2012-10-12 14:13:59

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ “የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አበው ፍላጎት ሌላ ቤተ ክርስትያን ለመፍጠር ሳይሆን ኅዳሴ በቀጣይነት ለማረጋገጥ ነው”


ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት የልዩ ኅትመት እቅዱን ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ ታሪካዊው የቅድስት መንበር ጉባኤ ወጣት ካህን በቲዮሎጊያ ሊቅነታቸውና በአማካሪነት በመሳተፍ የኖሩት ሕያው RealAudioMP3 የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተመክሮ የሚገልጥ ጽሑፋቸው በመጀመሪያ ገጽ በማስቀመጥ በይፋ ቀዳሜ ሕትመቱን የጀመረ ሲሆን፣ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ለዚህ ዝክረ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ተራኪ ጽሑፎች የስእል መግለጫዎች ጉባኤውና ጉባኤው የተካሄደበት ወቅት ታሪክ ሱታፌውና በመገናኛ ብዙሃን የተሰጠው ትኩረት ያካተተ እንደሚሆንም የተገለጠ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ “ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ሁሉንም አገሮችና ሕዝቦች የሚወክሉ ብፁዓን ጳጳሳት በአገረ ቫቲካን ለሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሲገናኙ ማየቱ በእውነቱ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን መላውን ዓለም ሁሉንም የሰው ዘር አለ ምንም ልዩነት እምታቅፍና የሁሉም በሰላም በአንድነት የመኖር ምልክት መሆንዋ ያረጋገጠ ሁኔታ የመሰከረ ነበር” እንዳሉ የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አክሎ፣ “የክርስትናው እምነት የደከመበት በሚመስለው በምዕራቡ ዓለም እምነትን ዳግም ማነቃቃት ያለው አስፈላጊነት ያስተጋባ እንደነበር በተለይ ደግሞ፣ ስለ ሥነ ፍጻሜ፣ ሥነ ግልጸትና መጽሓፍ ቅዱስ፣ የቤተ ክርስትያን ትውፊትና ሥልጣናዊ ትምህርት ሊጡርጊያዊ ተኃድሶ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ለውህደት የተሰኙት አንገብጋቢ ጉዳዮች የተነቃቃበት ነበር” ካሉ በኋላ ቤተ ክርስትያንና ወቅታዊው ዓለም፣ የተሰኙት ነጥቦች ላይ በማተኮረ የተወያየ ሆኖ፣ እነዚህ ነጥቦች ማእከል በማድረግ የተካሄደው ውይይት ሌሎች ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም በማቅረብ የሃይማኖት ነጻነት፣ የቤተ ክርስትያን ክርስትያን ካልሆኑት ሎሎች ሃይማኖቶች ጋር ግኑኝነት፣ ሃይማኖትን በነጻነት የመምረጡ መብት ብሎም ሃይማኖትን የመለወጥ መብት በማስተጋባትም ሃይማኖት በማኅበራዊ ባህላዊ ስነ ምግባራዊ መንፈሳዊ ረገድ ያለው አቢይ አስተዋጽኦ እውቅና በመስጠት ማቀብ” የተሰኙትን ማእከላዊ የጉባኤው ነጥቦችን ካብራሩ በኋላ፣ “ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ብፁዓን አበው በመንፈስ ቅዱስ ትምህርት ቤት ሥር መሆናቸውና በጋራ ለመተባበርና በእምነት የሚሠሩ የቃለ እግዚኣብሔር አገልጋዮች መሆናቸው ዳግም የተገነዘቡበት አቢይ ጉባኤ ነበር” እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.