2012-10-19 14:03:52

ሲኖዶስ፦ “Relatio post disceptationem - ዘገባ ድኅረ ውይይት”


ቁምስናዎች የዓለማውያን ምእመናን የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ሚናና የካህናት አገልግሎት የተለያዩ የመንፈሳዊ ንገደት ማስፈጸሚያ ቅዱሳን ሥፍራዎች በሚሉት ርእሶች በትላንትና ውሎው የተወያዩት የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሲኖዶስ አበው በንኡሳን ቡድን በመከፋፈል ውይይት ማካሄዳቸው RealAudioMP3 ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ የኪየቭና ሃልች በኡክራይን የግሪክ ስርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ መሪ አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ስቪያቶስላቭ ስኬቭቹክ፦ “ቤተ ክርስትይን በጠቅላላ በተለያዩ አገሮች በሚገኙት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ኅብረት ያላቸው ብፁዓን ጳጳሳት አማካኝነት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አማክኝነት ለቀረበላቸው ጥሪ በመታዘዝ በእሳቸው ዙሪያ በመገናኘት የወቅታዊው አለም ተጋርጦ ለማንበብና በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አማካኝነት ለመወጣትና ለዚህ የሚያነቃቃውም የእምነት ዓመት ያለው ምሉእ ትርጉም ለመገንዘብ የሚያበቃ ወቅት ነው” ሲሉ፦ የኪንሻሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞሰንግዎ ፓዚኒያ በበኩላቸውም “በዚህ በአሁኑ ወቅት ኢአማኒ የሆነው ስለ እግዚአብሔር በተመለከተ ጥያቄ ያማያቀርብ ያቀረበም እንደሆነ ጥያቄው አዛብቶ ለሚያቀርብ ዓለም ስለ እግዚአብሔር ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመናገር እንዴት ይቻላልን” በሚለው ጥያቄ ላይ ያነጣጠረ ንግግር ለሲኖዶሱ ማስደመጣቸውም ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አመልክተው በመቀጠልም የበስሎቫኪያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የቢዛንታይን ሥርዓት ለምትከተለው የፕረሶቭ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዣን ባብጃክ ባሰሙት ንግግር፦ መንፈሳዊ ንግደት በሚፈጸምባቸው ቅዱሳን ሥፍራዎች ዘንድ የሚታየው የካህነት እጥረት ግምት በመስጠት በነዚህ ቅዱሳን ሥፍራዎች የካህናት ኅላዌ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። መንፈሳዊ ንገደት የሚፈጸምባቸው ቅዱሳን ሥፍራዎች የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን” ሲያመለክቱ፣ የሎስ አንጀሎስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ሆራሲዮ ጎመዝ፦ እንዲህ ባለ ጉባኤ ሲሳተፉ ለመጀመሪያ ጊዜያቸው በመሆኑ የተሰማቸው ጥልቅ ኃሴት በማስተጋባት፣ በኩላዊት ቤተ ክርስትያን የዓለማውያን ምእመናን ሚና ላይ ያተኮረ ንግግር ሲያስደምጡ፣ በመክሲኮ የጓዳላኻራ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሲስኮ ሮበለስ ኦርተጋ በበኩላቸውም፦ በቤተ ክርስትያን በመወለድ ላይ የሚገኙት ቁጥራቸው ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያሉት የተለያዩ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ማእከል በማድረግ፦ “እነዚህ የሚወለዱት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በተገባ ለማወቅና የአገልግሎታቸው ዓላማና ማእከል ለመለየት እንዲቻል ደንብና ሥርዓት ያስፈልጋል፣ ብፁዓን ጳጳሳት የነዚህ ማኅበራት መወለድ የሚቃወሙ አይደሉም፣ ሆኖም አንዳንዶቹ ከሚሰጣቸው መመሪያ ውጭ ሊሆኑና ሊኖሩት የሚሹትን ውሳኔ እንደ ምክር ሳይሆን ድፍን ባለ አነጋገር በጳጳሳት ላይ ጫና በማድረግ ለማቅረብ ሲቃጣቸው ይታያል፣ ስለዚህ ቀርቦ መከታተልና መቆጣጠር ለሁሉም የሚበጅ ነው” በማለት የእውነትኛ የእምነት ውበት ለመመስከርና ጉልህ ሆኖ እንዲታይም የወቅታዊው ዓለም ተጋርጦ አበጥሮ በመለየት በቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስትይን ጋር በመሆን መፍትሔ ማቅረብ የሚለው መሠረታዊ ሃሳብ ብፁዓን አበው ባሰሙት ንግግር ያሰመሩበት ነጥብ መሆኑ ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.