2012-10-22 16:01:02

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አዲሶች ቅዱሳን ለሰው ልጅና ለወንጌል አገልግሎ አብነት፣ ለሲኖዶስና ለልኡካነ ወንጌል ማበረታታቻ ናቸው


በቅድስት ቤተ ክርስትያን ትላትና በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለተለያዩ የስድስት አገር ዜጎች ለሆኑት ለሰባት የቤተ ክርስትያን ልጆች በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅድስና የታወላቸው ሲሆን፣ የቅድስናው ይፋዊ አዋጅ ለየት የሚያደርገው RealAudioMP3 የተገባው “የእምነት ዓመት በአገረ ቫቲካን አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ያለው የመላ ካቶሊካዊት ቤት ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የተልእኮ ወንጌል ቀን የሚታሰብበት ዕለት መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ ከውጭና ከውስጥ በጠቅላላ ከሰማንያ ሺሕ በላይ የሚገመት ምእመን በተሳተፈበት ለጃኮሞ በርቲየው፣ ለፔርትሮ ካሉንግሶድ ለጆቫኒ ባቲስታ ፒያማርታ፣ ለማሪያ ካርመን ሱለስ ይ ባራንጉወራስ፣ ለማሪያና ኮፐ ለካተሪና ታካክዊዛና ለአና ሻፈር ቅድስና ለማወጅ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ስብከት፦ በቅድምያ ከተለያዩ አገሮች የመጡት ይፋዊ ልኡካን ምእመናን ቅዱሳኖቹን ለማክበር የመጡት መንፈሳውያን ነጋድያን እንዲሁም እዚህ በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት በሚል ርእስ ተመርቶ በመካሄድ ላይ ባለው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ተሳታፊዎች ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳትን ሰላምታን አቅርበው፣ የቅድስናው አዋጅ በሰንበት ዓለም አቀፍ የተልእኮ ወንጌል ቀን፣ የሲኖዶስና የእምነት ዓመት በተገባበት ወቅት የሚታወጅ በመሆኑ ያለው ክብር እጥፍ ድርብ ነው ሲሉ፦ በቤተ ክርስትያ ዘወትር የቅድስና ምንጭ የድህነት ምሥጢርርሱም ቅዱስና ጻድቅ የጌታ አገልጋይ ‘….ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል…. (ኢሳ. 53 ቍ. 11’ በማለት ነቢይ ኢሳያስ የሚገልጠው ተሰቅሎ ሞትን አሸንፎ የተነሳው በግርማ ሞገሱ ህያው የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ካሉ በኋላ እ.ኤ.አ በ 1883 ዓ.ም. በፈረንሳይ የተወለደው የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በማጋዳስካር በአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ላይ እያለ የደም ሰማዕትነት የተቀበለው አባ ቅዱስ ዣከስ በርተዩን ጠቅሰው የዚህ ልኡከ ወንጌል ሕይወትና አገልግሎት ካህናት የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲሆኑ ለመጠራታቸውና ስለ እምነታቸው ለሚሰደዱት ምእመናን ሁሉ አብነት ነው። በዚህ በተገባው የእምነት ዓመት በእርሱ አማላጅነት ለማዳጋስካር የተትረፈረፈ ጸጋን ተማጠው እግዚአብሔር የማዳጋስካርን ሕዝብ ይባርክ” እንዳሉ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንሳ አስታወቁ።
እ.ኤ.አ. በ 1600 ዓመታት አጋማሽ የኖረው የፊሊፒንስ ዜጋ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪ ፐድሮ ካሉንግሶድ ስለ እምነቱ በተሰነዘረበት የሐሰት ነቀፌታ የደም ሰማዕትነት የከፈለ የጥልቅ እምነትና የሚሰዋ ፍቅር አብነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጠቅሰው፦ የፐድሮ ካሉንግሶድ አብነት የፊሊፒንስ በጽናትና ሕይወታቸውንም ለእግዚአብሔር ለማቅረብ በሚደግፍ ንቃት ሕዝቡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲያውጅ” አሳስበው፣ አባ ጆቫኒ ባቲስታ ፒያማርታ በኢጣሊያ ብረሺያ ሰበካ ካህን የነበረ የሚሰዋ ፍቅርና የወጣት ሐዋርያ በመሆን በቅድስና ሕይወት ያገለገለ መሆኑ ጠቅሰው፦ “በቅዱስ ቁርባን ፊት አስተንታኝ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት ትንሳኤው ላይ መላ መንፈሳዊ ክህነታዊ ሕይወቱን እንዲያተኵር በማድርግ የሚሰዋ ፍቅር መስካሪ የወጣቶች ሐዋርያ በመሆን ለወጣት ትውልድ ያነጣጠረ አዲስ ሐዋርያዊ ግብረ ኖውሎ ያነቃቃ” በማለት ከገለጡት በኋላ በስፐይን እ.ኤ.አ. በ 1848 ዓ.ም. የተወለደች እናቴ ቅድስት ማሪያ ደል ካርመሎ ሳልየስ ይ ባራንጉወራ ጠቅሰው፦ “የሕንጸት አገልግሎታቸው ለንጽሕት ድንግል ማርያም በማማጠን በወጣቶችና እሳቸው በመሠረቱት የደናግል ማኅበር ዘንድ ፍርያማነቱን በማረጋገጥ እንደ ማርያም ሁሉን በእግዚአብሔር እጅ መተው ለሚለው እምነት አብነት ናቸው” እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንሳ አክለውም፦ እ.ኤ.አ. በ 1838 ዓ.ም. በጀርመን ሄፐንሃይም ከተማ የተወለደችው እናቴ ማሪያ ኮፐ፦ ምንም’ኳ የአልጋ ቁራኛ ብትሆንም በጽናትና በቁርጠኝነት በላቀው ተስፈኛ ሕይወት የበለጠው የካቶሊክ ባህል በቃልና በሕይወት በማጉላት በቅዱስ ፍራንቸስኮስ አብነት የማኅበሩ ደናግልን በማጽናትና በመንደገፍ የኖረ ሕይወትና የቅድስና አብነት ነች” ቀጥለውም በኔው ዮርክ በ1656 ዓ.ም. የተወለደችው ቅድስት ካተሪ ተካክዊዛ፦ “በብርቱ እምነትና በባህሏ አማካኝነት የጥሪ አብነት ሆነው የኖረቸው ሕይወት በተወለደችበት ሕዝብና ባህል መካከል ተኩኖ ለሚኖር ክርስትናና ቅድስና አብነት ነች፣ ይህች የካናዳ ጠባቂ ቅድስት የአመሪካ ቀደምት ተወላጅ ጎሳ አባል በመላ አመሪካዎች እምነት እንዲያብብ ታማልድልን በማለት እግዚአብሔር ቀደምት አገሮችን ክፍለ ኅብረሰብ ይባርክ” እንዳሉ ጋዜጠኛ ስፐራንሳ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ በጀርመን የተወደች ቅድስት አና ሻፈር “ባጋጠማት አደጋ ለአልጋ ቁራኛነትት ተጋልጣ ስቃይዋ ወደ እግዚአብሔር እንደ ሚቀርብ መሥዋዕት ካለ ምንም ቅሬታ በመኖር የታማኝነት አብነት በመሆን፣ የእሷ አብነት ገና መድሃኒት ባልተገኘለት ሕመም የተጠቁት በሚኖሩበት ህክምና ቤት ለሚሰጠው አገልግሎት ለታመሙትና ለአስታማሚዎች ሁሉ አብነት ነች” ካሉ በኋላ፣ እነዚህ አዲሶች ቅዱሳን የተለያየ ሕዝብ ባህልና ቋንቋ የሚወክሉ የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ባህርይ መስካሪያን የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ለሁሉም ሰው ዘረ መሆኑ የሚያረጋግጡ ናቸው እንዳሉ የገለጡት ጋዜጠኛ ስፐራንሳ፣ ቅዱስ አባታችን እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት አስተምህሮ፦ “የሁሉም ቅዱሳን ንግሥት የሆነቸው ቅድስት ድንግል ማርያም በመማጠን በጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የተጠቃው በተለይ ደግሞ ግልጸተ ማርያም ዘ ሉርድ ዋሻ በማሰብ ለዚህ አደጋ የተጋለጠው የሉርድ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ እናስብ” ባሉት የጸሎት ሃሳብ ላይ በማተኮር እንዲሁም በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ መላ ውሉደ ክህነት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የተሰማሩት ለቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ ተማጽነው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው፣ በቅዳሴው ሥነ ሥርዓትና በጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ለተሳተፉት ለፊሊፒንስ ምክትል ርእሰ ብሔር ጀዮማር ቢናይ፣ ለካናዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር አንደረው ሺር ለጀርመን የባቪየራ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ ባርባራ ሳም በቅድስት መንበር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ሚገል ዲያዝና ሌሎች አበይት ተወካዮችን በጠቅላላ ምእመናን ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ መለገሳቸው አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.