 10 አገሮች ገና ፊርማቸው እንዳላኖሩበት” ከገለጡ በኋላ “የእነዚህ አገሮች ፊሪማ እየተጠበቀ ነው” ማለታቸውንም ጋዜጠኛ ጂሶቲ ሲያመለክቱ፣ ምክትላቸው ክብሩ አባ በንቲቮሊዮ፦ “የባህር ሽፍቶች የሚፈጽሙት እገታ ከፍ እያለ መሆኑና፣ ይኸንን ሁሉ ችግር ግምት በመስጠት የባህር ተጓዦች ሕይወት ዋስትና የማሰጠቱ ኃላፊነት የሁሉም ምንግሥታት ነው” እንዳሉ ጂሶቲ አስታውቀዋል።
በዚህ የእምነተ ዓመትና እንዲሁም በቅርቡ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ መሠረት ያደረገ ለባህረኞች ለባህር ተጓዦች በባህር ሃብት ለሚተዳደሩት ዜጎች የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የባህር ተዳዳሪዎች ዕለታዊ ሕይወት ግምት የሰጠ አዲስ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለእምነት ዓመትና ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል በማተኮር የሚወጠንበትና እንዲህ ባለ መልኩ በዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለሚያገለግሉት ካህናት ገዳማውያን ዲያቆናትና ዓለማውያን ምእመናን ለመደገፍ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ቨሊዮ በሰጡት ማብራሪያ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠንቀቁ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.