2012-10-22 16:09:36

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ሲስታች፦ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የፍቅር ቋንቋ የሚናገር ሊሆን ይገባዋል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳመለከቱት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለየት ባለ መልኩ ምሥጢረ ጥምቀት ለተቀበሉት ነገር ግን ከቤተ ክርስትያን በተለያየ ምክንያት ርቀው ለሚገኙት ያነጣጠረ መሆኑ ማስታወሳቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የባርቸሎና ሊቀ ጳጳሳት RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ልዪስ ማርቲነስ ሲስትች ገልጠው፣ “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚገለገልበት ቋንቋ ፍቅር መሆን አለበት” ብለዋል።
በዚህ የክርስትና እምነት በተቀበሉት ጥንታውያን ክርስትያን አገሮች የሚታየው የእምንት መዛል በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ሱታፌ በዛለበትና በጠቅላላ ከቤተ ክርስትያን መራቅ በሚታይበት ክልል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ማበሰር ማለትም የራቀው በገዛ እራሱ እስኪመለስ መጠበቅ ሳይሆን ወደ እርሱ ቀርቦና ወደ እርሱ በመሄድ በአዲስ ቋንቋና ስልት ማበሠረት ያስፈልጋል። በዚህ እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ ማሰቡን ተለማምዶ በመኖር ላይ የሚገኘው ሰው፣ ሰብአዊ ፍጡር ለእግዚአብሔር ያቀና መሆኑ ያለው መንፈሳዊ ባህርዩ ሊከዳ አይችልም ስለዚህ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ተቀርጾ ያለው የእግዚአብሔር ህላዌ ለማዳመጥ እንዲችል በፍቅር ቀርቦ በፍቅር ቋንቋ መናገር መቻል ነው። ብለዋል።
“አዲስ አስፍሆተ ወንጌል፣ ክርስቶስን ከሁሉም በላይ አብልጠን የምናፈቅር መሆናችን እርሱ ስለኛ ብሎ ገዛ እራሱን አሳልፎ መስጠቱን ቤዛነቱን ከሞት መነሣቱን የሚያጎላ ሕይወት መኖርን ይጠይቃል፣ አስፍሆተ ወንጌል ማለትም ይኽ ነው። ያፈቀርነው ቀድመን የተፍቀርን መሆናችን ያረጋገጠልን ክርስቶስ ማቅረብ ማለት ነው። በሁለተኛ ደረጃም ሌሎችን እንደ ገዛ እራስህ አፍቅር የሚለው ትእዛዝ የሚያኖር መሆን አለበት፣ ለክርስቶስ ያለን ፍቅር መመዘኛው ለወንድማችን የምንገልጠው ፍቅር ነው፣ ስፍሆተ ወንጌል ለክርስቶስና ለወንድሞቻችን ያለን ፍቅር የሚመሰክር መሆን አለበት ከዚህ ውጭ አስፍሆተ ወንጌል ብሎ ለመናገረ አይቻልም” ብለዋል።
የኤኮኖሚና የባህል ቀውስ የሰው ልጅ ምንኛ በገዛ እራስ ተምሳይ ፍቅር ላይ ብቻ ታጥሮ ፍቅር ግለኝነትን እኔነትን በሚለው ትርጉም ቀይሮ ለመኖር የሚከተለው ሕይወት የጋረጠው አቢይ ችግር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ብፁነታቸው ይከንን በማስታወስም “ተከስቶ ያለው ዘረፈ ብዙ ቀውስ ወዴት እየመራን ነው? አለ ሥርዓትና ደንብ ሁሉ እንዳሻኝ የሚለው ልቅ አኗኗር በመኖር የተያይዘው ምርጫ ያጋባው ቀውስ ነው። አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ይኸንን ግምት የሰጠና በዚህ ደረጃና ሁኔታ ላይ ከሚገኘው ሰው ጋር መነጋገርና ለዚህ ሕዝብ ወንጌል ማበሰር ማለት ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይም አስፍሆተ ወንጌል አቢይ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የተሟላ ዝግጅትና ሕንጸት ጸሎት የሚጠይቅ መሆኑ ለመረዳቱ አያዳግትም” ብለዋል።
አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በቅዱሳት ምሥጢራት ላይ የጸና ሥነ ሰብእ ዳግም ማነቃቃት የሚጠይቅ መሆኑም ያብራሩት ብፁዕ ካርዲናል ሲስታች የእግዚአብሔር መኅሪነት የሚያጎላ መሆን አለበት ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.