2012-10-31 13:35:40

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ፦ ክርስቶስን የማወጅ ኃላፊነት


የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ ባለፈው እሁድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጠናቀቀው ለሦስት ሳምንት “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የክርስትና እምነት ለማስፋፋት” በሚል ርእስ ዙሪያ በቅዱስነታቸው ተጠርቶ የተካሄደው የመላ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓ ጳጳሳት RealAudioMP3 ሲኖዶስ አስመልከተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉት ሁሉ ወንጌል የመመስከር ኃላፊነት/ኅሊናዊ ግዴታ አለባቸው” በሚል ሃሳብ በማጠቃለል፣ ሲኖዶሱ በይዞታው እጅግ ጥልቅ፣ ሃብታም እንደነበር ገልጠው፣ “አስፍሆተ ወንጌል የአዕምሮ ብቃት ወይንም ምሁርነት የሚጠይቅ ይዞታ ማቅረብ ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ምሁርነት የሚጠይቅ ይዞታ ማቅረብ ማለት ከሆነ መረጃ ማቀረብ ወይንም ማስተላለፍ ይቀራል፣ ስለዚህ አስፍሆተ ወንጌል ምስክርነት ማለት ነው፣ የእያንዳንዱ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለ ኃላፊነትም ነው። አማራጭ ሆኖ የጥቂቱ ማኅበረ ክርስትያን አባላት ግዴታ ሳይሆን ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ሁሉ የሚመለከት ኅሊናዊ ግዴታ” ነው ብለዋል።
“አስፍሆተ ወንጌል በአንድ ወቅት አንድ ሰፊ ተቀባይነት የነበረው ጥንታዊ የክርስትያናዊ ባህል ይዞታ ሆኖ ይታይ እንደነበር” ከገለጡ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያይዝ ይላሉ፦ “በአሁኑ ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ሰብአዊ እውቀት የሚል ባህል በሰፋበት ወቅት የእያንዳንዱ አገር ባህል በወንጌል መስበክ ማለት ነው” የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
Fraternità di Comunione e Liberazione-የአርነትና ነጻነት ወንድማማችነት እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ክብሩ አባ ኹሊያን ካሮን በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለእምነት ዓመት መግቢያ ምክንያት የለገሱት ‘Porta Fidei-የእምነት በር’ የተሰየመው ሓዋርያዊ መልእክትና ለሲኖዶስ ማዘጋጃ የረቀቀው የዝክረ ነገር ሰነድ፣ የክርስትና እምነት የታወቀ ነው ብሎ በዘልማድ መመልከቱና ሌላውም ክርትስያን ክርስትና የፈረቃ ወይንም የሰንበት ተግባር ብቻ ሳይሆን በእለታዊ ኖሩ የሚገለጥ የሚኖር መሆን አለበት የሚል አንኳር ሃሳብ” ማእከል ያደረገ መሆኑ ጠቅሰቅ፣ ሲኖዶስና የእምነት ዓመት ተጣምረው የሚሄዱ ናቸው። ስለዚህ አስፍሆተ ወንጌል በቃልና በሕይወት እምነት በቃልና በሕይወት ለክርስትና እምነት መስፋፋት መሠረት መሆኑ በተለያየ መልኩ የተካሄደው ሲኖዶስ አስምሮበታል” ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.