2012-10-19 14:00:22

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ወኤርል፦ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለሁሉም የእምነት ኅዳሴ ቁርጠኝነት


በሃገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው 13ኛው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በተዋጣለት ሁኔታ እየቀጠለ ሲሆን፣ ትላትና በተካሄደው ዝግ ውሎው የሲኖዶሱ የፍጻሜ ሰነድ ለማዘጋጀት ላይ ያተኮረ እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኢሳበላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ትላትና ከሰዓት RealAudioMP3 በኋላ የሲኖዶስ አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ዶናልድ ወኤርል፦ “Relatio post disceptationem - ዘገባ ድኅረ ውይይት” እስካሁድን ድረስ ሲኖዶሱ የተወያየባቸው ነጥቦች በመዳሰስ ዋና ዋና ርእሶች ላይ ያተኮረ የድኅረ ውይይት ሰነድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት ጉባኤ ያቀረቡ ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው እንዳመለከቱትም “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጊዚያዊ መርሃ ግብር ሳይሆን፣ የቤተ ክርስትያን መጻኢ የመመልከት ስልትና የሁሉም ለእምነት ኅዳሴ ቁርጠኝነት የሚጠቅይ ነው ምክንያቱም ብስራተ ወንጌል የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚ የተልእኮ ዓላማ ብቻ ሳይሆን የተልእኮዋ መለያ ነው” እንዳሉ ያመለከቱት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘውም፣ ብፁዕ ካርዲናል ወኤርል ለየት የሚያደርጋቸው ካለ ምንም ውስብስብ በቀጥታ ግልጽ በሆነ ስልት መግለጫ የማቅረቡ ብቃታቸው የጎላበት፣ በላቲን ቋንቋ ባቀረቡት የድህረ ውይይት ሰነድ፦ “የቤተ ክርስትያን የአገልግሎት ሥልጣን የእግዚአብሔር ቃል በዚህ ዓለማዊነት ትስስር በሙላት የገዛ እራሱ ተጋርጦ ይዞ በመረጋገጥ ላይ በሚገኝበት በተለይ ደግሞ ጥንታውያን ክርስትያን በሚባሉት አገሮች እምነት በተወራረስ የሚተላለፍ በመሆኑ ይኽ ባህል ያጋባው የእምነት ድንቁርና ለመቅረፍ በአዲስ አገባብና ይዘት ማቅረብ ወይንም ወንጌል ለማድረስ የምትከተለው ስልት የምትከልስበት ወቅት ነው። ስለዚህ ይኽ ሁነት ቤተ ክርስትያን የምታውጀውና አውን ለምታደርገው መንፈሳዊነት ኅዳሴ ያለው አንገብጋቢነት የሚጠቁም ነው” ብለዋል።
ስለዚህ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጥያቄ በማንሳት፣ ሲኖዶስ የተወያየባቸው አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮችና የሰጠባቸው አስተያየት ጽማሬውን ሲያቀርቡ፦ የምስልምና እምነት እጅግ በተስፋፋበት ክልል የሚታየው አመጽና የሃይማኖት ነጻነት እገዳ እንዲወገድ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ማነቃቃት፣ የአቢያተ ክርስትያን ለውህደት ታልሞ የሚከናወነው የጋራው ውይይት የሚከተለው ሥልት የሚጠቀምበት ቋንቋና የቤተ ክርስትያን የግኑኝነት ጥበብ ኅዳሴ እንደሚያሻው” ካመለከቱ በኋላ፣ “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በባህላዊ ረገድና በሰው ማኅበረሰብ እና ኅብረተሰብ መካከል ላለው ግኑኝነት የሚደቅነው ተጋርጦ አቢይ ነው። በዚሁ ረገድ ቤተ ክርስትያን ‘Cortile dei Gentili- የአህዛብ ቅጥር ግቢ መርሃ ግብር በማህበራዊ ፍትህ የትብብርና የድጋፍ እርሱም በሚሰዋ ፍቅር መሠረት የምትሰጠው አስተዋጽኦ ለመጥቀስ ይቻላል፣ ብለዋል።
ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማስተግበሪያ ይሆናሉ በማለት ሲኖዶስ ያቀረበው ዝርዝር ላይ በማተኮር ብፁዕነታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፦ “ቁምስናዎች ንኡሳን ማኅበረ ክርስትያን ትምህርት ቤቶች መናብርተ ጥበብ የመንፈሳዊ ንግደት ተግባሮችን፣ ትምህርተ ክርስቶስ በተመለከተ በቤተ ክርስትያን ውስጥ አንድ የገዛ እራሱ በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ላይ ያተኮረ ጽኑ የአገልግሎት ሥልጣን ማረጋገጥ፣ እምነት በማስተላለፉ ረገድ አቢይ ሚና ለሚጫወተ ቤተ ሰብ በምሥጢረ ተክሊል የጸናው ብዙ እክል እያጋጠመው ያለው ይህ የኅብረተሰብ ማእከልና ሴቶች በቤተ ክርስትያን ሕይወት እምነት በማስተላለፉ ተልእኮ መሠረት በመሆናቸውም መደገፍ ያለው አስፈላጊነት” ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ተወያይተውበታል።
በመቀጠልም ብፁዕነታቸ፦ “ካህናት መናንያን ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መተኪያ የሌላቸው የቤት ክርስትያን አገልጋዮች ናቸው በማለት፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ለጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ተልእኮ ቀጣይነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት መኖር የሚጠይቅ ሲሆን፣ ይኽ ደግሞ የንጽሕና ሕይወት የመኖሩ ውሳኔ የማያወላውል መንገድ ነው። አለማውያን ምእመናን በሁሉ የቤተ ክርስትያን መስክ ማሳተፍ ማለትም ዓለማውያን ምእመናን በቃልና በሕይወት የተሸኘ እምነት በማነቃቃት ረገድ የሚሰጠው አስተዋጽኦ ግምት መስጠተ ያለው አስፈላጊነት” ገልጠው በመጨረሻም ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ለሚያጠናቅሩት የፍጻሜ ሰነድ ለማዘጋጀት ፈር የሚያስይዝ 14 ጥያቄዎችን ዘርዝረው በማቅረብ፣ ቤተ ክርስትያን ውስጣዊና ውጫዊ እክሎች በተመለከተ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዳላትና፣ ይኽም ለአዲስ ፔንጠቆስጤ የእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ ለመኖርና ቃሉን በደስታ ለማካፈል አተኮር የምታደርግበት ወቅት ነው በማለት የሰጡት መግለጫ እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.