2012-11-05 13:46:45

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ዘለዓለማዊ ሕይወት


ካለ ምንም አምልኮአዊ አባሪነትና የተገዥነት ትስስር ልቡን በሰማያዊ ቤት ላይ በማኖር በዚህ መንፈስ ምድርን በሚያፈቅር የነጋዲያን ነጻነት መንፈስ በዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ ያለን እምነት ታሪክንና ወቅታዊ ሁነትን እንድናፈቅር ያበቃናል በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት በተከበረው ዓመታዊ በዓል ሁሉም ቅዱሳት እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ያሉትን ሓሳብ ማእከል በማድረግ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ዘለዓለማዊ ሕይወት በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ ቅዱስነታቸው ሁሉ የሚኖረው የምድራዊ ሕይወት ትርጉም በጥልቀት እንዲያውቅ ማሳሰባቸው ገልጠው፣ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በላቲን ሥርዓት መሠረት ህዳር ወር መባቻ እይታችን በምድራዊው ዓለም ሳይታጠር ከምድራዊ ሕይወት ማዶ ወደ ሰማያዊ ዘለዓላማዊ ቤት ያተኵር ዘንድ በእምነት በማስገንዘብ የመዳን ጸጋ የተቀበሉት ከጌታ ጋር የሚኖሩት የዳኑት ማኅበረ ቅዱሳን በማስተዋል ወቅታዊው ሁኔትን በዚሁ መንፈስ በመመልከት በመንፈስም ከእነርሱ ጋር በሁባሬ መጓዝ እንዲሁም ከዚሁ ዓቢይ በዓለ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን በሞት የተለዩት በተስፋ የምናስብበት የምንጸልይበት የምንዘክርበት ዓመታዊ ዝክረ እለተ ሙታን መታሰቢያ ቀን በዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ ያለን እምነት እንድንኖር ቤተ ክርስትያን ታስተምረናለች ብለዋል።
በቅርቡ በተጠናቀቀው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ ዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ቁ. 14 በመጥቀስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳምራዊቷ ሴት ሕይወት ሰጭ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሰጥ መሆኑ ሲገለጥ፣ እግዚአብሔር ምድራዊ ሕይወታችን የተሻሻለ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን፣ የምድራዊ ሕይወታችን ትርጉምና ከምድራዊ ሕይወት ማዶ የሚጠብቀንን ዘለዓለማዊው ሕይወት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ መናንያን በሚኖሩት የንጽሕና የተአዝዞ እና የድኽነት ሕይወት መሠረትም የዚህ ዘለዓለማዊ ሕይወት መስካርያን ማለትም ከሞት ባሻገር ያለውን የሚጠብቀን ዘለዓላማዊ ሕይወት አድማስ መስካሪያን እንዲሆኑ የተጠሩ ናቸው ብለዋል።
በዚህ ዓለም ጥሮ ግሮ መኖር አስፈላጊ ነው። ዘለዓለማዊ ሕይወት ይጠብቀኛል ብሎ በምድራዊ ሕይወት ልንፈጽመው ከሚገባን ኃላፊነት መቆጠብ ጥበብ አይደለም። እንዳውም ምድራዊው ሕይወታችንን ዘለዓለማዊ ሕይወት ላይ ባለን የእምነት ተስፋ መሠረት በመኖር፣ ምድራዊ ጉዞአችን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በሚል እይታ የሚመራ መሆን አለበት። ይኽ ተስፋ ከሌለ ቀዳሚውና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚቻል አይሆንም በማለት ያቀረቡትን የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.