2012-11-07 14:20:24

የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ማእከል ያደረገ ዓውደ ጥናት


ትላትና ሮማ በሚገኘው Lumsa የተሰየመው ነጻው ፍልሰታ ለማርያም መንበረ ጥበብ አዘጋጅነት “የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ምሥረታ፣ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እስካ’ለንበት ጊዜ ድረስ” በሚል ርእስ ሥር የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ማእከል ያደረገ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ያመለከቱት የቫቲካን RealAudioMP3 ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ፣ የዚህ ተቋም አላማ ግብረ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና ግብረ ቅድስት መንበር ለዓለም ማሳወቅ መሆኑ ያሰመረው ዓወደ ጥናት ይኽ የመገናኛ ብዙኃን የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሥር ይተዳደር የነበረው ተቋም እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 1986 ዓ.ም. ገዛ እራሱ የቻለ ተቋም ሆኖ እንዲያገለግል የወሰኑት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሆናቸው በማስታወስ፣ ሆኖም የተቋሙ ምሥረታው ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጋር የተያያዘ መሆኑና ይኽም የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ሂደት ወቅት ስለ ቅዱስ ጉባኤው በተመለከተ፣ ስለ ጉባኤው ለማወቅና ሂደቱም በተመለከተ ዜና በጉጉት ይጠባበቍ ለነበሩት ምእመናንና ሕዝበ እግዚአብሔር በጠቅላላ ለመንግሥታትና ጋዜጠኞች ጭምር አንዳንድ መግለጫዎችን በይፋ ለመስጠት በሚል እቅድ መሠረት የማስታወቂያና የግኑኝነት ጉዳይ ቢሮ በሚል ስያሜ መጀመሩንም በተካሄደው ዓወደ ጥናት አስተምህሮ ያቀረቡት የቅድስት መንበር የዜናን ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በማብራራት፣ ይኽ በአሁኑ ወቅት የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል በሚል ስም የሚታወቀው ተቋም የውስጥ (የቤተ ክርስትያን፣ የቅድስት መንበር፣ የአገረ ቫቲካን)ና የውጭ አበይትና ዓለም አቀፍ ርእሰ ጉዳዮች በተመለከተ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት የሚሰጠው የቅድስት መንበር ውሳኔ፣ አመለካከት የሚያስተዋውቅ ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ገለጡ።
ከዚህ ቀደም የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ በመሆን ያገለገሉት ጆኣኪን ናቫሮ ቫልስ በአውደ ጥናቱ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ስለ አበይት አንገብጋቢ ግብረ ገባዊ ሥነ ምግባራዊ ስለ እምነት ጉዳይ በተመለከቱ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳይ ጭምር ቅድስት መንበር የምትከተለው መሠረታዊ ሃሳብ፣ አስተያየት በማያሻማ ሁኔታ ለምብራራት የሚያገለግል ተቋም መሆኑ ጠቅሰው፣ ጋዜጠኝነት አሉ ባልታ የሚነዛ ሳይሆን እውነት የሚያጎላ መሆን አለበት የሚለው መሠረታዊ የመገናኛ ብዙኃን ዓላማ የሚኖር ግልጽ ያልተወሳሰበ የገዛ እራሱ ቋንቋና አነጋገር ሥልት የሚከተል ተቋም ነው፣ እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.