2012-10-25 08:55:30

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 24/10/2012)
እምነት የእግዚአብሔር ጸጋ፣ ነጻ የሰው ልጅ ተግባር ነው


ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ
በዛሬው የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ በዚህ ባለንበት ዘመን የክርስትና እምነት ትርጉም በሚለው ርእስ ላይ ለማስተንተን እወዳለሁኝ፣ ያሉት ቅዱስ አባትችን፣ እምነት ማለት ምን ማለት ነው? በዚህ ዛሬ ሥነ ምርምርና የግብረአዊ ሞያ ወይንም እደ ጥበብ እጅግ ተራቆ በመጠቀበት ከዚህ በፊት ሊታሰብ RealAudioMP3 ለማይቻለው አድማስ በር በከፈተበት ወቅት እምነት ትርጉም አለውን? ዛሬ እምነትን መኖር ሲባል ወይንም ማመን ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት እርግጥ ነው በዚህ በምንኖርበት ዘመን የታደሰ የእምነት ሕንጸት አስፈላጊ ነው፣ ይኽም ሲባል ለእምነት እውነታዎችና ለድህነት ክንዋኔዎች የተረጋገጠ ማስተዋልን የሚያጠቃልል እውቀት በተለይ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከእውነተኛውና ኅያው ከሆነው እግዚአብሔር ጋር ለመገናኘትና በእርሱ አማካኝነትም በእግዚአብሔር ላይ እማኔ ለማኖር መላ ሕይወትን የሚያጠቃልል ሁነት ማለት ነው።
ዛሬ በአካቢያችንና በዙሪያችን የመንፈሳዊ ምድረ በዳነት ሲያድግ ይታያልይኽም በአለማችን የሚከሰቱት አንዳንድ ሁኔታዎች በጠቅላላ እድገት የተረጋገጠው የተደናላደለው ኑሮ የተረጋገጠበት በሚመስለው ይኽ ካለው አሉታዊ ጎድኑ ወንድማማችነት ለተካነው ማኅበረሰብ ግንባታ የማይበጅ ሆኖ እንደሚገኝ በውስጣችን ይኸንን ዓይነት ስሜት የሚቀሰቅስ ሆኖ ይገኛል። ያም ሆኖ ይኽ በሥነ ምርምር የተርጋገጠው ብልጽግና እንዲሁም የግብረአዊ ወይንም እደ ጥበብ ስኬታማነት ሁሉ እውን ቢሆንም የሰው ልጅ በእውነት ነጻና የነጻነቱ ባለ ቤቶ ሆኖ ወይን የበለጠ ሰብአዊ ሆኖ አይታይም፣ እንዳውም ብዝብዛ፣ ማምታታት፣ በሌልው ላይ ተጽእኖ የማሳደር፣ ዓመጽ፣ ጭቆና፣ ኢፍትኃዊነት የቁሳዊነት ባህል ብቻ የሚያረማምደው በሚታየውና በሚጨበጠው በእጅ ሥራ ላይ ብቻ እምነት ለማኖር የሚገፋፋ ነው። በሌላው ረገድ ብዙዎች አቅጣጫ ተዛብቶባቸው መንገድ ለመለየት ተስኖአቸው ካለው ተጨባጩ አድማስ ባሻገር ለመመልከት ነገር ግን በአግድም ዝንባሌ ተውጠው ሁሉን ነገር ይኽንን የሚጻረርም ቢሆን አሜን ብሎ ለመቀበልና ለማመን ተዳርገው ይገኛሉ። ከዚህ በመንደርደርም በእውነት ተጨባጭ የሆነውን ጥያቄ እርሱም መኖር ትርጉም አለው ወይ? መጻኢነት ለሰው ልጅ፣ ለእኛ ለአዲስ ትውልድ ይኖር ይሆን? ነጻነትችን ስኬታማ እንዲሆን በየትኛው አቅጣጫ ሊመራ ይገባዋል? ከሞት ባሻገር ምን ይጠብቀናል? ተራ ተመስለው የሚታዩት ጥያቄዎች ለማንሳት ግድ ይሆናል።
የሥነ ምርምር እወቅት ምንም’ኳ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ቢሆንም ቅሉ፣ ለሰው ልጅ ሕይወት ለብቻው ግን በቂ አይደለም። ዕለታዊ እንጀራ ብቻ ሳይሆን ፍቅር፣ ትርጉም፣ ተስፋ፣ ቀውስና ችግርና ጨለማና መዛባት ቢኖርም እውነተኛ ትርጉም ባለው መሠረት ለመኖር እንዲቻል ጽኑ መሠረት ያስፈልጋል። እምነት ይኸንን ጽኑ መሠረት የሚለግስ ለንድ አንተ-ባለቤት ለሆነው የሥነ ምርምር እወቅት ከሚሰጠው እርግጠኝነት በላይ የተረጋገጠ መረጋጋት እርካታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ማመን በእርሱ ላይ እምነትን ማኖር ማለት ነው። እምነት የሰው ልጅ ቀልብ የሚያገል የእውነት በተለይ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር እውነተኛነት አለ የአእምሮ ብቃት መቀበል ማለት አይደለም፣ ስለዚህ እምነት የሰውን ልጅ የአእምሮ ብቃት አይክድም፣ እንዲህ በመሆኑም በግብረ ነጻነት በእርሱ አባት ቀድሞ የሚያፈቅር አነተ-ባለቤት በሆነው ተስፋና እምነት በሚለግሰው ላይ እማኔ ማኖርና እርሱን መከተል ማለት ነው። እግዚአብሔርን መከተል አልቦ ይዞታነት ያለው ሳይሆን፣ ለእኛ በክርስቶስ አማካኝነት በሙላት ገዛ እራሱን ግርማውን የገለጠው ለእያንዳንዱ ሰው ልጅ ቅርብ የሆነው እግዚአብሔር በተመለከተ ላለን ግንዛቤ የሚያጎላ፣ በበለጠም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ለእያንዳንዱ ሰው ልጅ አለ ምንም ገደብ፣ በመስቀሉ በእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ አማካኝነት ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠት ማለት በሆነው ስጦታ ገዛ እራሱን አሳልፎ በመስጠት ፍቅሩን ገልጠዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ እግዚአብሔር ሰብአዊነታችንን ወደ እርሱ ለማድረስ በሰብአዊነታችን ሙሉ በሙሉ ዝቅ ማለቱን እንገነዘባለን። እምነት ላይ እምነትን ማኖር በእርሱ ማመን በሁሉም ሰብአዊ ሁኔታ በመድረስ በሚለውጠው ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ላይ መታመን ማለት ነው። እምነት መኖር ማለት ከዚህ አንተ-ባለቤት ከሆነው ጋር መገናኘት፣ ተስፋ የሚኖርበት ዘለዓለማዊነትን መመኘት ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊነቱን የሚጸግው እግዚአብሔር ላይ ልክ እንደ አንድ ሕፃን ልጅ መታመን ማለትም፣ ችግሮቻችን በጠቅላላ ሰብአዊነታችን አንተ-ባለቤት በሆነው ዘንድ ማለትም እግዚአብሔር ላይ ማኖር ወይንም ማሳረፍ ማለት ነው። በእምነት አማካኝነት የሚረጋገጠው ድህነት እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ዘር የሰጠው ጸጋ ነው። ስለዚህ ምንም’ኳ የምንኖርበት ዓለምና ዕለታዊ ሕይወታችን አሉታዊ ሁኔታ የሚፈራረቅበት ቢሆንም ቅሉ ክርስትያናዊ እምነት ማለት በታማኝነት ገዛ እርስና ዓለምን እኛ ልንዋሰው የማችያለንን በጥልቅ ትርጉም ለሚደግፈው ገዛ እራስ መተው፣ እነሆኝ ማለት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ተንትነው። ይኽ ነፃው እርግጠኝነት ዋስትና የሆነው እምነት በቃል ልናበስረውና በክርስትያናዊ ሕይወታችን ለንገልጠው ልንመሰክረው ይገባናል ብለዋል።
ዛሬ በዙሪያችን ብዙዎች ይኸንን ብስራት ባለ መቀበል ወዲያ በመተው በግድ የለሽነት ሕይወት የሚኖቱ ብዙ ናቸው፣ ካሉ በኋላ አያይዘውም በመጨረሻው የማርቆስ ወንጌል ምዕ. 16 ቍ. 16 ኢየሱስ ‘ያመነና የተጠመቀ ይድናል የማያምን ግን ይፈረድበታል’ ሲል እውነትኛውን ቁርጥ እድርጎ ነግሮናል። በመንፈስ ቅዱስ ተግባር ላይ የምናኖረው ተስፋ ዘወትር ወንጌልን ለናበስርና ልንሰብከውም እምነትን በብርታት አለ ምንም ፍርሃት እንመሰክረውም ዘንድ ይገፋፋናል፣ እምነትን አምቢ ማለትና አለ መቀበል ወይንም እምነትን በመቀበል ለምናቀርበው ስብከትና ብስራት የተለያየ መልስ ሊሰጠው ይችላል። ቅዱስ አቆስጢኖስ ‘እኛ ዘሩን እንዘራለን ዘሩን…ነገር ግን ዘሩን ስንዘራ ይሚሳለቁብን የሚቀልዱብንና የሚንቁንን አሉ፣ እነርሱን የፈራን እንደሆን የምንዘራው ዘር አይኖረንም አዝመራ በደረሰም ጊዜ የምንሰበስበው ምርት አይኖረንም፣ የዘሩ ምርት የሚገኘውም ከመልካሙ ለም መሬት ነው (Discorsi sulla disciplina cristiana-ስለ ክርስትያናዊ ሥርዓት ቃለ ሰነድ 13,14: PL 40, 677-678 ተመልከት) ሲል ይገልጠዋል። ስለዚህ ለተበሰረው ለሚሰበከው የሚሰጠው እምቢተኝነት ሊያስደነግጠንና ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም። እንደ ክርስትያኖች መጠን የለሙ መሬት ምስክሮች ነን። እምነታች ምንም’ኳ ሰብአዊ ውስንነት ያለን ቢሆንም ቅሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል ዘር ተኑሮበት የተትረፈረፈ ፍትህ ሰላምና ፍቅር አዲስ ሰብአዊነትና ድህነት የተሰኙትም ምርቶች የሚሰጥ ለም መሬት እንዳለ ያረጋግጥልናል ብለዋል።
የሰው ልጅ፣ ሞቶ ሞትን አሸንፎ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የመዳን ጸጋን የለገሰው ወንጌሉን ለህልውናችን ብርሃን ሆኖ እንዲመራን ገዛ እራሱን ለገለጸው እግዚአብሔር ሰብአዊ ልብችንና አእምሮአችን ክፍት የመሆን ባህርዩ ከየት ነው? እኛ በእግዚአብሔር እንታመናለን በእርሱ ላይ ያለን እምነት እርሱ ቅርባችን ሆኖ ስለ ነካን ከሞት የተነሳው መንፈስ ቅዱስን የሰጠንም ኅያው በሆነው እግዚአብሔር ላይ እምነት እንዲኖረን ነው። ስለዚህ እምነት ሰማያዊ ጸጋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ “የግልጸት ግንዛቤ ዘወትር በጥልቀት ከፍ እያለ እንዲሄድ መንፈስ ቅዱስ ካለ ማቋረጥ እምነትን በጸጋዎቹ ይፈጽመዋል.፣ ሁሉም በእውነት ላይ እምነታቸውን ለማኖር እና የእምነት ጣፋጭነቱን ለማጣጣም የሰው ልጅ ልብና አእምሮ ለእግዚአብሔር ክፍት እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ ውስጣዊ ድጋፍ ይሆናል (Cost. dogm. Dei Verbum-አንቀጸ እምነት ድንጋጌ፣ ቃለ እግዚአብሔር 5) በእምነት በምናደረገው ጉዞ መሠረቱም ምሥጢረ ጥምቀት ነው። ይኽም መንፈስ ቅዱስ የሚጸግወን ምሥጢር በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች የሚያደረገን በአማኞች ‘በቤተ ክስትያን’ ማኅበረሰብ ጋር የሚያስተባብረን ነው። ስለዚህ በገዛ እራስ ኃይል አምነት አይገኝም፣ እምነት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ነው። ለብቻ አይታመንም ለብቻ በእምነት አይኖርም፣ በማኅበረሰብ ከወንድሞች ጋር ተኩኖ የሚኖር ነው። እያንዳንዱ አማኝ ወይንም ምእመን ይኸንን አሜን ተአምኖተ እምነት አድርጎ በመናዘዝ ከወንድሞች ጋር በጋራ እንዲኖረውም ተጠርተዋል።
እምነት ጸጋ ነው፣ ሆኖም ግን የሰው ልጅ ጥልቅ ነጻ ተከትሎ ወይንም ምርጫም ነው። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ፦ “ማመን ሊኖር የሚችለው በጻጋ በመንፈስ ቅዱስ ውስጣዊ እርዳታ ብቻ ነው፣ ነገር ግን ማመን በትክክል ስበአዊ ድርጊት መሆኑም እውነተኛ ነገር ነው። በእግዚአብሔር ማመንና የገለጣቸውን እውነቶች አጥብቆ መያዝ የሰውን ነጻነትም ሆነ የማሰብ ኃይል አይቃረንም (ቍ. 154 ተመልከት)፣ ያመለክተዋል። እንዳውም ከፍ ከፍ በማድረግ ሕይወትን የሚያነቃቃ ነጻነትን የሚክድ ሳይሆን ከነጻነታችን እንደ መሰደድ ከእኛ ውጭ ማለትም ከራስ መዘጋት የሚያገል ከራስ መተማመን ከራስ የአእምሮ ስልት ተገዥነት የሚያላቅቅ እውነተኛ ነጻነት ለመጨበጥ የሚያስችለንን መንገድ እንድንገዘብ ለሚያደረገን ለእግዚአብሔር ተግባር አሜን እንድንል ያበቃናል። እምነት ወይንም ማመን በሙሉ ነጻነት ገዛ እራስ እነሆኝ ብሎ ማቅረብ በደስታ በታሪክ ልክ አብርሃም ናዝራዊቷ ማርያም እንዳደረጉት ለእግዚአብሔር እቅድና አሳቢነት ማቅረብ ማለት ነው። እምነት ትርጉም ያለው ልባችንንና አእምሮአችን ለእግዚአብሔር አነሆኝ ለማለት ክፍት የሚያደርግ የኢየሱስ ጌትነቱን የምንናዘዝበት ማለት ነው። ይኽ ደግሞ ሕይወት ሆኖ ወደ ሙሉእ ትርጉም የሚመራ አዲስ የሚያደርገው በደስታ ሃብታም በማድረግም ለታማኝ ተስፋ መንገዱን ክፍት የሚያደርግ ማለት ነው ሲሉ ያቀረቡትን የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠቃለው ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ የምንኖርበት ዘመን ክርስትያኖች ከክርስቶስ ጋር የተቆራኙ በእምነት የሚያድጉ ከመጽሓፍ ቅዱስና ከቅዱሳት ምሥጢራት ጋር ሱታፌ ያላቸው መሆንን ይጠይቃል። ክርስትያን በመንፈስ ቅዱስ ያለው አዲስ ሕይወት የእግዚአብሔር ኅላዌ በጉዞአችን የሚደግፈን ፍጻሜ ለሌለው ሕይወት ክፍት የሚያደርግ ግልጽ ተራኪ መጽሐፍ መሆን ይጠበቅብናል በማለት በጣልያንኛ ቋንቋ የለገሱት የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ በአበይት ዓለም አቀፋዊ ቋንቋዎች አጠር በማድረግ ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.