2012-10-12 14:10:57

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም የእምነት ዓመት መክፈቻ ቀን፦ “ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ምድረ በዳነት ባጠቃው ወቅታዊው ዓለም ዳግም ክርስቶስን ታውጅ”


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና ጧት የእምነት ዓመት መክፈቻ፣ ዝክረ 50ኛው ዓመት የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ዝክረ 20ኛው ዓመት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ ምክንያት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በስምንት የምስራቅ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ፓትሪያርኮች ብፁዓን ጳጳሳት፣ 80 ብፁዓን ካርዲናሎች 15 የሲኖዶስ አበው በጠቅላላ በ 400 ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ታጅበው ከ 20 ሺሕ በላይ የሚገመቱት ከውጭና ከውስጥ የመቱጡት ምእመናን የተሳተፉበት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ በቤተ ክርስትያን ክርስቶስን የማወጁ እስትንፋስ ዳግም ኅያው ማድረግ ዋነኛው ዓላማ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፦ “ዛሬ በታላቅ ደስታ ዝክረ 50ኛው ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻ ቀን የእምንት ዓመት ሲከፈት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ቀን ነው” እንዳሉ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ኃሴት በተሞላበት መንፈሳዊነት የእምነት ዓመት ማስጀመር ክርስቶስ የእምነታችን ማእከል መሆኑ ባሰሙት ስብከት አበክረው፣ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለቤተ ክርስትያን የሰጠው ተልእኮ በደቀ መዛሙርቱ ላይ በመንፈስ ቅዱስ እፍ በማለት ቀጣይነቱ ያረጋገጠለትን አስፍሆተ ወንጌል ለዓለም የማቅረቡ ዓላማ ባለቤት ገዛ እርሱ እግዚኣብሔር ሲሆን፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ለክርስቶስ ድንቅ ተግባር ተቀዳሚ የአገልግሎት መሣሪያና አስፍፈላጊ መሆንዋ በማብራራት፣ የእምነት ዓመት በጠቅላላ ካለፉት የ 50 ዓመታት እርሱም ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ እ.ኤ.አ. በ 1967 ዓ.ም. የእምነት ዓመት ያወጁት በእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ ስድተኛ ሥልጣናዊ ትምህርት፣ እ.ኤ.አ. በ 2000 የእዮቤል ዓመት ምክንያት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላትና ዛሬ ነገም ብቸኛው አዳኝ መሆኑ ማእክልነቱን ዳግም ያስተጋቡበት በጠቅላላ ከቤተ ክርስትያን ሂደት ጋር የተጣመረ መሆኑ በማብራራት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማስጀመር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቆዝሞስና የታሪክ ማእከል መሆኑ በሚገልጠው በቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት ትምህርት ላይ ለመወያየት በጥያቄ ለማስገባት ሳይሆን፣ ይኸንን ዘወትር የሚኖር የማለይወጠው ዘለዓለማዊው አንቀጸ ሃይማኖት ዳግም አሜን ለማለትና እማኔውን ለማስተጋባት ነው ሲሉ የገለጡት የጉባኤው ትርጉም ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ይኽ አንቀጸ ሃይማኖት ማእከል በማድረግ ወቅታዊው ዓለም ለሚያቀርበው አንገብጋቢ ጥያቄ መልስ የሚስጥ ነው፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የእምነት ውበት ማንጸባረቅ የሚለው የቤተ ክርስትያን ተልእኮ በተመለከተ ያሳየው የጋለውና የሚማርክ ውይይት የእሳቸው ቀጥተኛ ተመክሮ እንደነበርም አስታውሰው፣ አስፈላጊው ጉዳይ “ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ምድረ በዳነት ባጠቃው ወቅታዊው ዓለም ዳግም ክርስቶስን ማወጅ” የሚለው ጥሪ መኖር ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገልጠዋል።
“ተቀዳሚው የቤተ ክርስትያን ዓለማ የሆነው አስፍሆተ ወንጌል፣ አለ ምንም የመደናገር ፈተና በተጨባጩና ትክክለኛ በሆነው መንገድ እርሱም በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔዎች ላይ ተመሥርቶ የሚከናወን መሆን አለበት፣ ስለዚህ ዳግም ወደ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነዶች መመለስና ማጤን አስፈላጊ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በእምነት ላይ አዲስ ውጥን ያኖረ ሳይሆን የማይለወጠው እምነት በዚህ ዘገምታዊ ለውጥ በሚታይበት ዓለም ዳግም ሕያው ለማድረግ ምን መደረግ አለበት በሚለው ሃሳብ ላይ ነው የተወያየው፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ በተለያየ ውሳኔዎቹ መሠረት ሰጥቶበታል። በዚህ በምድረ በዳው ዓለም በሕወታቸው ቃል የተገባውችውን መሬት የሚያመለክቱ ተስፋን የሚያጸኑ የእምነት ሰዎች እጅግ ያስፈልጋሉ፣ በሕይወት የሚኖር እምነት ልብን ከጨለምተኝነት ፈተና ለሚያላቅቀው ለእግዚአብሔር ጸጋ ክፍት ያደርጋል። አስፍሆተ ወንጌል ከምን ግዜም በበለጠ ዛሬ በእግዚአብሔር የተለወጠ መንገድን በሚጠቁም አዲስ ሕይወት መመስከር ማለት ነው”ንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ካጠናቅሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በዕለቱ ሁለተኛው ምንባብ የነጋድያን ጥበብ ላይ ያተኮረ፣ ጥበበኛው ተጓዥ የኑሮው ሕይወት በስነ ጥበብ ተመክሮ ሃብታምና በተካፍሎ መኖር የሚያንፅ እንደሆነም ቅዱስ አባታችን ሲያብራሩ፦ “የእምነት ዓመት በወቅታዊው ዓለም ምድረ በዳ መንፈሳዊ ነጋድያን በመሆን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ብቻ አንግቦ፣ ‘ለመንገድ የሚሆነውን በትርም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን ስንቅም ቢሆን ገንዘብም ቢሆን ቅያሬ ልብስም እንኳ ቢሆን አትያዙ’ (ሉቃ. 9፣3) ወንጌልና የቤተ ክርስትይንን እምነት ብቻ ይዞ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በትክክል አስቀምጦት ይገኛል፣ ዝክረ 20ኛው ዓመት በመታሰብ ላይ ያለው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በማጠቃለያው ቅድስት ድንግል ማርያም በአስፍሆተ ወንጌል የጉዞ የመንገድ ብርሃነ ኮከብ ሁኚ” በማለት ያስቀመጠው ጸሎት በመድገምም ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.