2012-10-17 18:23:49

13ኛ መደበኛ አጠቃላይ የጳጳስ ሲኖዶስ ጉባኤ


ቤተ ክርስትያን አዳዲስ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና አዳዲስ የቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎችን እንደ የአዲስ ስብከተ ወንጌል ጸደይ መቀበል አለባት ሲሉ የ13ኛው መደበኛ ጉባኤ የጳጳሳት ሲኖዶስ አበው ዛሬም ስብሰባቸውን በመቀጠል ስለ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስም ሳይቀር በመወያየት ተወያይተዋል፣ ማምሻውን በዋሽንግቶን ሊቀ ጳጳስና የሲኖዶሱ ዋና አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ዶናልድ ውርል በሚቀርበው ዘገባ ይወያያሉ፣
የመንፈስ ቅዱስ ስጦጣዎችና አዳዲሱ የቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎች ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል እንደ አዲስ ጸደይ ማየት እንደሚያስፈልግ ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያን እነኚህን እንቅስቃሴዎች ስትቀበል የሱታፌ እና የኅብረት መንፈስን እግምት ውስጥ በማግባት መሆን እንዳለበት በማሳሰብ አባቶችን የሚያስፈሩና እንደ መከላከያ ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች መራቅና አንዳንዴም እንቅስቃሴዎችን እስከ ማውገዝ የሚያደርሰው ፍራቻ መወገድና ሁሉንም ለጥቅም መዋል እንደሚቻል ተውያዩበት፣ አንዳንዴ ካህናት ለእነዚህ እንቅስቃሴዎች ባለመዘጋጀቸው እና ለነፍሳት ጥበቃ ሲሉ መንፈሳዊ ድርቀት እስከ ማስከተል እንደሚጸኑ በማመለከት ግዜው የደረሰ ስለሚመስል ቤተ ክርስትያን ለእነዚህ እንቅስቃሴዎች ብርዋን መክፈት እንዳለባት አሳስበዋል፣ እርግጥ ነው አንዳንዴ የዚህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ወዲያውኑ ተሎ ይጠፋሉ የቤተ ክርስትያንን ትምህርት ለመቋወም እንደተነሱ አብዮታዊ እንቅስቃሴዎችም ሆነው ይታያሉ ሆኖም ግን አዲሱ ስብከተ ወንጌል እነኚህን መሣርያዎች ኃያል መሣርያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት እንደሌለበት አሳስበዋል፣
የሲኖዶሱ አበው ከዛ በመቀጠል የተመለከቱት ጉዳይ ግሎባዊ የምጣኔ ሃብት ቀውስን ሲሆን እንደ አጋጣሚ አሁን አለማችንን ማጥቃቱ ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል ዕንቅፋት ሊሆን እንደሚችልና የማኅበረሰባዊና የእምነት ቀውስም ሊያስከትል እንደሚችል አልደበቁም፣ ስለዚህ ይህንን እውነት በመቀበል በእያንዳንዱ አገር ሰበካና ቍምስና ችግረኞች ሊረዱበት የሚችሉበት መፍትሔ በመፈለግ ለምጣኔ ሃብቱ ቀውስ መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ የመታባበርና የኅብረትሰባዊ የብድርና የዕድር መዋቅሮች መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተወያዩበት፤ በዚህ መንገድ ብቻ ከዕዳ ነጻ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ መዋቅርና ለሰው ልጅ አገልግሎት የሚውል አግባብ ሊፈጠር እንደሚችል ገልጠዋል፣ በዚህም ቤተ ክርስትያን የምጣኔ ሃብት ቀውሱን ተፈጥሮንና አከባቢን በመጠበቅና የሰው ልጅ መብትን በሚያስከብር ሁኔታ ችግሩን ለመቅረፍ እንድትችል ይሁን ሲሉ ማሳሳቢያ አቅርበዋል፣
ከመስመሩ ሳይወጡ አበው የሴቶችና የሕጻናትን ሁኔታ በማስታወስ አዲሱ ስብከተ ወንጌል እነኚህን ሁለት ነጥቦች ካላተኰረና ለችግሮቻቸው መፍትሔ ካላገኘ ስኬታም ሊሆን አይችልም ሲሉ እያንዳንዱ ይህንን እግምት ውስት ማግባት እንዳለበትም አሳስበዋል፣
በዚህ መስክ ብዙ የሚያበረክቱ ጳጳሳዊ ተቅዋሞችና እንቅስቃሴዎችን በማስታወስ የሲኖዶሱ አበው እነኚህ አውታሮች በሄዱበት አካባቢና አገልግሎት በሚሰጥበት መስክ ሙሉ ነጻነት እንዲያገኙና ነጻነታቸውም በተነካ ሁኔታና አጋጣሚ ሁላቸው አብረው እንዲከላከሉለትና በእነዚህ ተቅዋሞች ለሰላምና ለመሠረታውያን የሰው ልጅ መብት የሚበረከተውን አገልግሎት ማስታወስ እንዳለብን አሳስበዋል፣
ሲኖዶሱ በዛሬ ዕለት ውይይቱ በመጨረሻ ያመለከተው በብዛት ሙስሊሞች በሚገኙባቸው አገሮች አዲስ ስብከተ ወንጌል እንዴት እተግባር ላይ መዋል እንደሚቻል ሲሆን በእነዚህ አገሮች ክርስትያኖች ሁሌ እንደ ሁለተኛ ዜጎች የሚመለከቱበትን ሁኔታ እንዴት መሻሻል እንደሚቻል እንዲሁም የአምልኮ ነጻነትንና ውስጠ ሃይማኖታዊ ውይይት እንዴት ማዳበር እንደሚቻል መፍትሔ በመሻት ተወያይተዋል፣ በእነዚሁ አገሮች በሚካሄዱ የትምህርትና የምግባረ ሠናይ ተል እኮዎች ዋነኛ ምስክርነቶች መሆናቸውን በማስታወስም ቤተ ክርስትያን ብዙ እንደምታበርክት አመልክተዋል፣
ቤተ ክርስትያን በቍምስናዎችዋና በምታበርክታቸው በብዙ ጐሣዎችና ሃይማኖቶች መካከል የምትሰጠውን አገልግሎት ለአዲስ ስብከተ ወንጌል በሚረዳ መንገድ እንዲደረግ አሳስበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.