2012-11-09 15:07:01

ዓለም አቀፍ የ Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ባሻገር (ስለ ኃልውናና እውነታ እወቀት የሚያጠና) የፍልስፍና ዘርፍ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት


ተፈጥሮ በአጋጣሚ ወይንም በድንገተኛ የግኡዝነት ስብስቦሽና መደጋግፍ ላይ የጸና አለ መሆኑ ለይቶ በስነ ምርምር አመክንዮ ተደግፎ የሚያስተምረው “Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ” የተሰኘው ፍልስፍና ላይ ያተኮረ ኤደንተስ በመባል የሚተጠራው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሥነ ትምህርት ተንከባካቢና/ተከላካይ RealAudioMP3 የሥነ ካቶሊካዊ ትምህርት የምርምርና የጥናት ማእከል ያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጥናት ከ 25 አገሮች የተወጣጡ ከ150 በላይ ተጋባእያን በማሳተፍ ትላትና በሮማ መከፈቱ ሲገለጥ፣ ለዚህ ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት በማንበብና ንግግር በማሰማት ያስጀመሩት የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖነ ግሮቾለቭስኪ መሆናቸ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት “Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ፣ የፍልስፍና ዘርፈ ጥናት እጅግ አስፈላጊና ማራኪ፣ ይኽም የሰው ልጅ ለፍጹም ለወሰን አልቦነት ለመጀመሪያና ለፍጻሜ የኅልውና የስነ አመክንዮና ሃሳብ መሠረት የሆነውን ለመለየት በሰው ልጅ አእምሮ የሚደረግ የፍልስፍናው ምርምር ከሰብአዊ የባህል መድረክ ጨርሶ ያልተሰረዘ ኩላዊ ባህርይ ነው። አለ “Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ” ምርምር ፍልስፍናዎች ሃይማኖቶችም አበይት አስተሳሰቦችም ባልኖሩ ነበር፣ ስለዚህ ከዚህ አንጻር የሥነ ከግኡዝነት ማዶ ጥናት ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ ለመገመቱ አያዳግትም” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“ለዓበይት የኅላውና የሥነ መሆናዊ ጥያቄዎችና ትርጉም ለመገንዘብ ለማወቅ የሚደረገው የምርምር ጥናት ማንም ቸል የማይለው በበለጠ ደግሞ ሊቃውንትና ምሁራን የሚያተኵሩበት” መሆኑ የገለጡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አክለውም፦ “ምሁራንና ሊቃውንትም በገዛ እራሳችው አመለካከትና ለደረሱበት ጥልቅ የምርምር ሃሳብ ገዛ እራስ መዝጋት ያስከተለው ችግር የቅርብ ታርክ ትውስት ነው። በአሁኑ ወቅት ጥልቅና አበይት የሥነ ኅልውና ጥያቄዎችና ትርጉም የመሻቱ ዝንባሌ ቸል እየተባለና ከዚህ ጥልቅ ኃላፊነት ውጭ ትሁኖ ለመኖር መንገድ የሚያስቀይሱት በዓለም የሚፈጠሩት የተደረሱት የዕደ ጥበብ ግኝቶች ከግኡዝነት ወዲያ ላለው ምርምር እንዲዘነጋ የሚያደርጉ ተመስለው ሊታዩ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን ትርጉምና መሠረት መሻት ከሰው ልጅ መሆናዊነት ለመሰረዝ አይቻልም” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ወደ ላይ የማቅናቱ ሰብአዊ ባህርይ ለማሰናከል ወይንም እንዲዘነጋ ለማድረግ የተለያዩ ያንን የሚፈለገውን እውነት ለመተካት የሚቃጣቸው እውነት እንደሆኑ ተደርገው የተሰበኩት ኅልዮዎች ሁሉም አልፍዋል” እንዳሉ ብፁዕ ካርዲናል ግሮቾለቭስኪ ባሰሙት ንግግር ማስታወሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
የዓውደ ጥናቱ ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ኸሱስ ፈርናንደዝ ሄርናንደዝ፦ “በህዚ ባለንበት ወቅት “Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ” የተሰኘው የጥናት ዘርፍ የሚያገል የምሁራን አዝማሚያ በስፋት ይታያል፣ ስለዚህ የተከሰተውና ይኽ ደካማው አስተሳሰብ ተብሎ የሚገለጠው ባህል Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ የተሰኘው ፍልስፍና እንዲዘነጋ ለማድረግ ቢቃጣውም ዳሩ ግን ያቀረበው መሠረተ አልቦ አስተሳሰብ ከሰው ልጅ የሥነ ኅልውና ጥያቄ ለማጥፋት እይቻለውም። ስለዚህ Metaphysics-ከግኡዝነት (አካላዊ) ማዶ ጥናት ብቻ ነው ለመሆናችንና ለምንፈጽመው ተግባር ውህደት አቅጣጫና ትርጉም የሚገልጠው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.