2012-10-22 16:12:03

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “አዲስ አስፍሆተ ወንጌልና ቅድስና”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማሕተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ዲስ አስፍሆተ ወንጌልና ቅድስና” በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል በአገረ ቫቲካን “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት” በሚል RealAudioMP3 ርእስ ተሸኝቶ በመካሄድ ላይ ያለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ፣ ጥልቅና ሰፊ ብሎም ዓቢይ ኃላፊነት የጎላበት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ጠቅሰው፣ ያለፉት የሲኖዶስ ውሎዎች ጽማሬ ትላትና እሁድ ቅዱስ አባታችን የፈጸሙት የቅድስና አዋጅ መሆኑም ገልጠው፣ ቅዱሳን ሰብእዊነትን ቦግ የሚያደርገው የእምነት ብርሃንና ደስታ የሚያስተጋቡ ናቸው፣ እነዚህ በቤተ ክርስትያን ቅድስና የታወጀላቸው ካህናት ምእመናን ደናግል ዓለማውያን ምእመናን የሚገኙባቸው ሰባቱ የቤተ ክርስትያን ልጆች አፍሪካን ሁለቱ አመሪካዎችን ኦቻይና እስያን ኤውሮጳን የሚወክሉ መሆናቸው አባል ሎምባርዲ በማስታወስ የኢየሱሳውያን ማህበር አባል አባ ጃኮሞ በርዚዩ፣ ዓለማዊ ምእመን ፓውሎ ካሊንግሶድ፣ አባ ጆቫኒ ባቲስታ ፒያማርታ፣ እናቴ ማሪያድ ደል ሞተ ካርመሎ፣ እናቴ ማሪያ አና ኮፐን፣ ዓለማዊት ምእመን ካተሪና ተካክዊታንና፣ አና ሻውፈርን መሆናቸውም ገልጠው፣ ቅዱሳኖች የክርስትና እምነት ተስፋ አብሳሪያን የእምነት ታማኝነት በቃልና በሕይወት ምስክሮች ናቸው። ስለዚህ ሕይወት የሚለውጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ሞትን አሸንፎ የተነሣው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች ናቸው። አለ ቅዱሳኖች የአስፍሆተ ወንጌል ቀናተኛነትና እምነትን በኃሴት የመመስከሩ ስሜት ባልኖረ ነበር ስለዚህ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ከነዚህ የወቅቱ ቅዱሳን ሕይወት አብነት እንጀምር በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.