2012-10-15 14:36:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኢየስስ ከህይወት በኋላ ሌላ ህይወትና እግዚአብሔር መኖሩም አይታወቅም ብለው ከሚያምኑት ጎን በጽሞና አብሯቸው ይጓዛል


ትላንትና እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሲኖዶስ ብፁዓን አበው የመላ አገሮች ካቶልካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት የዛሬ 50 ዓመት በፊት በሁለተኛው የቫቲካን ቅዱስ ጉባኤ ከተስተፉት ውስጥ በሕይወት ያሉት 69 ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት፣ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርትጠለመዎስ አንደኛ የውህደት አንግሊካዊት RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊሊያምስ በተገኙበት የምሳ ማዕድ ግብዣ ተቋድሰው ባሰሙት ንግግር፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ከሲኖዶስ አበው ጋር የምሳ ማዕድ ሲቋደስ ደስ የሚያሰኘው ውብ ባህል ጀማሪ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን ዘክረው፣ ይኸንን ባህል በመከተል በምሳ ግብዣ ከሁሉም የ 13ኛው ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ ተሳታፊዎች ጋር መገናኘት እንዲሁ የፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊሊያም በማዕዱ መገኘታቸው አመስግነው፦ “አጋጣሚው ለውህደት በታለመው ጎዞ ያለው ትብብር የሚያጎላ መሆኑና ለውህደት በሚያስበው ልብ ተባብሮ መገኘት ለሚደረገው የጋራ ጉዞ ምስክር ነው። ስለዚህ ይኸንን ውስጣዊው የተወሃደው የጋራው ጎዞ በውጫዊው ተጨባጭ እውን ይሆንም ዘንድ እግዚአብሒር ይደግፈናል” ብለዋል።
አብሮ መሆን የሚሰጠው ደስታ ለተሰጠው የጋራው አስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ እንደሚያጠነክረው በወንጌል ሰፍሮ ያለው የሁለት የኤማሁስ ደቀ መዛሙርት ታሪክ በማስታወስ፣ ይኽ ከህይወት በኋላ ሌላ ህይወትና እግዚአብሔር መኖሩም አይታወቅም ብለው ለሚያምኑት” ተምሳይ መግለጫ መሆኑ አብራርተው፣ እነዚህ የኤማኡስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱሰኛው ተስፋቸው ጨልሞ ዓለም ቦዶና እግዚአብሔር የሌለ ወይንም ስለ ሕያዋን ግድ የማይል ነው በሚለው ባዶነት ተከበው ነገር ግን ጨርሶ ያላከተመለት የእምነት ጭላንጭል በውስጣቸው በማኖር በመጋዝ ላይ እያሉ፦ “ጌታ በምሥጢር አብሮአቸው በመሆን በታሪክ የእርሱ በጽሞና አብሮ ለመጓዝ ማረጋገጫ የሆነው የእግዚአብሔር ምሥጢረ ኅልውና እንዲረዱት ይደግፋቸዋል። ከእራት ማእድ በኋላ ይነግራቸው የነበረው ያዳመጡት ቃል ለልባቸው ኃሴት ለአእምሮአቸው ብርሃን ሁኖላቸው በእራት ማእድ እንዳወቁትና ልባቸው እውነተኛ ማየትን እንደጀመረ ተገንዝበዋል” ያሉት ቅዱስ አባታችን አክለው፦ በሲኖዶሱ አማካኝንት ቤተ ክርስትያን ከወቅታዊው ሕዝብ ጋር አብራ በመጓዝ ላይ ትገኛለች በማለት፣ “እግዚአብሔር ብርሃኑን እንዲሰጠን ልባችንን እንዲያበራ ኅያው ምስክሮች እንዲያደርገን ጌታን እንጸልይ፣ በቅዱስ ቁርባን በሱታፌና በቅዱስ ማእድ በሙላት ክፍት ሆነን እርሱን ለማየት እንድንበቃና ለዓለም እንድንመሰክረው ብርሃኑን ለዓለማ እናካፍል ዘንድ እንዲረዳን እንጸልይ” በማለት ያሰሙትን ንግግር አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.