2012-11-01 12:22:53

ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ለዕለተ ስደተኞች መልዕክት አሰተላለፉ፣


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናትና ታስቦ የዋለውን የስደተኞች ዕለት መሠረት በማድረግ መልዕክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መገለጫ አስታውቀዋል ።መግለጫው እንዳመለከተው ሀገራቸው እና ቀያቸው ጥለው የሚሰደዱ ሰዎች እምነት እና ተስፋ አንግበው እንደሚጓዙ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት መልእክት አስገንዝበዋል። በአጠቃላይ ሰዎች ሁሉ በተለይ ክርስትያኖች እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች የስደተኞች ወደር የሌለው ሰብአዊ ክብራቸው ማክበር እንደሚጠበቅባቸው የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት መልእኽት መጠየቁ ቅድስት መንበር ላይ የወጣ መግለጫ አመልክተዋል።
በደቡባዊ ጣልያን ሲሲሊ ክፍለ ሀገር በላምፐዱሳ ደሴት እና አከባቢ ከሰሜናዊ እና አፍሪቃ እና አፍሪቃ ቀንድ ሀገራት የተሰደዱ በርካታ ስደተኞች እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን የደሴቲቱ ፡ ቆመስ ዶን ስተፋኖ ናስታሲ ቅድስነታቸው ሀገራት አቀፍ የስደተኞች ዕለት ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረት በመስጠት መግለጫ መሰጠታቸው ከላምፐዱሳ ከተማ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።
በደቡባዊ ጣልያን የሲሲሊ ክፍለ ሀገር የላምፐዱሳ ደሴት ቆመስ ዶን ስተፋኖ ናስታሲ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት ፡ በነዲክቶስ 16ኛ Gaudiem Spes ደስታ እና ተስፋ የተሰየመ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ በመጥቀስ ሰብአውነትን ትኩረት የሰጠ እና ቤተ ክርስትያን የሌሎች ሰዎች ሥቃይ እና ደስታ የቤተ ክርስትያን ሥቃይ እና ደስታ መሆኑ ያስረዳል ካሉ በኃላ ፡ ትናትና መልዕክት ይህንኑ የሚያንጸባርቅ እንደሆነ አስገንዝበዋል ።
ቅድስነታቸው ደስታ እና ተስፋ አንግበው እንዲራመዱ በሄድባቸው ሀገራት ሰብአዊ መብታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የስራ እና የሕክምና አገልግሎት እንድያገኙ ቅድስነትቸው በአጽኖት መጠየቃቸው በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ እና ይህን ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ ተስፋ ማደረጋቸው የላምፐዱሳ ደሴት ቆመስ ዶን ስተፋኖ ናስታሲ ገልጸዋል። ስደተኞች ከሚኖሩበትሕብረተ ሰብ ተዋህደው እንዲኖሩ እና እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠራቸው ሰዎች ወንድማሞች እና እህታሞች መሆናቸው መዘንጋት እንደማይገባ እና ቤተ ክርስትያን ስደተኞችን የመንከባከብ ግዴታ እንዳላት እና በካሪታስ በኩል ለስደተኞች የምትሰጠው ሰብአዊ አገልግሎት የሚመሰገን እንደሆነ የቅድስነታቸው ለስድተኞት ዕለት ያስተላለፉት መልዕክት ማስታወቁ ይታወቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.