2012-10-22 16:05:43

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እግዚአብሔር ለወቅቱ ሰው የሚያቀርቡ ሰዎች አስፈላጊነት


ቅዳሜ ጧት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በስማቸው የሚጠራው በየዓመቱ እምነትንና ሥነ ምርምር ባጣመረ ጥበብ አቢይ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የሚሰጠው የራትዚንገር ሽልማት ለበቁት በቲዮሎጊያ የትምህርት ዘርፍ ለቲዮሎጊያ ሊቅ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ተወላጅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የቲዮሎጊያ RealAudioMP3 ሥነ ታሪክ መምህር ፕሮፈሰር አባ ብሪያን ዳለይና የፍልስፍናና የሥነ ሃይማኖት ፍልስፍና ሊቅ ለፈርንሳዊው ፕሮፈሰር ረሚ ብራገ ሽልማቱ መስጠታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዝጠኛ በነደታ ካፐሊ እንደገለጡትም፣ በዚህ በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አበው የወከሉት ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በተካሄደው የራትዚንገር የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ንግግር፦ “ለወቅታዊው ሰው እግዚአብሔርን ለማቅረብ የሚተጉ ሰዎች መኖር ምንኛ አስፈላጊ ነው” እንዳሉ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው ሁለቱ የራትንዚንገር ሽልማት ተሸላሚዎች በቤተ ርክስትያን በየጥሪያውቸውና እንዲሁም ባላቸው ሊቅነት ንቁ ሲታፌ በመኖር፦ “ለአቢያተ ክርስትያን አንድነት ታልሞ ለሚደረገው ውይይት አቢይ አስተዋጽዖ የሰጡና በመስጠት ላይ መሆናቸውም” ይኽ ደግሞ “ከአይሁድና ከምስልምና ሃይማኖት ጋር ለሚደረገው የጋራው ውይይት፣ ቤተ ክርስትያን ከሌሎች ሃይማኖትና እንዲሁም ከተለያዩት አቢያተ ክርስትያን ጋር የምታደረገው ውይይት የሚከተለው መንገድ የሚያመልከት ነው” እንዳሉ ካፐሊ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ሽልማቱን በመስጠትና የሁለቱ ሊቃውንት ማአክላዊው ሥራ በመጥቀስ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነዶች በተለይ ደግሞ ካቶሊክዊት ቤተ ክርስትያን ክርስትያን ካልሆኑት ሃይማኖቶች ጋር ለምታደረገው ውይይት መሠረት የሆነው Nostra aetate- ያለንበት ዘመን የተሰኘው፣ Unitatis redintegratio- ኅብረተ ክርስትያን ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ጋር ለሚደረገው ውይይት መሰረት የሆነውና ስለ ሃይማኖት ነጻነት እርሱም Dignitatis humanae-ሰብአዊ ክብር የተሰኙት ውሳኔዎች ዳግም ለማንበብ አወንታዊ ግፊት መሆኑ ማብራራታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ገልጠው፣ “ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ከሌሎች ሃይማኖትና ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ጋር የምታደረገው ውይይት በተመለከተ የሁለቱ ፕሮፈሰሮች አስተንትኖና አስተምህሮ ማዳመጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይኽ ደግሞ ቤተ ክርስትያን ከወቅታዊው ዓለም ጋር የምታደርገው ግኑንኘትና ውይይት በምንና እምን ላይ የጸና መሆኑ የሁለቱ ሊቃውንት ሥራ የሚያሰምርበትና የሚያብራራው ብቻ ሳይሆን፣ ሥርዓት ባለው አገባብ የሚያሳውቅ ነው” ብለዋል።
“እውቀት ማካፈል ጥበብ ማስተላለፍ መሆን እንዳለበት” ያብራሩት ቅዱስ አባታችን አክለውም ለዚህ አብነትም የሁለቱ ሊቃውንት ሥራ የሚመሰክረውና ቀለል ባለ መንገድ ሆኖም ቅዉም ነገሩን ላላ ካለ ማድረግ ያለው ጥልቅ መልእክቱን ካለ ማዛባት እየሰጡት ላለው አስተዋጽኦ አድንቀው፣ ጠንካራ ሥነ ምርምር የተካነው ሥራቸው ለሰው ልጅ ያላቸው አሳቢነት የሰው ልጅ ትክክለኛውና እውነተኛው የመኖር ጥበብ ወይንም ዘይቤ እንዲከተል ለማድረግ ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ አስታወቁ።
“በሥነ እውቀት ጥበብ የተካነና የሚኖር እምነት አማካኝነት እግዚአብሔር ለወቅቱ ዓለምና ሕዝብ ቅርብ ለማድረግ ብሎም የእምነት ታማኝነት ለማሳቅ የሚያደርጉት የሥነ ምርምር ጥረት አስፈላጊ ነው፣ ሁሉም ሰብአዊ ፍጡር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳ በተጠራበት ጥሪ አማካኝነት በሚሰጠው አገልግሎት የሰው ልጅ የመኖሩ ዘይቤ ለማስታዋል የሚያግዝ መሆኑና ይኸንን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሚያበክረው ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ለማረጋገጥ ከምን ግዜም በበለጠ ያለው አንገብጋቢነት የሚጠቁም ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐል ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.