2012-10-15 14:40:52

ሲኖዶስ፣ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኦናየካን፦ የናይጀሪያ ክርስትያን ምእመናን አመጽን በሰላም መንገድ መልስ ይሰጡበት ዘንድ ጥሪ አቀረቡ


እዚህ በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው 13ኛው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስታይን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የአቡጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆን ኦሎኡንፈሚ ኦናየካን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በናይጀሪያ የሚገኘው ቦኮ ሃራም በማለት ገዛ እራሱ ለሰየመው አክራሪያን ሙስሊሞች RealAudioMP3 ሽበራ ዒላማ የሆኑት ማኅበረ ክርስትያን የናይጀሪያ ክፍለ ማኅበረ-ሰብ ናቸው፣ እነዚህ አሸባሪያ ሙስሊሞች የሚሰነዝሩት ጥቃት ካቶሊኮች ወይንም በቅላላ በክርስትያኖች ላይ ያነጣጠረ ብቻ ሳይሆን መላ አገሪቱን የሚያውክ የአገርና የሕዝብ ጠላት ነው። ይኽንን የአገሪቱ መንግሥት ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። በርግጥ በናይጀሪያ ማኅበረ ክርስትያን ውሁዳንና ለስደት የተጋለጡ ቢሆንም ቅሉ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር የአንግሊካዊት ቤተ ክርስታይን ምእመን ናቸው፣ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ካቶሊክ ናቸው” በማለት በናይጀሪያ ኅብረ - ሃይምኖትና ኅብረ - ባህላዊ ገጽታውን ገልጠው፣ ተከስቶ ያለው የጋራው አብሮ መኖር የሚያናጋው ተጋርጦ የሁሉም ተጋርጦ ነው፣ ስለዚህ ክርስትያኖች በተለይ ደግሞ ካቶሊኮች እምነታቸውን በተረጋግጦ እንዲኖሩት እና የሰላም ሰዎች መሆናቸው መመስከር እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
ምንም’ኳ አንዳንድ ክርስትያኖች ለሚደርስባቸው አመጽ ተስተካካይ ግብረ መልስ እንዲሰጥ የሚቃጣቸውና ይኽንን የሚያነቃቁ ያሉ ቢመስልም፣ መላው ማኅበረ ክርስትያን፣ ክርስትና አመጽ በአመጽ የሚል እንዳልሆነና በሰላም የሚሸነፍ መሆኑ የሚያውቁ መሆናቸው የገለጡት ብፁዕ አቡነ ኦናየካን አክለም፣ አክራሪው ኃይል በቀላሉ ለሚሰነዝሩት ጥቃት ኢላማ የሚያደጉት ክልል በጸጥታ ኃይል አባላት ጥበቃ ሥር ባለ መሆኑ፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ለዚህ ዓይነት ጥቃት በቀላሉ ተጋልጣ ትገኛለች፣ በአቢያተ ክርስትያን ክልል የዜጎችና የምእመናን ሕይወትና ጸጥታ ጥበቃ አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት ይኸንን ጉዳይ ግምት ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል።
አስፍሆተ ወንጌል በናይጀሪያ የቅርብ ታሪክ ተጨባጭ ሁኔታ ነው፣ ስለዚህ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በናይጀሪያ በአገሪቱ ለተሰበከው ወንጌል ዳግም በማነቃቃት አሜን በማለት ለተቀበልክው እምነት ማነቃቃት ማለት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.