2012-11-05 13:49:20

የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን አዲስ ፓትሪያርክ ምርጫ


እ.ኤ.አ. ባለፈው መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ርክስትያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ ሸኑዳ ሶስተኛን እንዲተኩ በግብጽ የበሀሪያ ረዳት ጳጳስ ስልሳ ዓመት ዕድሜ ያላቸው ብፁዕ አቡነ ታዋድሮስ የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ እንዲሆኑ RealAudioMP3 መመረጣቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ 118ኛው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ከድኅረ ሙባራክ ቀዳሜ ፓትሪያርክ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የዚህ የተካሄደው ምርጫ አስፈላጊነትና ያለው አስተዋጽኦ በሮማ የቅዱስ ጊዮርጊስ የግብጽ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ ለፓትሪያርክ ምርጫ በካይሮ የተገኙትን ብፁዕ አቡነ ባርባኣና ኤል ሶርያንይ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ አስመልክተው፣ ብፁዕ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ሁለተኛ ከሥነ መድሃኒት ቅመማ ሊቅ በግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን አቢይ አገልግሎት የሚሰጡ መመረጣቸው ለሁሉም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ምእምናን አቢይ ጸጋ ነው። የነፍሰ ኄር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ሸኑዳ ሶስተኛን ፈለግ ይከተሉ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁኝ በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል፣።








All the contents on this site are copyrighted ©.