2012-10-24 12:32:36

ሲኖዶስ; 57 አንቀጾች የያዘ የመጀመርያው ረቂቅ ጽሑፍ


ስለ አዲስ ስብከተ ወንጌል የሚወያይ በሃገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው 13ኛው መደበኛ አጠቃላይ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በትናንትና ዉለው ባለፉት ቀናት በዝግ ዉⶀአቸው ያዘጋጁት 57 አንቀጾች የያዘ የመጀመርያው ረቂቅ ጽሑፍ ላይ ተወያየ፣ ይህ ረቂቅ ጽሑፍ በጉባኤው ከተጠናና ከተመረመረ በኋላ እፊታችን ቅዳሜ አበው ለእያንዳንዱ አንቀጽ ድምጻቸውን እንዲሰጡለት ለአበው ይቀርባል፣ አበው ካጸደቁት በኋላ ለር.ሊ.ጳ ይተላለፋል፣ ቅዱስነታቸው ደግሞ የሚጨመር ካለ ጨምረው የሚቀር ካለ አስቀርተው ድኅረ ሲኖዶሳዊ ቃለ ምዕዳን ያቀርባሉ፣
የሲኖዶሱ አባቶች ሁሌ እንደሚያደርጉት በትናንትናም ቅዱስነታቸው የመሩት ጸሎተ ስብሐተ ነግህ ካሳረጉ በኋላ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ቅዱስነታቸውንና የሲኖዶስ አባቶችን ወክለው አጋርነታቸውንና ትብብራቸው በጭንቅ ለሚገኘው ለሲርያ ሕዝብ ለመግለጽ የሚላከው ቡድን ሲኖዶሱ ከመጨርሹ በፊት የሚሄዱ አይመስልም ሲሉ ከገለጡ በኋላ በዕለቱ ቅዱስነታቸውን ወክለው የሲኖዶሱ ሊቀ መንበር ሆነው የሚመሩ ብፁዕ ካርዲናል ሞንሰንጎ እንደሆኑና በጉባኤው 258 አበው እንደተሳተፉ ያመለከቱ የሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ኤተሮቪች በአባቶች ስም ለዲሞክራስያዊ ኮንጎ ጳጳሳትና ምእመናን ቅርበታቸውን ገልጠው ባለፉት ቀናት በዓማጽያን የታገቱትን ሶስት ሚስዮናውያን አለምንም ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፣ የሲኖዶሱ አባቶች በኮንጎ ረኪበ ጳጳሳት የተላለፈውን ጥሪ እንደሚደግፉና ድምጻቸውም ከጳጳሳቱ ድምጽ እንደሚጨምሩ ገልጠዋል፣
የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የሲኖዶስ አባቶች ሥራ ውጤት የሆነው ረቂቅ ጽሑፍ ለአባቶች አቅርበዋል፣ ረቂቁ በመጀመርያ 326 አንቀጾች እንደቀረቡ ሆኖም አባቶች በጥንቃቄ መርምረው ወደ 57 አንቀጾች እንደጨመቅዋቸው ከገለጡ በኋላ የሲኖዶሱ አፈጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ውርል እና የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ካረ አንቀጾቹን ለሲኖዶሱ አባላት አንድ በአንድ በላቲን አንብበዋል፣ በአጠቃላይ እነኚህ አንቀጾች በአራት ምዕራፎች ተከፋፍለዋል፣ አንደኛው ክፍል ስለ አዲስ ስብከተ ወንጌል ባህርይ ሁለተኛው ያለው የቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ሶስተኛ ለዘመናችን ሁኔታዎች የሚሰጡ ግብረ ተልእኮአዊ መልሶች በመጨረሻም የአዲስ ስብከተ ወንጌል አስፈጻሚዎች ወይም ተካፋዮች የሚሉ ምዕራፎች ናቸው፣
የረቂቅ ሰነዱ አንቀጾች ከሚያመልክታቸው ዋና ዋና ችግሮች ዓለማውነት በብዙ ጉዳዮች የሚያደርገው ጫና በሃይማኖት ነጻነት በሰው ልጅ መብት በስደተኞች በቤተ ክርስትያን ኅብረተሰብ አዊ ትምህርት በድሆች እርዳታ በትምህርተ ክርስቶስ በገዳማዊ ሕይወት በቤተ ሰብ በቤተ ክህነት በእምነትና አመክንዮ በሚደረግ ድርድር በወጣቶች በውስጠ ሃይማኖታዊ ውይይትና በክርስትያን አንድነት ላይ ብርቱ ጫና እያደረገ ነው፣
የተለያዩ አስተያየቶችና ውይይቶች ከተካሄዱ በኋላ የሲኖዶሱ አባቶች ይህንን ረቂቅ ሰነድ አጣርቶ የሚያቀርብ ምክር ቤት መርጠዋል፣ የምክር ቤቱ አባቶች ከሶስት ክፍለዓለማት የተመረጡ ሲሆን ከአፍሪቃ ብፁዓን ካርዲናሎች ናፔር ተርክሰንና ሞንስወንጎ ፓሲንያ፤ ከአመሪካ ብፁዓን ካርዲናሎች ዶላን ሸረር እና ብፁዕ አቡነ ሲልቫ ረታማለስ፤ ከኤስያና ከኦሻንያ ብፁዓን ካርዲናሎች ግራስያስ ፐል እና ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ታግል፤ ከኤውሮጳ ብፁ ዓን ካርዲናሎች ሾንቦርን ኤርዶ እና ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ፎርተ ተመርጠዋል፣ በትናንትና ጉባኤ ፍጻሜ ላይ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ቅዱስ አባታችን ለእያንዳንዱ የሲኖዶስ አባት ከብር የተሰራ የአንገት መስቀል ገጸ በረከት እንደሚሰጡ መስቀሉም የሲኖዶሱ ማስታውሻ ሆኖ የሲኖዶሱ መኽፈቻና መዝጊያ ቀኖች የተቀረጹበት ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.