2012-10-10 14:02:26

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ የድጋፍና የትብብር መርሃ የሚያሰናክል እንዳይሆን መጠንቀቅ


ጀነቭ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ባለፉት ቀናት የተባበሩት መንሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የባላይ ድርገት ባካሄደው RealAudioMP3 63ኛው ክፍለ ስብሰባው ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚና የቁጠባ ቀውስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ አገሮች በጦርነት ምክንያት ለሚሰደዱት መርጃ የሚሰጠው ድጋፍ ማደናቀፍ የለበትም” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ግጭት የሚካሄድባቸው አገሮች ቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱንም የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ቶማሲ አክለው ይኽ ችግር የስደተኞች ብዛት ከፍ እንዲል ከማድረጉም አልፎ በብዛት ሴቶችና ሕፃናት እንዲሁም በእድሜ የገፉት ዜጎች ለከፋ አደጋ እያጋለጠ መሆኑና ከጦርነት ከተለያዩ ችግሮች ሕይወትን ለማዳን መሰደድ ግድ ነው። ስለዚህ እነዚህን ስደተኞች ማስተናገድና ተገቢ እርዳታ የማቅረቡ ኃላፊነት የሁሉም ነው። ለነዚህ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ከሚሰጠው መሠረታዊ ድጋፍ በተጨማሪም ሥነ አእምሮአዊ ማኅበራዊ ብሎም ገዛ እራሳቸውን እንዲችሉ ታልሞ የሚሰጣቸው ሕንጸት ያካተተ መሆኑ ገልጠው፣ ይኸንን ሰፊ የድጋፍ መርሃ ግብር በዓለማችን ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ መጓተት ወይንም መሰናከል የለበትም እንዳሉ ጋዜጠኛ ላ ቨላ ባጠናቀሩት ዘገባ ጠቅሰው፣ ቅድስት መንበር በተወካይዋ ብፁዕ አቡነ ቶማሲ በኩል ስደተኞችና ተፈናቃዮችን ለማስተናገድና ለመደገፍ የተለያዩ አገሮች የሚሰጡት አስተዋጽኦ ምክንያት ምስጋናዋን በማቅረብ፣ በዚሁ መርሃ ግብር ቅድስት መንበር አቢይ ብቻ ሳይሆን፣ ተቀዳሚ ሚና የምትጫወትም መሆንዋ አስታውሰው፣ የዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ ሕዝቦችን ለስደተና ለመፈናቀል የሚዳርጉትን ችግሮች ከወዲሁ በመቅረፍ መርሃ ግብር ጠንቅቆ እንዲበረታ ብፁዕነታቸው አደራ በማለት፣ በሕዝቦች መካከል እርቅ ምህረትና ይቅር ባይነት ትብብርና መደጋገፍ እንዲበረታም ማድረግ ለችግሩ መሠረታዊ መፍትሔ ማሰጠት እንደሆነም አብራርተው፣ ለሁሉም ሰው ልጅ ጸጥታና ደህንነት ማረጋገጥ የመንግሥታት ግብረ ገባዊ ግዴታ ብሎም ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ኃላፊነት ነው እንዳሉ ጋዜጠኛ ላ ቨላ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.