2012-10-15 14:44:09

ፓትሪያርክ ብፁዕ አብነ ፉዋድ ጥዋል፦ በመካከለኛው ምስራቅ ሃይማኖታዊ አክራሪነት እየተስፋፋ በመሆን የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ለብቻው እንዳይተው ጥሪ አቀረቡ


በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመስተፍ ላይ የሚገኙት በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካትሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ለሲኖዶስ ባሰሙት ንግግር እምነትን ለማስተላለፍ ቅድስት መሬትን ዳግም ማግኘት ማለት መሆኑ ገልጠው፣ ቅድስት መሬት RealAudioMP3 ያላት ጥሪና መንፈሳዊነትና ታሪክዋን ዳግም ማግኘት አስፈላጊ ነው እንዳሉ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸንን ያሰሙት ንግግር አንኳር የሆነውን ነጥበ በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እምነት የተወለደውና ሌሎች የተካፈለበት የመጀመሪያ ክልል የቅድስት መሬት ክልል ነው። ምክንያቱ የእምነት ማእከል ኢየሱስ ክርስቶስና እርሱን የተከተሉት ደቀ መዛሙርት የኖሩትና ያስተላለፉት እምነት ብዙ መሥዋዕትነት ለመክፈል ምክንያት የሆነው እምንት ዛሬ በክልሉ ማኅበረ ክርስትያን በውሉደ ክህነት አባላት በወጣቶች ዘንድ ኅያው ነውን የሚል ጥያቄ በማቅረብ በዘልማድ የሚኖር ክርስትና እጅግ ያስፈራኛል” ብለዋል።
የቅድስት መሬት ማኅበረ ክርስትያን የእምነት አብነት ነው ሲሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሉት ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ “አብነት የሚያስብለውም ስለ ሚጸልይ፣ በቅዱስ ቁርባን የሚሳተፍ የሚሰዋ ፍቅር የሚካፈል እርሱም በተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤቶች በሕንጸት ማእከሎች በሕክምና ቤቶች በኩል የሚኖረውና በተግባር የሚመሰክረው እመነት በመሆኑ ነው። በአይሁድና በክርስትና እምነት መካከል የሚከናወነው የጋራ ውይይትም በእውነቱ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ከቅድስት መሬት የሚጀምር መሆን እንዳለበት ያረጋግጥልናል” ብለዋል።
መካከለኛው ምስራቅ በአረብ አገሮች ጸደይ ገጠመኝ በቀጥታ የተነካ መሆኑ አስታውሰው፣ ይህ የቅርቡ ገና በመቀጠል ላይ ያለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘግምተኛ ለውጥ በትክክል ካልተመራ እንደሚታየውም ለሃይማኖታዊ አክራሪነት ለም መሬት ሆኖ ነው የሚገኘው፣ ስለዚህ ለዚህ ክልል ማኅበረ ክርስትያን የተጋረጠው ሁኔታ መገመቱ አያዳግትም፣ የሲኖዶስ አበውም ይኸንን ተገንዝበው ለመካከለኛው ምስራቅ ጸልየዋል።
ምንም’ኳ በመካከለኛው ምስራቅ ለማኅበረ ክርስትያን የማያመች አስቸጋሪ ሁኔታ እየተፈጠረ ለስደት የሚዳርግ ሆኖ ቢገኝም ቅሉ፣ ቅድስት መሬት አለ ማኅብረ ክርስትያን መቅረት የለባት፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን እንዳሉትም ማኅበረ ክርስትያን የተጋረጠባቸው እክል በመወጣት በክልላቸው እምነትን እንዲመሰክሩ ያሉትን ሃሳብ የራሳቸው በማድረግ ጥሪ አስተላልፈው፣ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ለብቻው እንዳልሆነ በተጨባጭ ሁኔታ የሚመሰክር ተመክሮ አለ፣ ምንም’ኳ የመካከለኛው ምስራቅ ውሁዳን የክልሉ ክፍለ ኅብረተሰብ ቢሆንም የኩላዊት ቤተ ክርስትይን መንፈስ በሚያንጸርቁ መንፈሳዊ ነጋድያን ድጋፍና ጸሎት ፈጽሞ ውሁድ እንዳልሆነ ነው የሚሰማው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.