2012-10-31 13:39:53

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ፦ ተከታታይ ሥርጭት


በዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት እየተከበረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በአርቆ አሳቢነት ተጠናቅሮ እንዲቀርብ በማለት ያቀረበው ማሳስቢያ ተከትሎ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ RealAudioMP3 ይፋ ሆኖ ለንበብ የበቃበው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህረተ ክርስቶስ መዝገቡ ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ነው።
የቫቲካን ረዲዮ ልክ ለዝክረ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ጉባኤ ምክንያት ተከታታይ የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ሰነዶች ታሪካዊ ቲዮሎጊያዊ አንቀጸ እምነታዊ ባህርዩ ላይ ያተኮረ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ ቤተ ክርስትያን ጉባኤዎች ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ ተመርቶ እንደ ቀረበው የስርጭት መርሃ ግብር፣ ይኸው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ያረደረገ ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር እንደሚያቀርብ ሲገለጥ፣ አባ ኮዋልዝይክ የሚያቀርቡት የሥርጭት መርሃ ግብር የመጀመሪያው ተከታታይ ሥርጭት መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ በእምነት ዓመት ምክንያት ካቀረቡት ማሳሰቢያዎች ውስጥ አንዱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በተከታታይ አንድ ወጥ በሆነ ስልት እንዲነበብ እንዲጸለይ የሚልና ለእምነት ዓመት ምክንያት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት ‘Porta Fidei-የእምነት በር’ ሓዋርያዊ መልእክት” ዘንድ ተመልክቶ እንዳለም ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን የካቶሊካዊ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ እውነተኛ የእምነት ማስፈጸሚያና ለእምነት ድጋፍ መሆኑ ያሰመሩበት ሃሳብ በጥልቀት እንደሚመለከት ነው ብለዋል።
ይኽ የዛሬ 20 ዓመት በፊት ለንባብ የበቃው የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ የገዛ እራሱ የአስተዋጽዖ ሰነድ ያለው ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ለወጣቶች ለየት ባለ መልኩ ያተኮረ ‘CatechismoYouCat-ትምህረት ክርስቶስ ለወጣት ትውልድ’ በሚል ርእስ ሥር ተደርሶ በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለንባብ መብቃቱንም አስታውሰው፣ የእምነት ዓመት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ላይ ያነጣጠረ የጥልቅ ጥናት የንባብና የጸሎት መርሃ ግብር ይወጠን ዘንድ ያለው አስፈላጊነት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በማሳሰብ ገልጠዉታል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. “‘CatechismoYouCat-ትምህረት ክርስቶስ ለወጣት ትውልድ መዝገብ” መግቢያ ላይ እንዳመለከቱት “ወጣቱ ትውልድ ትምህርተ ክርስቶስ በጥልቅና በጋለ ስሜት በጽናት በግል በማኅበር በቤተሰብ እንድያነበውና እንዲያስተነትነው፣ በማሳሰብ፣ በማኅበራዊ የድረ ገጽ በኩል ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥም ከሁሉም ዓለም ወጣቶች ጋር የግኑኝነትና የውይይት ርእስ በማድረግ በእርሱ ታንጾ እንዲያድግ አደራ እላለሁኝ” በማለት የሰጡት ምክር ጠቅሰው፣ እንዲህ ባለ መልኩ ቅዱስነታቸው እንዳሉትም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ላይ ያተኮረ ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር እምነት መግለጥ ከሚለው የመጀመሪያ ክፍል ርእስ በማድረግ እንደሚቀርብ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.