2012-11-02 14:36:15

የሰላም የእግር ጉዞ በቅድስት መሬት


አስተማሪዎች ተማሪዎች የክልል መስተዳድር አባላት የተለያዩ የማሙያተኞች ማኅበራት የተሳተፉበት በጠቅላላ 200 ሰዎች የሰላም መልእክት ለማድረስ በሚል መርህ ሥር በኢጣሊያ ከፐሩጃ አሲዚ የሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ የሚያንጸባርቅ የሰላም የእግር ጉዞ በእስራኤልና በእስራኤል በተያይዙት የፍልስጥኤም ክልሎች መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ የሰላም የእግር ጉዞ የተለያዩ የሰብአዊ መብትና ክብር ተማጓች ማኅበራት በኤውሮጳ የሚገኙት ቅርንጫፎቻቸው አማካኝነት ያሳተፈ የሰላም ጠረጴዛ የተሰየመው ማኅበር ያዘጋጀው ሲሆን፣ ይኽ የሰላም የእግር ጉዞ በስደሮት ራማላሕ በሄብሮን በእየሩሳሌም ከተካሄደ በኋላ ትላንትና በቤተ ልሔም ቀጥሎ መዋሉ የሰላም ጠረጴዛ ማኅበር በኢጣሊያ ለሚገኘው ቅርንጫፍ ተጠሪ ፍራንቸስኮ ካቫሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።
የዚህ ዓይነቱ የሰላም የእግር ጉዞ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በኢጣሊያ ከፐሩጃ እስከ አሲዚ የሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ ጋር በተያያዘ መልኩ ከቤተ ልሄም እስከ እየሩሳሌም የሰላም የእግር ጉዞ መካሄዱ አስታውሰው፣ በሰላም እጦት በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀውና ውጥረት የሚታይበት ክልል ሰላም በመገንባት ጥሪ ቀዳሚ ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ፣ ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻል መሆኑ ታምኖበት ለሰላም ውይይት መድረክ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓይነት ተጨባጭ ተግባር ያለው ሰላም የመሻት ፍላጎት የሚያንጸባርቅ መርሃ ግብር ማከናወን አቢይ ጠቀሜታ አለው።
“በሰላም ለመኖር ተብሎ ከሌላው ጋር ላለ መገናኘት የሚገነባው ባህላዊ ማኅበራዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ የልዩነት አጥር ለሰላምና ለመረጋጋት ዋስትና አያሰጥም ስለዚህ ተነጥሎ በሰላም ለመኖር አይቻልም። ይኽ የሰላም የእግር ጉዞ ይኸንን በማንጸባረቅ መፈራራት ከሚያጸናው የልዩነት አጥር ተላቆ የጋራ መከባበርና መቀባበል የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ በማስተግበር ብቻ ሰላም ለማረጋገጥ መነሳት ነው። ካልሆነ ግን ዘወትር በፍርሃ ተውጦ መኖር ይሆናል። ፍርሃት የሚያቆመው ውሳኔ ፈጽሞ ሰላም አያስገኝም” ካሉ በኋላ እስራኤላውያንና ፍልስጥኤማውያን የሰላም እንቅስቃሴና ማኅበራት አባላት እንዲሁም ከኤውሮጳ ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የተወጣጡ ዜጎች ያሳተፈ የሰላም የእግር ጉዞ እንደነበርም ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.