2012-10-15 14:32:46

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ምድራዊ ሀብት በምድራዊ ዓለም ደስታና ዘለአለማዊ ሕይወትን አያሰጥም፣ በድኽነት ከተጠቁት ጋር ተካፍሎ መኖርን ይጠያቃል


ትላንታን እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በላቲን ሥርዓት የእለቱ ሰንበት እርሱም “በሀብታሙ ወጣት ጥያቄ” ላይ ያነጣጠረውን ምንባብ ቅዱስ ወንጌል ተንተርሰው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት አስተምህሮ፣ RealAudioMP3 “ምድራዊ ሀብት በምድራዊ ሕይወት ደስታና ዘለአለማዊ ሕይወት አያሰጥም ከድኾች ጋር ተካፍሎ መኖርን ይጠይቃል፣ ሀብታሙ ወጣቱ እንደ ሁሉም በዘለዓለማዊ ሕይወት ፍላጎት የተማረከ ሲሆን በሌላው ረገድ በገዛ እራስ ሃብት ላይ መተማመን የተላመደ ዘለዓለማዊው ሕይወት ልዩ ትእዛዞችን በመፈጸም በእጅ ለማስገባቱ እድል ያለው እንደሆነም ይገምታል” ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣቱ በፍቅር ዓይን እርሱም በእግዚአብሔር ዓይኖች አተኵሮ በመመልከት፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የወጣቱን ደካማውን ጉኑን ለይቶ በማወቅ፣ ማለትም ከምድራዊ ሀብት ጋር ያለው ትስስር ጠንቅቆ የሚያውቀው በመሆኑ፣ ሁሉን ለድኾች እንዲሰጥ ልቡ ከምድራዊ ሀብት ጋር ካለው ትስስር አላቆ ከሰማያዊ ቤት ጋር እንዲያስተሳስር በማሳሰብ ይኸንን ካደረገ በኋላ ‘ናና ተከተለኝ’ ሆኖም ኢየሱስ ያቀረበለት ቅድመ ሁኔታ በደስታ ከመቀበል ይልቅ ዘለዓለማዊ ደስታ ሊሰጠው ከማይችለው ከምድራዊው ሀብት ገዛ እራሱን ማላቀቅ ስለተሳነው ‘እየተከዘ ተለይቶት ሄደ’፣ ኢየሱስ ሀብታም የእግዚአብሔርን መንግሥት ይወርስ ዘንድ ምንኛ ከባድ ቢሆንም፣ ነገር ግን የማይቻል ማለት እንዳልሆነ ሲያስተምር፦ “እግዚአብሔር ብዙ ሀብት ያለው ሰው ለመማረክ እንደሚችልና ከድኾች ጋር ተካፍሎ መኖርንና መተባበርንም እንዲተገብር ይገፋፋል፣ ይኽም የሚሰዋ ፍቅር አመክኖዮ እንዲኖር ይጋብዛል” የቤተ ክርስትያን ታሪክም የነበራቸው ምድራዊ ሀብት በወንጌላዊ ሥልት በመኖር ለቅድስና የበቁ ብዙ መሆናቸው የቤተ ክርስትያን ያመለክታል፣ ለምሳሌም ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ፣ ቅድስት ኤሊሳቤጥ ዘሃንጋሪ ቅዱስ ካርሎስ ቦሮመዮ በማስታወስ፣ ቅዱስ ቄለመንጦስ ዘእስክንድሪያን በመጥቀስም “በወንጌል የሚገለጠው የሀብታሙ ወጣት ምሳሌ፣ በምድራዊ ሀብት የታደሉት ሁሉ ልክ እንደ ተወገዘ የድህነት ጸጋን ቸል በማለት መኖር ወይንም ሀብትን አርግፍ አድርጎ በመጣል ወይንም ለዘአለዓምዊ ሕይወት እንቅፋት ነው በሚል ጭፍን ቅድመ ፍርድ ውስጥ ውስጥ እንደ ሚያደባ ጠላት አድርጎ መመልከት ሳይሆን፣ በትክክልና በተገባ ሥርዓት እንዴት አድርገው ሊጠቀሙበት እንደሚገባቸው ማወቅ ያስፈልጋል” ካሉ በኋላ ቅዳሜ በፕራግ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ያወጀችላቸው እ.ኤ.አ. በ 1611 ዓ.ም. የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት ፈደሪኮ ባችስታይንና ሌሎች 13 የንኡሳን ወንድሞች ማኅበር አባላት ወንድሞቹን አስታውሰው፣ “እነዚህ ብፁዓን በዚህ የእምነት ዓመት ወቅት ብፅዕና የታወጀላችው ቀደምት ናቸው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ገዛ እራስ ከርእሩ ጋር ስለ አርሱ ለመሰቃየት ዝግጁ መሆን ይጠይቃል” በማለትም፣ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቀን ለማክበር ከፖላንድ የመጡት የሚገግኙባቸው ከውስጥና ከውጭ የመጡት ምእመናን ሁሉን ሰላምታን አቅርበው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው ሐዋርያው ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.