2012-11-05 13:43:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሙሉ ሱታፌ ከእግዚአብሔር ጋር


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ዝክረ ዕለተ ሁሉም ሙታን አስባ በዋለችበት ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በ 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት የነፍሳተ ሙታን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው RealAudioMP3 ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “ተስፋችን በመስቀል ላይ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው ፍቅር አማካኝነት ቦግ ያለ ነው” በማለት “እኛ ክርስትያኖች ሞትን እንዴት እንጋፈጣለን እንመለክታለን” ከሚለው መሠረታዊ የህልውና ጥያቄ በመንደርደር ቅዱስ አባታችን ማኅበረ ክርስትያን ለዚህ ዓይነቱ ጥያቄ በእግዚአብሔር ላይ ካለው እምነት የመነጨ መልስ የሚሰጥ፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ላይ የጸና እይታ ያለው መሆኑ ሲያብራሩ፦ “በዚህ ዓይነት እምነት የሚኖር ምድራዊ ሕይወትና ሞት ለዘለዓለማዊ ሕይወት ክፍት የሆነ የዚህ ምድራዊ ሕይወት ቀጣይ ህላዌነት ሳይሆን ይኸንን ምድራዊ ሕይወት ልቆ የሚሄድ አዲስ ሕይወት ማለት ነው። የምንጠባበቀው ዘለዓለማዊ ሕይወት ጽንሰ ሃሳብና ኅልዮ ሳይሆን ህያው ከሆነው እግዚአብሔር ጋር ሙሉ ሲታፌ የሚያረጋገጥ ነው” ብለዋል።
ይህ ሱታፌ በእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ፍቅር በእርሱ አማካኝነት እርሱ ከፈጠረው ወንድምና እህት ጋር አንድ ተኵኖ የሚኖርበት መሆኑና ተስፋችን በመስቀል ላይ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጠው ፍቅር ቦግ ያለ መሆኑ ሲያስረዱ፦ ምሉእ ሕይወት ዘለዓለማዊ ሕይወት ነው። ይኽ ሕይወት ልክ ከሚከበው ደመና ባሻገር የሰማይ መኖር እረግጠኛነት፣ ከዚህ ምዳራዊ ሕይወት ባሻገር ዘለዓለማዊ ሕይወት መኖሩን እንገነዘባለን” ካሉ በኋላ የሚያስቡዋቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሁሉም የነፍሳት እረኞች ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት፦ “እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስትያኑን በእምነትና በፍቅር ያገለገሉ፣ በድምራዊ ሕይወታቸው የተለያዩ ችግሮች ቢጋረጥባቸውም በተስፋ በእምነትና በፍቅር በመኖር በዚህ እምነት የእግዚኣብሔርን መንጋ በመምራትና በመንከባከብ በዘለዓለማዊ ሕይወት ተስፋ በማኖር ያለፉ” መሆናቸው በማስታወስ፣ በዚህ ቀን ሁሉም ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ውዶቹን በመጎብኘት የሚፈጽመው መንፈሳዊ ንግደት፦ “በዘለዓለማዊ ሕይወት ካለን ተስፋ የመነጨ መንፈሳዊ ተግባር ነው፣ ያለን ሲታፌ ሞትም ቢሆን እንደማይሽረው የሚያረጋግጥ ቅዱስ ተባር ነው” እንዳሉ የቅዳሴውን ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.