Home Archivio
2012-10-19 14:06:54
ሲኖዶስ፦ ቁምስናዎች የሚደነቅ ኃይል አላቸው ሆኖም ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዳግም መነቃቃት ይኖርባቸዋል።
የቁስምናዎች የአስፍሆተ ወንጌል ዓለም አቀፍ የአገልግሎት ማእከል ሊቀ መንበር አባ ፒየርጆርጆ ፐሪኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የብፁዓን አበው ሲኖዶስ፦ ቁምስናዎች የመንፈሳዊ ንግደት ቅዱሳን ሥፍራዎች ለአስፍሆተ ወንጌል አመችና ተቀዳሚ ናቸው በማለት እንዳሰመሩበት ጠቅሰው።
በሲኖዶስ ከቀረቡት ከተለያዩ ክፍል ከተሰጡት ምስክርነቶች ለአስፍሆተ ወንጌል እንቅፋት የሆኑት ከውስጥና ከውጭ የሚሰነዘሩት መሰናክሎች ለመለየት ተችለዋል። መሰናክሎች የሚታወቁ ቢሆንም ቅሉ እንደ ቤተ ክርስትያን በተለይ ደግሞ ቤተ ክርስትያን በኵላዊነት ባህርይዋ ሥር በመመልከት ኵላዊ መፍትሄ ማቅረብ ወሳኝ በመሆኑ ይኸንን ግምት በመሰጠት በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዙሪያ እንዲወያይ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የተጠራው የብጹዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ ጸጋ ነው። ስለዚህ በእክሎች ተዳክሞ እጅ ሰጥት መሸነፍ እንዳያጋጥም ለቅዱስ መንፈስ ሥፍራ በመስጠት እንዲያድስና እንዲለውጥ በመፍቀድ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በፊትም ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እንዳሉት መንፈስ ቅዱስ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መሠረት ነው። አለ መንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ንፋስን በዱላ መምታይ ይሆናል ስለዚህ አለ መንፈስ ቅዱስ ምንም ነገር ለመገንባት አይቻልም፣ ሁሉንም ለማደስ ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል።
ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ዋና ተወናያን ቁምስናዎች ናቸው። ስለዚህ የምእመናን በቁምስና ሱታፌ ማበረታታት፣ በቁምስናዎች መካከል ግኑኝነት መፍጠር፣ ሁሉም በጥሪው አማካኝነት በማገልገል በቤተ ክርስትያን ግንባታና በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማገልገል ከካህናት ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ውህደት ማረጋገጥ አለበት፣ ስለዚህ ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ኅብረት ግድ ነው። ከዚህ ኅብረት ውጭ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማርጋገጥ አይቻልም በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.