2012-11-02 14:42:44

ቅዱስ መጽሐፍ ላለ መፍራት የሚሰጠው ምክንያት


የሮማ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮ ተጠሪ አባ ማውሪዚዮ ሚሪሊ “ቅዱስ መጽሐፍ ላለ መፍራት የሚሰጠው ምክንያት” በሚል ርእስ ሥር ለወጣቶች የደረሱት በቅዱስ ጳውሎስ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ የበቃው መጽሐፋቸው በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ጋር ባካሄዱት RealAudioMP3 ቃለ ምልልስ፦ እንዲህ ባለ ርእስ ሥር መጽሐፍ ለመድረስ ያነቃቃቸው በሮማ ሰበካ ደረጃ ከወጣቶች ጋር የተካሄዱት የተለያዩ ጉባኤዎችና ለወጣቶች ከሚሰጡት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ተመክሮ መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ መጽሐፍ ላለ መፍራት የሚያቀርባቸው ምክንያቶች የእግዚአብሔር ቃል የሚያቀርበው ምክንያት በመለየት፣ በማስተንተን 365 ምክንያቶች በማቅረብ ለአንድ ዓመት መንፈሳዊ ጉዞ የሚሸኝ መንፈሳዊ ምክር የተኖርበት መጽሐፍ ነው ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እትፍሩ በማለት ካስተጋቡት ቃል በመንደርደር፣ ይኸንን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ ማለትም ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራእይ ያሉትን መጻሕፍቶችን በመዳሰስ እግዚአብሔር ላለ መፍራት የሚሰጠን ምክንያቶች ማእከል ያደረገ መሆኑ አብራርተው፣ ላለ መፍራት ምክንያታችን እግዚአብሔር መሆኑ በቃለ እግዚአብሔር አማካኝነት በማረጋገጥ፣ ወጣቱን ለመደገፍ በተለይ ደግሞ በዚህ የእምነት ዓመት ለማበረታታትና በእተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በሚዘጋጁት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የወጣቱ ሱታፌ ለማነቃቃት እምነት በቃልና በሕይወት መስካሪ ሆኖ እዲያድግ ለመደገፍ ነው ካሉ በኋላ፣ የደረሱት የመጽሐፍ ሽያጭ ገቢ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደጃነይሮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በኤኮኖሚ ችግር ሳቢያ ከመሳተፍ ውጭ ለሚሆኑት ወጣቶች ለማሳተፍ ታቅዶ ለተወጠነው የግብረ ሠናይ እቅድ የሚውል ነው በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.