2012-11-02 14:32:48

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ አቡነ ፎርተ፦ ቤተ ክርስትያን በዓለም ፊት የኃሴትና የተስፋ መግልጫ ነች


በአገረ ቫቲካን የሲኖዶስ አዳራሽ ለሦስት ሳምንት “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት” በሚል ርእስ ሥር በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት ተጥርቶ የተካሄደው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ እንደሚያመለክተው RealAudioMP3 “እግዚአብሔር የፈጠረውና ያፈቀረውን ዓለም በእማኔና በቅንነት መመልከት” የሚል ሃሳብ የተኖርበት ይኸንን አቢይ የቤተ ክርስትያን ሁነት በማስመልከት የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢጣሊያ የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ላቀረበላቸው ቃለ መጠይስ ሲመልሱ፦ “በቅድሚያ የመላ ዓለም የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ያላቸው ተኣዝዞአዊ ውኅደት፣ ቤተ ክርስትያናዊነት የሚያጎላ ይኽ ደግሞ የዓለም መንደር መሆኑ የማያዛባው በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዙሪያ የሚጸናው አንድነት የጎላበት ኵላዊነት መግለጫና ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ በወቅታዊ ምልክት አማካኝነት ለሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እማኔ ኃሴትና እምነት የተንጸባረቀበት፣ ዓለምን በእግዚአብሔር ዓይኖች በቅንነትና በእማኔ መመልከት ያለው አስፈላጊነት የጎላበት ቅዱስ ጉባኤ ነው” ብለዋል።
ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል እርሱም ወንጌል ለማካፈል አዲስ ቋንቋ መጠቀም በዚህ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት በተስፋፋበት ዓለም አዲስ ቋንቋ በመጠቀም ሥነ ጥበብ አማካኝነት ማወጅ ያለው አስፈላጊነት የተሰመረበት መሆኑ ሲያብራሩ፦ “የሥነ ውበት መንገድ እርሱም ክርስቶስ ፍጹም መልካምና ውብ እረኛ መላውን የሰው ልጅ በተለይ ደግሞ በድኽነት የተጎሳቆሉትን የዚህ እጹብ ድንቅ ውበት ተካፋዮች መሆናቸውና እወተኛ የውበትን ስሜት ለመኖር ሁሉም የተጠራ የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መሆኑ ማበሠር ማለት ነው። እግዚኣብሔር ፍጹም ውበት ነው፣ ሁሉም በኑባሬ የዚህ ውበት ሱታፌ ነው። ስለዚህ የኸንን የሚያጎላ አዲስ ቋንቋ መጠቀም” ማለት ነው ብለዋል።
በድህነትና በታሪክ መካከል ያለው ግኑኝነት አቢይ የቲዮሎጊያ ተጋርጦ ነው። ከግዜ መለወጥ ምክንያት ቲዮሎጊያ ቅዉም ዓላማው ሳይስት አዲስ ቋንቋ የመጠቀም ብቃት ሊኖረው እንደሚገባም ሲገለጡም፦ “የብሥራት ቃል ትስብእትነቱን ለማረጋገጥ ባህሎች በእምነት መስበክ ነው። ስለዚህ ባህሎች በእምነት የመስበኩ ተግባር ዘወትር እየታደስ መቀጠል እንዳለበት የሚያመለክት ነው” ካሉ በኋላ፣ አያይዘውም ወንጌል ለሁሉም መሆኑና ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ለዚህ አገልግሎት የተጠሩ ናቸው። ዓለማውያን ምእመናን ከብፁዓን ጳጳስትና ከቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ጋር በመሆኑ ይኸንን እምነት ለመመስከር የተጠሩ ናቸው። ስለዚህ ቤተሰብ ቀዳሜ ሰባኬ ወንጌል መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው። ሁሉም እንደየደረጃውና ጥሪው አማካኝነት ሰባኬ ወንጌል መሆኑ ሲገለጡ፦ ሁሉም በዚህ የቅድስት ቤተ ክርስትያን ጥሪ ሱታፌ አለው፣ ሁላችን በአቢይ የቅዱስ ጴጥሮስ ጀልባ ውስጥ መሆናችን የሚያሳስብ ተግባር ነው” ብለዋል።
አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሁሉም አቢያተ ክርስትያን የጋራው ግኑኝነት የሚያነቃቃ ምስክርነት በፍቅር የሚል ነው። ይኽ ደግሞ እኔ-ባለቤት ሌላው እርሱም አንተ-ባለቤት የሆነውን ለመቀበል ለማስተናገድ የተጠራ መሆኑ ያመልከተናል። በሁሉም መስክ ከሁሉም ጋር መወያየት ያለው አስፍላጊነት ሲገልጡ፦ “በመካባበርና ሌላውን በመቀበል ለኅልውናችን ውበት ያጎናጸፈውና ምክንያትም ለሆነው በእምነት ታማኝ ሆኖ ወንጌልን ማበሰር ማለት ነው” ብለዋል።
ስለዚህ፦ የተካሄደው ሲኖዶስ ቤተ ክርስትያን በታደሰ ፍሰሃና ተስፋ ለሁሉም ሰው ዘር ይኸንን የፍሰኃና የተስፋ ውበት ለማበሰር የተጠራች መሆንዋ ለዚህ ቅዱስ ተግባር በአዲስ መንፈስ የሚያነቃቃ ነው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.