2012-10-25 09:57:13

ስድስት ኣዲስ ካርዲናሎች ይሾማሉ


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ካቀረቡ በኋላ እ.አ.አ እፊታችን ኅዳር 24 ቀን 2012 ዓም በክርስቶስ ንጉሥ በዓል ዋዜማ በሚደረገው የካርዲናሎች ጉባኤ 6 ኣዲስ ካርዲናሎች እንደሚሾሙ ገልጠዋል።
ኣዲስ ካርዲናሎቹ ከሶስት የተለያዩ ክፍለ ዓለማት የተመረጡ ናቸው። ከኣመሪካ ከኣፍሪቃና ከኤስያ ሲሆኑ የቤተ ር.ሊ.ጳ ኃላፊ ብፁዕ ኣቡነ ማይክል ሃርቨይ ናቸው፡ ቅዱስነታቸው እንደገለፁት ብፁዕነታቸውን የቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ ፎሪ ለ ሙራ ሊቀ ካህናት እንዲሆኑ ሁሌ በልባቸው እንደነበርና ብፁዕ ኣቡነ ማይክል ካርዲናል ሲሾሙ የዚሁ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት እንደሚሆኑ ነው። ሁለተኛው የሊባኖስ ማሮናዊት ቤተ ክርስትያን የኣንፆክያ ፓትርያርቅ ብፁዕ ወቅዱስ ኣቡነ በሻራ ቡጥሮስ ራይ ናቸው። ሶስተኛ የህንድ ኣገር የሲሮ ማላንካረዚ ትሪቫንድሩም ልሂቅ ሊቀ ጳጳስ የሆኑ ብፁዕ ኣቡነ ባሲልዮስ ክሊሚስ ቶቱንካል ናቸው። ኣራተኛ ከናይጀርያ የኣቡጃ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ጆን ኦሎሩፈሚ ኦናየካን ናቸው። ኣምስተኛ ከኮሎምብያ የቦጎታ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ሩበን ሳላዛር ጎመዝ ናቸው። በመጨረም ስድስተኛው ከፊሊፕንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ልዊ ኣንቶንዮ ታግል ናቸው።
ቅዱስነታቸው የካርዲናሎቹ ዋና ስራ ሲገልፁ @ካርዲናሎች የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሆነውን ር.ሊ.ጳ ወንድሞቼ በእምነት የማፅናናት ተልእኮውና የቤተ ክርስትያን ኣንድነትና ሱታፌ ምንጭና መሰረት ለመሆን በሚያደርገው ጥረት እንዲረዱት ነው።@ ብለዋል። ስድስቱ ኣዲስ ካርዲናሎች ተልእኮኣቸውን በተለያዩ የቅድስት መንበር ኣገልግሎት እያደረጉ ናቸው ከፊሎቹም በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ ኣብያተ ክርስትያን ኣባታዊ ኖላዊ ኣገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ገልጠዋል።
የተልእኮው ክብደትን እግምት ውስጥ በማስገባትም ሁላችን በፀሎት እንድናስባቸው እንዲህ ሲሉ ተማጥነዋል። “ሁላችሁን ለተመረጡት ኣዲስ ካርዲናሎች እንድትፀልዩ እማጠናለሁ። በተለይ የብፅዕት እመቤታችን ድንግል ማርያም እናታዊ ኣማላጅነት እንዳይለያቸው በዚህም ሁሌ ለክርስቶስና ለቤተክርትያኑ በብርታት እንዲያፈቅሩና ሁለመናቸውንም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስትያኑ ኣገልግሎት እንዲያውሉ ይችላሉ። ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.