2012-10-17 14:43:06

ሲኖዶስ፦ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕትነት በአቢያተ ክርስትያን የክርስትና ሕይወት የሚያነቃቃና አምባ ገነናዊ አመለካከት ካስከተለው ባዶነት ነጻ የሚያወጣ ነው


በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ በትላንትና ውሎው የ20ኛው ክፍል ዘመን የእምነት ሰማዕታት የታደሰ ክርስትያናዊ ሕይወት የሚያንቃቃና አምባ ገነናዊ አመለካከት ለዘመናት ካስከተለው ባዶነት ነጻ የሚያወጣ መሆን እንደተሰመረበት ሲኖዶሱ የተከታተሉት RealAudioMP3 የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢሳበላ ፒሮ አስታውቀው፣ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. በርእደ መሬት አደጋ እጅግ ለተጠቃቸው ለአገረ ሐይቲ ድጋፍና ትብብር ጥሪ በማቅረብ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በዳግመ ግምባታው ሂደት በቀዳሚነት እንደምትገኝም መመስከሩንም ገልጠዋል።
በዓለማችን ተከስተው የነበሩት የኮሙኒዝም ሥርዓት ባስከተለው አምባ ገነናዊ ድርጊት እጅግ የተጎሳቆለችና ሰማዕነት የከፈለቸው ቤተ ክርስትያን በመጥቀስ፣ መንግሥት ሕዝብ አለ እግዚአብሔርና አለ ቤተ ክርስትያን በመሆን ባዶውን ሰብአዊነት ቃለ ተአምኖ በማኖር የተኖረው ባህል ዛሬም በሰው ልጅ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ለማንም ያልተሰወረ ነው። ይኽንን የተፈጠረው ሰብአዊ ባዶነት ለመቅረፍ የደም ሰማዕትነት የከፈሉት ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የ 20ኛው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስትያን ልጆች የክርስትናው ሕይወት የሚያነቃቁ ባዶነቱን በመንቀልም የእምነተ አመክንዮ የመሰከሩ ናቸው። ያመኑት እምነት ታማኝ መሆኑና የሚጠፋ ርእዮተ ዓለም ማለት እንዳልሆነ በከፈሉት የደም ሰማዕትነት በማረጋገጥ፣ የሰው ልጅ ሙላት እግዚአብሔር ነው ማለታቸው ሲኖዶሱ እንዳሰመረበት የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠና ፒሮ አያይዘውም በዚህ በከትላትና በስትያ የሲኖዶሱ ውሎ የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኤቶሮቪች በቻይና ለ 20 ዓመታት በእስር የታጎሩት እ.ኤ.አ. በ 1979 ዓ.ም. ነጻ ተለቀው የፈንግሻይንግ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉካስ ልይ 90 ዓመተ ዕድሜ ያላቸው ለሲኖዶስ ያስተላለፉት የምስክርነት ቃል መልእክት ተነቦ፣ ብፁዕ አቡነ ልዩ የሲኖዶስ አበው ጉባኤ የተዋጣለት እንዲሆን እንደሚጸልዩና ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና ለሲንዶስ አበው በመንፈስ ቅርብ መሆናቸው እንዳረጋገጡ ብፁዕ አቡነ ኤቶሮቪች ካነበቡት መልእክት ለመረዳት እንደተቻለ አስታውቀዋል።
በመቀጠልም ጉባኤው በሃይቲ በመካሄድ ላይ ስላለው ዳግመ ግንባታ ብሎም በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የአለማውያን ምእመናን ተሳተፎ የማያሻማ መሆኑና የቤተ ክርስትያን በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ክርስትናን ለማስፋፋት የሁሉም ትብብር የሚጠይቅ ዓላማ መሆኑ ብፁዓን አበው እንዳሳሰቡ ኢዛቤላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤቶች ካቶሊካዊ መለያቸው በማጉላት እምነት በቤተ ክርስትያን የሚኖር በቁምስና የሚገለጥ ብቻ ሳይሆን ካቶሊካዊነት እምነት የሚያንጸባርቁ እንዲሆኑም ብፁዓን አበው በማሳሰብ በአፍሪቃ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ክርስትና ለማስፋፋት ተግባር ባህሎችን መስበክ በሚል ሐዋርያዊ ግብረ ኖውሎ እንዲረጋገጥ የመሐሪው ክርስቶስ ማንነት ምሥጢረ ንስሐ እርቅ ይቅር የመባባሉ የክርስትያናዊ ሕይወት ምርጫ የሚጠይቀው ወንጌላዊ ሕይወት በማነቃቃት የኃጢአት ትርጉም የምህረት ጸጋ ማለትም የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ቡራኬ ላይ ያለው ግንዛቤ ማጎልበት በአፍሪቃ አንገንጋቢ መሆኑ የሲኖዶስ አበው እንዳመለከቱም ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አመለከቱ።
ቅዱስ ቍርባን የመንፈሳዊ ሕይወት ምንጭ ሰው በመለኮታዊ ውበት እንዲማረክ የሚያደርግ መሆኑ በማተኮርም በእስያ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊጡርጊያዊ ባህልና ትውፊት ላይ ግንዛቤ እንዲያድግ ሊጡርጊያ በተመለከተ የተለያዩ ደጋፊ የጥናት ጽሑፎች እንዲቀርብ በማረግ ቤተ ክርስታይንና ሊጡርጊያዋ ማስተዋወቅ ያለው አስፈላጊነት መገለጡ ለማወቅ ሲቻል። በዚያኑ ዕለት ከቅትር በኋላ በተካሄደው ጉባኤም ብፁዓን አበው፣ በቅዱሳን ማንነት ላይ በማተኮር በእምነትና በሕይወት ግልጽና ያልተወሳሰቡ እምነት በቃልና በተግባር የመሰከሩ በማብራራት፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የተስተካከለ ሕይወት ለክርስትና መስፋፋት ያለው አቢይ ድጋፍ በማጉላት ክርስትናን በፈረቃ በማይኖር ሕይወት እምነት በመመስከር ክርስትያን ክርስትና ለማስፋፋት የሚኖረው ሕይወት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማለት መሆኑ እንዳሰመሩበት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታወቁ።
ወንጌላዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማለት ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ያተኮረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በበለጠ እንዲበራታታና ምእመናን ቅዱስ መጽሓፍ በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤና እውቀት ከፍ እንዲል በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማነቃቃት ያለው አስፈላጊነትም ብፁዓን አበው ገልጠው፣ በሰበካዎችና በቁምስናዎች በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የጋራ እቅድ ተወጥኖ ተመሳሳይ በሆነ መልኵ እንዲከናወን በምእመናን በቁምስናዎችና በሰበካዎች ትብብርና መቀራረብ ውህደት በማጠናከር ከተለያዩ ክፍሎች የሚሰነዘርው ተጋርጦ በጋራና በተባበረ የእምነት ኃይል አማካኝነት በማሸነፍ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማረጋገጥ እንደሚቻል ማሳሰባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ችግሮች ለአደጋ ተጋልጦ የሚገኘው ቤተሰብ፣ በስደት በከተማ መስፋፋት፣ በፍች በተለያዩ በሽታዎች የሚደርስበት እክል ለይቶ ለመቅረፍ ምሥጢረ ተክሊል ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ብቻ አድርጎ ከመመልክቱ ኣዝማሚይ ተገሎ፣ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ቲዮሎጊያዊ ስነ ሰብእ ገጽታውን በማጉላት በዚሁ ዘርፍ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እግብር ላይ ማዋል ብፁዓን አበው አስፍላጊነቱ እንደተወያዩበት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.